1የእስራኤልም፡ልጆች፡እነዚህ፡ናቸው፤ሮቤል፥ስምዖን፥ሌዊ፥ይሁዳ፥ይሳኮር፥ዛብሎን፥
2ዳን፥ዮሴፍ፥ብንያም፥ንፍታሌም፥ጋድ፥አሴር።
3የይሁዳ፡ልጆች፤ዔር፥አውናን፥ሴሎም፤እነዚህ፡ሦስቱ፡ከከነዓናዊቱ፡ከሴዋ፡ልጅ፡ተወለዱለት።የይሁዳም፡ የበኵር፡ልጅ፡ዔር፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ክፉ፡ነበረ፤ገደለውም።
4ምራቱም፡ትዕማር፡ፋሬስንና፡ዛራን፡ወለደችለት፤የይሁዳም፡ልጆች፡ዅሉ፡ዐምስት፡ነበሩ።
5የፋሬስ፡ልጆች፤ኤስሮም፥ሐሙል።
6የዛራም፡ልጆች፤ዘምሪ፥ኤታን፥ሄማን፥
7ከልኮል፥ዳራ፤ዅሉም፡ዐምስት፡ነበሩ።የከርሚም፡ልጅ፡እስራኤልን፡ያስጨነቀ፥ዕርሙንም፡ሰርቆ፡የበደለ፡ ዐካን፡ነበረ።
8የኤታንም፡ልጅ፡ዐዛርያ፡ነበረ።
9ለኤስሮም፡የተወለዱለት፡ልጆች፤ይረሕምኤል፣አራም፣ካልብ፡ነበሩ።
10አራምም፡ዐሚናዳብን፡ወለደ፤ዐሚናዳብም፡የይሁዳን፡ልጆች፡አለቃ፡ነአሶንን፡ወለደ፤
11ነአሶንም፡ሰልሞንን፡ወለደ፤ሰልሞንም፡ቦዔዝን፡ወለደ፤
12ቦዔዝም፡ኢዮቤድን፡ወለደ፤ኢዮቤድም፡እሴይን፡ወለደ፤
13እሴይም፡የበኵር፡ልጁን፡ኤልያብን፥ኹለተኛውንም፡ዐሚናዳብን፥ሦስተኛውንም፡ሳማን፥
14አራተኛውንም፡ናትናኤልን፥
15ዐምስተኛውንም፡ራዳይን፥ስድስተኛውንም፡አሳምን፥ሰባተኛውንም፡ዳዊትን፡ወለደ፤
16እኅቶቻቸውም፡ጽሩያና፡አቢግያ፡ነበሩ።የጽሩያም፡ልጆች፡አቢሳ፥ኢዮአብ፥ዐሳሄል፡ሦስቱ፡ነበሩ።
17አቢግያም፡ዐማሳይን፡ወለደች፤የዐማሳይም፡አባት፡እስማኤላዊው፡ዬቴር፡ነበረ።
18የኤስሮምም፡ልጅ፡ካሌብ፡ከሚስቱ፡ከዓዙባ፡ከይሪዖትም፡ልጆች፡ወለደ፤ልጆቿም፡ያሳር፥ሶባብ፥አርዶን፡ ነበሩ።
19ዓዙባም፡ሞተች፥ካሌብም፡ኤፍራታን፡አገባ፤ርሷም፡ሆርን፡ወለደችለት።
20ሆርም፡ኡሪን፡ወለደ፥ኡሪም፡ባስልኤልን፡ወለደ።
21ከዚያም፡በዃላ፡ኤስሮም፡ስድሳ፡ዓመት፡በኾነው፡ጊዜ፡ወዳገባት፡ወደገለዓድ፡አባት፡ወደማኪር፡ልጅ፡ ገባ፤ሰጉብንም፡ወለደችለት።ሰጉብም፡ኢያዕርን፡ወለደ፤
22ለርሱም፡በገለዓድ፡ምድር፡ኻያ፡ሦስት፡ከተማዎች፡ነበሩት።
23ጌሹርና፡አራምም፡የኢያዕርን፡ከተማዎች፡ከቄናትና፡ከመንደሮቿ፡ጋራ፡ስድሳውን፡ከተማዎች፡ ወሰዱባቸው።እነዚህ፡ዅሉ፡የገለዓድ፡አባት፡የማኪር፡ልጆች፡ነበሩ።
24ኤስሮምም፡በካሌብ፡ኤፍራታ፡ከሞተ፡በዃላ፡የኤስሮም፡ሚስት፡አቢያ፡የቴቁሔን ፡አባት፡አሽሑርን፡ ወለደችለት።
25የኤስሮምም፡የበኵር፡ልጁ፡የይረሕምኤል፡ልጆች፡በኵሩ፡ራም፥ቡናህ፥ኦሬን፥ኦጼም፥አኪያ፡ነበሩ።
26ለይረሕምኤልም፡ዓጣራ፡የተባለች፡ሌላ፡ሚስት፡ነበረችው፤ርሷም፡የኦናም፡እናት፡ነበረች።
27የይረሕምኤል፡የበኵሩ፡የራም፡ልጆች፡መዓስ፥ያሚን፥ዔቄር፡ነበሩ።
28የኦናምም፡ልጆች፡ሸማይና፡ያዳ፡ነበሩ።የሸማይ፡ልጆች፡ናዳብና፡አቢሱር፡ነበሩ። 186 ዕብ.፥ቴቆዐህ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
29የአቢሱርም፡ሚስት፡አቢካኢል፡ነበረች፤አኅባንንና፡ሞሊድን፡ወለደችለት።
30የናዳብም፡ልጆች፡ሴሊድና፡አፋይም፡ነበሩ፤ሴሌድም፡ያለልጆች፡ሞተ።
31የአፋይምም፡ልጅ፡ይሽዒ፥የይሽዒም፡ልጅ፡ሶሳን፥የሶሳንም፡ልጅ፡አሕላይ፡ነበረ።
32የሸማይም፡ወንድም፡የያዳ፡ልጆች፡ዬቴርና፡ዮናታን፡ነበሩ፤ዬቴርም፡ያለልጆች፡ሞተ።
33የዮናታንም፡ልጆች፡ፌሌትና፡ዛዛ፡ነበሩ፤እነዚህ፡የይረሕምኤል፡ልጆች፡ነበሩ።
34ለሶሳንም፡ሴቶች፡ልጆች፡እንጂ፡ወንዶች፡ልጆች፡አልነበሩትም፤ለሶሳንም፡ኢዮሄል፡የተባለ፡ግብጻዊ፡ አገልጋይ፡ነበረው።
35ሶሳንም፡ለአገልጋዩ፡ለኢዮሄል፡ልጁን፡አጋባት፥ርሷም፡ዐታይን፡ወለደችለት።
36ዐታይም፡ናታንን፡ወለደ፤ናታንም፡ዛባድን፡ወለደ፤
37ዛባድም፡ኤፍላልን፡ወለደ፤ኤፍላልም፡ዖቤድን፡ወለደ፤ዖቤድም፡ኢዩን፡ወለደ፤
38ኢዩም፡ዐዛርያስን፡ወለደ፤
39ዐዛርያስም፡ኬሌስን፡ወለደ፤ኬሌስም፡ኤልዓሣን፡ወለደ፤
40ኤልዓሣም፡ሲስማይን፡ወለደ፤
41ሲስማይም፡ሰሎምን፡ወለደ፤ሰሎምም፡የቃምያን፡ወለደ፤የቃምያም፡ኤሊሳማን፡ወለደ።
42የይረሕምኤልም፡ወንድም፡የካሌብ፡ልጆች፡በኵሩ፡የዚፍ፡አባት፡ሞሳ፥የኬብሮንም፡አባት፡የመሪሳ፡ ልጆች፡ነበሩ።
43የኬብሮንም፡ልጆች፡ቆሬ፥ተፉዋ፥ሬቄም፥ሽማዕ፡ነበሩ።
44ሽማዕም፡የዮርቅዓምን፡አባት፡ረሐምን፡ወለደ፤ሬቄምም፡ሸማይን፡ወለደ።
45የሸማይም፡ልጅ፡ማዖን፡ነበረ፤ማዖንም፡የቤትጹር፡አባት፡ነበረ።
46የካሌብም፡ቁባት፡ዔፋ፡ሀራንን፥ሞዳን፥ጋዜዝን፡ወለደች።
47ሀራንም፡ጋዜዝን፡ወለደ።የያህዳይም፡ልጆች፡ሬጌም፥ኢዮታም፥ጌሻን፥ፋሌጥ፥ሔፋ፥ሸዓፍ፡ነበሩ።
48የካሌብም፡ቁባት፡ማዕካ፡ሸቤርንና፡ቲርሐናን፡ወለደች።
49ደግሞም፡የመድማናን፡አባት፡ሸዓፍንና፡የመክቢናንና፡የጊብዓን፡አባት፡ሱሳን፡ወለደች፤የካሌብም፡ሴት፡ ልጅ፡ዓክሳ፡ነበረች።
50የካሌብ፡ልጆች፡እነዚህ፡ናቸው፤የኤፍራታ፡የበኵሩ፡የሆር፡ልጅ፡የቂርያትይዓሪም፡አባት፡ሦባል፥
51የቤተ፡ልሔም፡አባት፡ሰልሞን፥የቤት፡ጋዴር፡አባት፡ሐሬፍ።
52ለቂርያትይዓሪምም፡አባት፡ለሦባል፡ልጆች፡ነበሩት፤ሀሮኤ፡የመናሕታውያን፡እኩሌታ።
53የቂርያትይዓሪምም፡ወገኖች፤ይትራውያን፥ፉታውያን፥ሹማታውያን፥ሚሽራውያን፤ከነዚህም፡ጾርዓውያንና፡ ኤሽታኦላውያን፡ወጡ።
54የሰልሞንም፡ልጆች፡ቤተ፡ልሔም፥ነጦፋውያን፥ዓጣሮትቤትዮአብ፥የመናሕታውያን፡እኩሌታ፥ጾርዓውያን፡ ነበሩ።
55በያቤጽም፡የተቀመጡ፡የጸሓፊዎች፡ወገኖች፤ቲርዓውያን፥ሺምዓታውያን፥ሡካታውያን፡ነበሩ፤እነዚህ፡ ከሬካብ፡ቤት፡አባት፡ከሐማት፡የወጡ፡ቄናውያን፡ናቸው።