1በኬብሮንም፡ለዳዊት፡የተወለዱለት፡ልጆች፡እነዚህ፡ናቸው።በኵሩ፡አምኖን፡ከኢይዝራኤላዊቱ፡ ከአኪናሖም፥ኹለተኛውም፡ዳንኤል ፡ከቀርሜሎሳዊቱ፡ከአቢግያ፥
2ሦስተኛው፡አቤሴሎም፡ከጌሹር፡ንጉሥ፡ከተልማይ፡ልጅ፡ከመዓካ፥አራተኛው፡አዶንያስ፡ከአጊት፥
3ዐምስተኛው፡ሰፋጥያስ፡ከአቢጣል፥ስድስተኛው፡ይትረኃም፡ከሚስቱ፡ከዔግላ።
4ስድስቱ፡በኬብሮን፡ተወለዱለት፤በዚያም፡ሰባት፡ዓመት፡ከስድስት፡ወር፡ነገሠ፤በኢየሩሳሌምም፡ሠላሳ፡ ሦስት፡ዓመት፡ነገሠ።
5እነዚህ፡ደግሞ፡በኢየሩሳሌም፡ተወለዱለት፤ከዓሚኤል፡ልጅ፡ከቤርሳቤሕ፥ሳሙስ፥ሶባብ፥ናታን፥
6ሰሎሞን፥አራት፤ኢያቤሐር፥ኤሊሱዔ፥
7ኤሊፋላት፥ኖጋ፥ናፌቅ፥ያፍያ፥
8ኤሊሳማ፥ኤሊዳሄ፥ኤሊፋላት፥ዘጠኝ።
9እነዚህ፡ዅሉ፡ከቁባቶች፡ልጆች፡በቀር፡የዳዊት፡ልጆች፡ነበሩ፤ትዕማርም፡እኅታቸው፡ነበረች።
10የሰሎሞንም፡ልጅ፡ሮብዓም፡ነበረ፤ልጁ፡አቢያ፥
11ልጁ፡አሣ፥ልጁ፡ኢዮሳፍጥ፥ልጁ፡ኢዮራም፥ልጁ፡አካዝያስ፥ልጁ፡ኢዮአስ፥
12ልጁ፡አሜስያስ፥ልጁ፡ዐዛርያስ፥ልጁ፡ኢዮአታም፥
13ልጁ፡አካዝ፥ልጁ፡ሕዝቅያስ፥ልጁ፡ምናሴ፥
14ልጁ፡ዓሞጽ፥ልጁ፡ኢዮስያስ።
15የኢዮስያስም፡ልጆች፤በኵሩ፡ዮሐናን፥ኹለተኛውም፡ኢዮአቄም፥ሦስተኛውም፡ሴዴቅያስ፥አራተኛውም፡ ሰሎም።
16የኢዮአቄምም፡ልጆች፤ልጁ፡ኢኮንያን፥ልጁ፡ሴዴቅያስ።
17የምርኮኛውም፡የኢኮንያን፡ልጆች፡ሰላትያል፥መልኪራም፥
18ፈዳያ፥ሼናጻር፥ይቃምያ፥ሆሻማ፥ነዳብያ፡ነበሩ።
19የፈዳያ፡ልጆች፡ዘሩባቤልና፡ሰሜኢ፡ነበሩ፤የዘሩባቤልም፡ልጆች፤ሜሱላም፥ሐናንያ፥እኅታቸውም፡ ሰሎሚት።
20ሐሹባ ፥ኦሄል ፥በራክያ ፥ሐሳድያ፥ዮሻብሒሴድ፡ዐምስት፡ናቸው።
21የሐናንያም፡ልጆች፡ፈላጥያና፡የሻያ፡ነበሩ።የረፋያ፡ልጆች፥የአርናን፡ልጆች፥የዐብድዩ፡ ልጆች፥የሴኬንያ፡ልጆች።
22የሴኬንያም፡ልጅ፡ሸማያ፡ነበረ።የሸማያም፡ልጆች፡ሐጡስ፥ይግአል፥ባርያሕ፥ነዓርያ፥ሻፋጥ፡ስድስት፡ ነበሩ።
23የነዓርያም፡ልጆች፡ኤልዮዔናይ፥ሕዝቅያስ፥ዐዝሪቃም፡ሦስት፡ነበሩ።
24የኤልዮዔናይም፡ልጆች፡ሆዳይዋ፥ኤልያሴብ፥ፌልያ፥ዐቁብ ፥ዮሐናን፥ደላያ፥ዓናኒ፡ሰባት፡ነበሩ። 187 ዕብ.፥ዳኒኤል፡(ደያኔ፡እግዚእ፥የእግዚአብሔር፡ዳኛ)። 188 ዕብ.፥ሐሹባ፡(ዕሰባ፥ዕስባት)። 189 ዕብ.፥ኦሄል፡(ድንኳን)። 190 ዕብ.፥በራክያህ፡(ብርከ፡እግዚእ•የጌታ፡ጕልበት)። 191 ዕብ.፥ዐቁብ፡(ዐቃቢ•ከልካይ፥ጠባቂ)። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org