1የይሁዳ፡ልጆች፡ፋሬስ፥ኤስሮም፥ከርሚ፥ሆር፥ሦባል፡ናቸው።
2የሦባልም፡ልጅ፡ራያ፡ኢኤትን፡ወለደ፤ኢኤትም፡አሑማይንና፡ላሃድን፡ወለደ።እነዚህ፡የጾርዓውያን፡ ወገኖች፡ናቸው።
3እነዚህም፡የኤጣም፡አባት፡ልጆች፡ናቸው፤ኢይዝራኤል፥ይሽማ፥ይድባሽ፥እኅታቸውም፡ሃጽሌልፎኒ።
4የጌዶርም፡አባት፡ፋኑኤል ፥የሑሻም፡አባት፡ኤጽር፤እነዚህ፡የቤተ፡ልሔም፡አባት፡የኤፍራታ፡የበኵሩ፡ የሆር፡ልጆች፡ናቸው።
5ለቴቁሔም፡አባት፡ለአሽሑር፡ሔላና፡ነዕራ፡የተባሉ፡ኹለት፡ሚስቶች፡ነበሩት።
6ነዕራም፡አሑዛምን፥ኦፌርን፥ቴምኒን፥አሐሽታሪን፡ወለደችለት።እነዚህ፡የነዕራ፡ልጆች፡ናቸው።
7የሔላም፡ልጆች፡ዴሬት፥ይጽሐር፥ኤትናን፡ናቸው።
8ቆጽ፡ዓኑብን፥ጾቤባን፥የሃሩምንም፡ልጅ፡የአሐርሔልን፡ወገኖች፡ወለደ።
9ያቤጽም፡ከወንድሞቹ፡ይልቅ፡የተከበረ፡ነበረ፤እናቱም፦በጣር፡ወልጄዋለኹና፡ብላ፡ስሙን፦ያቤጽ፡ ብላ፡ጠራችው።
10ያቤጽም፦እባክኽ፥መባረክን፡ባርከኝ፥አገሬንም፡አስፋው፤እጅኽም፡ከእኔ፡ጋራ፡ ትኹን፤እንዳያሳዝነኝም፡ከክፋት፡ጠብቀኝ፡ብሎ፡የእስራኤልን፡አምላክ፡ጠራ፤እግዚአብሔርም፡የለመነውን፡ ሰጠው።
11የሹሐም፡ወንድም፡ክሉብ፡የኤሽቶንን፡አባት፡ምሒርን፡ወለደ።
12ኤሽቶንም፡ቤትራ፡ፋንና፡ፋሴሐን፡የዒርናሐሽንም፡አባት፡ተሒናን፡ወለደ፤እነዚህ፡የሬካ፡ሰዎች፡ናቸው።
13የቄኔዝም፡ልጆች፡ጎቶንያልና፡ሰራያ፡ነበሩ።የጎቶንያልም፡ልጅ፡ሐታት፡ነበረ።
14መዖኖታይ፡ዖፍራን፡ወለደ።ሰራያም፡የጌሃራሽምን፡አባት፡ኢዮአብን፡ወለደ፤እነርሱም፡ጠራቢዎች፡ነበሩ።
15የዮፎኒም፡ልጅ፡የካሌብ፡ልጆች፡ዒሩ፥ኤላ፥ነዓም፡ነበሩ።
16የዔላም፡ልጅ፡ቄኔዝ፡ነበረ።የይሃሌልኤል፡ልጆች፡ዚፍ፥ዚፋ፥ቲርያ፥አሳርኤል፡ነበሩ።
17የዕዝራም፡ልጆች፡ዬቴር፥ሜሬድ፥ዔፌር፥ያሎን፡ነበሩ፤ዬቴርም፡ማርያምን፥ሸማይን፥የኤሽትምዓን፡ አባት፡ይሽባን፡ወለደ።
18አይሁዳዊቱም፡ሚስቱ፡የጌዶርን፡አባት፡ዬሬድን፥የሦኮንም፡አባት፡ሔቤርን፥የዛኖዋንም፡አባት፡ ይቁቲኤልን፡ወለደች።እነዚህም፡ሜሬድ፡ያገባት፡የፈርዖን፡ልጅ፡የቢትያ፡ልጆች፡ናቸው።
19የሆዲያ ፡ሚስት፡የነሐም፡እኅት፡ልጆች፡የገርሚው፡የቅዒላ፡አባትና፡ማዕካታዊው፡ኤሽትሞዐ፡ነበሩ።
20የሺሞንም፡ልጆች፡አምኖን፥ሪና፥ቤንሐናን፥ቲሎን፡ነበሩ።የይሽዒም፡ልጆች፡ዞሔትና፡ቢንዞሔት፡ነበሩ።
21የይሁዳም፡ልጅ፡የሴሎም፡ልጆች፡የሌካ፡አባት፡ዔር፥የመሪሳ፡አባት፡ለዓዳ፥ከአሽቤዓ፡ቤት፡የሚኾኑ፡ ጥሩ፡በፍታ፡የሚሠሩ፡ወገኖች፥
22ዮቂም፥የኮዜባ፡ሰዎች፥ኢዮአስ፥ሞዐብን፡የገዛ፡ሳራፍ ፥ያሹቢሌሔም፡ነበሩ።
23ይህ፡ዝና፡ከቀድሞ፡ዠምሮ፡ነበረ።እነዚህ፡በነጣዒምና፡በጋዴራ፡የሚቀመጡ፡ሸክላ፡ሠራተኛዎች፡ ነበሩ።በዚያ፡በንጉሡ፡ዘንድ፡ስለ፡ሥራው፡ይቀመጡ፡ነበር። 192 ዕብ.፥ፍኑኤል፡(ገጸ፡አምላክ)። 193 ዕብ.፥ሆዲያህ፡(ይሁዲት)። 194 ዕብ.፥ሳራፍ፡(ሰራፊ•ዐጣኝ፥አንዳጅ)። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
24የስምዖንም፡ልጆች፤ነሙኤል፥ያሚን፥ያሪን፥ዛራ፥ሳኡል፤
25ልጁ፡ሰሎም፥ልጁ፡መብሳም፥ልጁ፡ማስማዕ።
26የማስማዕም፡ልጆች፤ልጁ፡ሐሙኤል ፥ልጁ፡ዘኩር፥ልጁ፡ሰሜኢ።
27ለሰሜኢም፡ዐሥራ፡ስድስት፡ወንዶችና፡ስድስት፡ሴቶች፡ልጆች፡ነበሩት፤ለወንድሞቹ፡ግን፡ብዙ፡ልጆች፡ አልነበሯቸውም፥ወገናቸውም፡ዅሉ፡እንደ፡ይሁዳ፡ልጆች፡አልተባዙም።
28በቤርሳቤሕም፥በሞላዳ፥
29በሐጸርሹዓል፥በቢልሃ፥በዔጼም፥
30በቶላድ፥በቤቱኤል፥በሔርማ፥በጺቅላግ፥
31በቤትማርካቦት፥በሐጸርሱሲም፥በቤትቢሪ፥በሸዓራይም፡ይቀመጡ፡ነበር።እስከዳዊትም፡መንግሥት፡ድረስ፡ ከተማዎቻቸው፡እነዚህ፡ነበሩ።
32መንደሮቻቸውም፡ኤጣም፥ዐይን፥ሬሞን፥ቶኬን፥ዐሻን፥ዐምስቱ፡ከተማዎች፤
33እስከ፡በዓልም፡ድረስ፡በእነዚህ፡ከተማዎች፡ዙሪያ፡የነበሩ፡መንደሮቻቸው፡ዅሉ፡ነበሩ።መቀመጫቸውና፡ የትውልዳቸው፡መዝገቦች፡እነዚህ፡ናቸው።
34ምሾባብ፥የምሌክ፥የአሜስያስ፡ልጅ፡ኢዮስያ፥
35ኢዮኤል፥የዮሺብያ፡ልጅ፥የሰራያ፡ልጅ፡የዓሢኤል፡ልጅ፡ኢዩ፥
36ኤልዮዔናይ፥ያዕቆባ፥የሾሐያ፥ዐሳያ፥ዓዲዔል፥ዩሲምኤል፥በናያስ፥
37የሺፊ፡ልጅ፡ዚዛ፥የአሎን፡ልጅ፡የይዳያ፡ልጅ፡የሺምሪ፡ልጅ፡የሸማያ፡ልጅ፤
38እነዚህ፡በስማቸው፡የተጠሩ፡በወገኖቻቸው፡ላይ፡አለቃዎች፡ነበሩ፤የአባቶቻቸውም፡ቤቶች፡በዝተው፡ ነበር።
39ለመንጋዎቻቸው፡መሰምሪያ፡ይሹ፡ዘንድ፡ወደጌዶር፡መግቢያ፡እስከ፡ሸለቆው፡ምሥራቅ፡ድረስ፡ኼዱ።
40የለመለመችም፡እጅግም፡ያማረች፡መሰምሪያ፡አገኙ፤ምድሪቱም፡ሰፊና፡ጸጥተኛ፡ሰላም፡ያላትም፡ ነበረች፤በቀድሞም፡ጊዜ፡በዚያ፡ተቀምጠው፡የነበሩ፡ከካም፡ወገን፡ነበሩ።
41እነዚህም፡በስማቸው፡የተጻፉ፡በይሁዳ፡ንጉሥ፡በሕዝቅያስ፡ዘመን፡መጥተው፡ድንኳኖቻቸውንና፡በዚያ፡ የተገኙትን፡ምዑናውያንን፡መቱ፥እስከ፡ዛሬም፡ድረስ፡ፈጽመው፡አጠፏቸው፤በዚያም፡ለመንጋዎቻቸው፡ መሰምሪያ፡ነበረና፡በስፍራቸው፡ተቀመጡ።
42የስምዖንም፡ልጆች፡ዐምስት፡መቶ፡ሰዎች፡ወደሴይር፡ተራራ፡ኼዱ፤አለቃዎቻቸውም፡የይሽዒ፡ ልጆች፥ፈላጥያ፥ነዓርያ፥ረፋያ፥ዑዝኤል፡ነበሩ።
43ያመለጡትንም፡የዐማሌቃውያንን፡ቅሬታ፡መቱ፥በዚያም፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡ተቀምጠዋል።