Skip to content
← 1 Chronicles

Chapter 5 · Amharic

1 Chronicles

1የእስራኤልም፡በኵር፡የሮቤል፡ልጆች፡እነዚህ፡ናቸው።ርሱ፡የበኵር፡ልጅ፡ነበረ፤ነገር፡ግን፥የአባቱን፡ ምንጣፍ፡ስላረከሰ፡ብኵርናው፡ለእስራኤል፡ልጅ፡ለዮሴፍ፡ልጆች፡ተሰጠ፤ትውልዱ፡ግን፡ከብኵርና፡ጋራ፡ አልተቈጠረም።

2ይሁዳም፡በወንድሞቹ፡መካከል፡በረታ፥አለቃም፡ከርሱ፡ኾነ፤ብኵርናው፡ግን፡ለዮሴፍ፡ነበረ።

3የእስራኤል፡በኵር፡የሮቤል፡ልጆች፤ሄኖኅ፥ፈሉስ፥አስሮን፥ከርሚ፡ነበሩ። 195 ዕብ.፥ሐሙኤል፡(ሕማመ፡ኤል•የእግዚአብሔር፡ቍጣ፣ሙቀት)። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

4የኢዮኤል፡ልጆች፤ልጁ፡ሸማያ፥

5ልጁ፡ጎግ፥ልጁ፡ሰሜኢ፥ልጁ፡ሚካ፥

6ልጁ፡ራያ፥ልጁ፡ቢኤል፥የአሶር፡ንጉሥ፡ቴልጌልቴልፌልሶር፡የማረከው፡ልጁ፡ብኤራ፤ርሱ፡የሮቤል፡ ነገድ፡አለቃ፡ነበረ።

7ወንድሞቹ፡በየወገናቸው፡የትውልዶቻቸው፡መዝገብ፡በተቈጠረ፡ጊዜ፤አንደኛው፡ኢዮኤል፥

8ዘካርያስ፥እስከ፡ናባውና፡እስከ፡በዓልሜዎን፡ድረስ፡በዐሮዔር፡የተቀመጠው፡የኢዮኤል፡ልጅ፡የሽማዕ፡ ልጅ፡የዖዛዝ፡ልጅ፡ቤላ፤

9በገለዓድ፡ምድር፡እንስሳዎቻቸው፡በዝተው፡ነበርና፥በምሥራቅ፡በኩል፡ከኤፍራጥስ፡ወንዝ፡ዠምሮ፡ እስከምድረ፡በዳው፡መግቢያ፡ድረስ፡ተቀመጠ።

10በሳኦልም፡ዘመን፡ከአጋራውያን፡ጋራ፡ተዋጉ፥እነርሱም፡በእጃቸው፡ተመትተው፡ወደቁ፤በገለዓድ፡ ምሥራቅ፡በኩል፡ባለው፡አገር፡ዅሉ፡በድንኳኖቻቸው፡ተቀመጡ።

11የጋድም፡ልጆች፡በባሳን፡ምድር፡እስከ፡ሰልካ፡ድረስ፡በአፋዛዣቸው፡ተቀመጡ።

12አንደኛው፡ኢዮኤል፥ኹለተኛው፡ሳፋም፥ያናይ፥ሳፋጥ፡በበሳን፡ተቀመጡ።

13የአባቶቻቸውም፡ቤቶች፡ወንድሞች፡ሚካኤል፥ሜሱላም፥ሳባ፥ዮራይ፥ያካን፥ዙኤ፥ኦቤድ፡ሰባት፡ነበሩ።

14እነዚህም፡የቡዝ፡ልጅ፡የዬዳይ፡ልጅ፡የኢዬሳይ፡ልጅ፡የሚካኤል፡ልጅ፡የገለዓድ፡ልጅ፡የኢዳይ፡ልጅ፡ የዑሪ ፡ልጅ፡የአቢካኢል፡ልጆች፡ነበሩ።

15የአባቶቻቸውም፡ቤቶች፡አለቃ፡የጉኒ፡ልጅ፡የዐብዲኤል ፡ልጅ፡ወንድም፡ነበረ።

16በገለዓድም፡ምድር፡በባሳን፡በመንደሮቹም፡በሳሮንም፡መሰምሪያዎች፡ዅሉ፡እስከ፡ዳርቻቸው፡ድረስ፡ ተቀምጠው፡ነበር።

17እነዚህ፡ዅሉ፡በትውልዶቻቸው፡በይሁዳ፡ንጉሥ፡በኢዮአታም፡ዘመንና፡በእስራኤል፡ንጉሥ፡በኢዮርብዓም፡ ዘመን፡ተቈጠሩ።

18የሮቤልና፡የጋድ፡ልጆች፡የምናሴም፡ነገድ፡እኩሌታ፥ጽኑዓን፥ጋሻና፡ሰይፍ፡ የሚይዙ፥ቀስተኛዎችም፥ሰልፍ፡የሚያውቁ፡ሰልፈኛዎችም፥አርባ፡አራት፡ሺሕ፡ሰባት፡መቶ፡ስድሳ፡ነበሩ።

19ከአጋራውያንና፡ከኢጡር፡ከናፌስና፡ከናዳብ፡ጋራ፡ተዋጉ።

20በሚዋጉበትም፡ጊዜ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ጮኸዋልና፥በርሱም፡ታምነዋልና፥ተለመናቸው፤በላያቸውም፡ ረዳት፡ኾናቸው፥አጋራውያንና፡ከነርሱ፡ጋራ፡የነበሩትም፡ዅሉ፡በእጃቸው፡ተሰጡ።

21ከከብቶቻቸውም፡ዐምሳ፡ሺሕ፡ግመሎች፥ኹለት፡መቶ፡ዐምሳ፡ሺሕም፡በጎች፥ኹለት፡ሺሕም፡ አህያዎች፥ከሰዎችም፡መቶ፡ሺሕ፡ማረኩ።

22ሰልፉ፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ነበረና፡ብዙ፡ሰዎች፡ተገድለው፡ወደቁ፤እስከ፡ምርኮም፡ዘመን፡ድረስ፡ በስፍራቸው፡ተቀመጡ።

23የምናሴ፡የነገድ፡እኩሌታ፡ልጆች፡በምድሪቱ፡ተቀመጡ።ከባሳንም፡ዠምሮ፡እስከ፡በዓልአርሞንዔምና፡ እስከ፡ሳኔር፡እስከአርሞንዔም፡ተራራ፡ድረስ፡በዙ።

24የአባቶቻቸውም፡ቤቶች፡አለቃዎች፡እነዚህ፡ ነበሩ፤ዔፌር፥ይሽዒ፥ኤሊኤል፥ዓዝርኤል፥ኤርምያ፥ሆዳይዋ፥ኢየድኤል፤እነርሱ፡ጽኑዓን፡ኀያላን፡የታወቁ፡ ሰዎች፡የአባቶቻቸውም፡ቤቶች፡አለቃዎች፡ነበሩ። 196 ዕብ.፥ሑሪይ። 197 ዕብ.፥ዐብዲኤል፡(ዐብደ፡እግዚእ፥የጌታ፡አገልጋይ)። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

25የአባቶቻቸውንም፡አምላክ፡በደሉ፥እግዚአብሔርም፡ከፊታቸው፡ባጠፋቸው፡በምድሩ፡አሕዛብ፡አማልክት፡ አመነዘሩ።

26የእስራኤልም፡አምላክ፡የአሶርን፡ንጉሥ፡የፎሐን፡መንፈስ፥የአሶርንም፡ንጉሥ፡የቴልጌልቴልፌልሶርን፡ መንፈስ፡አስነሣ፤የሮቤልንና፡የጋድን፡ልጆች፡የምናሴንም፡ነገድ፡እኩሌታ፡አፈለሰ፥እስከ፡ዛሬም፡ወዳሉበት፡ ወደ፡አላሔና፡ወደ፡ኦቦር፥ወደ፡ሃራና፡ወደጎዛን፡ወንዝ፡አመጣቸው።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source