Skip to content
← 1 Chronicles

Chapter 6 · Amharic

1 Chronicles

1የሌዊ፡ልጆች፤ጌድሶን፥ቀአት፥ሜራሪ።

2የቀአትም፡ልጆች፤ዕምበረም፥ይስዓር፥ኬብሮን፥ዑዝኤል።

3የዕምበረምም፡ልጆች፤አሮን፥ሙሴ፥ማርያም።የአሮን፡ልጆች፤ናዳብ፥አብዮድ፥አልዓዛር፥ኢታምር።

4አልዓዛር፡ፊንሐስን፡ወለደ፤ፊንሐስ፡አቢሱ ን፡ወለደ፤

5አቢሱም፡ቡቂን፡ወለደ፤ቡቂም፡ዖዚ ን፡ወለደ፤

6ዖዚም፡ዘራእያን፡ወለደ፤ዘራእያም፡መራዮትን፡ወለደ፤

7መራዮት፡አማርያን፡ወለደ፤

8አማርያም፡አኪጦብን፡ወለደ፤አኪጦብም፡ሳዶቅን፡ወለደ፤ሳዶቅም፡አኪማዐስን፡ወለደ፤

9አኪማዐስም፡ዐዛርያስን፡ወለደ፤

10ዐዛርያስም፡ዮሐናንን፡ወለደ፤ዮሐናንም፡ዐዛርያስን፡ወለደ፤ርሱም፡ሰሎሞን፡በኢየሩሳሌም፡በሠራው፡ቤት፡ ካህን፡ነበረ፤

11ዐዛርያስም፡አማርያን፡ወለደ፤አማርያም፡አኪጦብን፡ወለደ፤

12አኪጦብም፡ሳዶቅን፡ወለደ፤ሳዶቅም፡ሰሎምን፡ወለደ፤

13ሰሎምም፡ኬልቅያስን፡ወለደ፤ኬልቅያስም፡ዐዛርያስን፡ወለደ፤

14ዐዛርያስም፡ሰራያን፡ወለደ፤ሰራያም፡ኢዮሴዴቅን ፡ወለደ፤

15እግዚአብሔርም፡ይሁዳንና፡ኢየሩሳሌምን፡በናቡከደነጾር፡እጅ፡ባስማረከ፡ጊዜ፡ኢዮሴዴቅ፡ተማርኮ፡ኼደ።

16የሌዊ፡ልጆች፤ጌድሶን፥ቀአት፥ሜራሪ።

17የጌድሶንም፡ልጆች፡ስም፡ይህ፡ነው፤ሎቤኒ፡ሰሜኢ።

18የቀአትም፡ልጆች፤ዕምበረም፥ይስዓር፥ኬብሮን፥ዑዝኤል፡ነበሩ።

19የሜራሪ፡ልጆች፤ሞሖሊም፥ሙሲ።የሌዋውያን፡ወገኖች፡በያባቶቻቸው፡ቤቶች፡እነዚህ፡ናቸው።

20ከጌድሶን፤ልጁ፡ሎቤኒ፥ልጁ፡ኢኤት፥ልጁ፡ዛማት፥

21ልጁ፡ዮአክ፥ልጁ፡አዶ፥ልጁ፡ዛራ፥ልጁ፡ያትራይ።

22የቀአት፡ልጆች፤ልጁ፡ዐሚናዳብ፥ልጁ፡ቆሬ፥ልጁ፡አሴር፥

23ልጁ፡ሕልቃና፥ልጁ፡አቢሣፍ ፥ልጁ፡አሴር፥ 198 ዕብ.፥አቢይሹዐ። 199 ዕብ.፥ዖዚ፡(ዕዙዝ•ብርቱ፥ጠንካራ)። 200ዕብ.፥የሆ፡ጻዳቅ፡(አምላክ፡ያጸደቀው)። 201 ዕብ.፥ኤቢያሣፍ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

24ልጁ፡ኢኢት፥ልጁ፡ኡሩኤል፥ልጁ፡ዖዝያ፥ልጁ፡ሳውል።

25የሕልቃና ም፡ልጆች፤ዐማሲ፥አኪሞት ።

26የሕልቃናም፡ልጆች፤ልጁ፡ሱፊ፥

27ልጁ፡ናሐት፥ልጁ፡ኤልያብ፥ልጁ፡ይሮሐም፥ልጁ፡ሕልቃና።

28የሳሙኤልም፡ልጆች፤በኵሩ፡ኢዮኤል፥ኹለተኛውም፡አብያ።

29የሜራሪ፡ልጆች፤ሞሖሊ፥ልጁ፡ሎቤኒ፥ልጁ፡ሰሜኢ፥

30ልጁ፡ዖዛ፥ልጁ፡ሳምዓ፥ልጁ፡ሐግያ፥ልጁ፡ዐሳያ።

31ዳዊትም፡ታቦቱ፡ዐርፎ፡ከተቀመጠ፡በዃላ፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡ያቆማቸው፡የመዘምራን፡አለቃዎች፡ እነዚህ፡ናቸው።

32ሰሎሞንም፡የእግዚአብሔርን፡ቤት፡በኢየሩሳሌም፡እስኪሠራ፡ድረስ፡በመገናኛ፡ድንኳን፡ማደሪያ፡ፊት፡ እያዜሙ፡ያገለግሉ፡ነበር፤በየተራቸውም፡ያገለግሉ፡ነበር።

33አገልጋዮቹና፡ልጆቹ፡እነዚህ፡ናቸው፤ከቀአት፡ልጆች፡ዘማሪው፡ኤማን ፡ነበረ፤ርሱም፡የኢዮኤል፡ ልጅ፥

34የሳሙኤል፡ልጅ፥የሕልቃና፡ልጅ፥የይሮሐም፡ልጅ፥የኤሊኤል፡ልጅ፥የቶዋ፡ልጅ፥

35የሱፍ፡ልጅ፥የሕልቃና፡ልጅ፥የመሐት፡ልጅ፥

36የዐማሲ፡ልጅ፥የሕልቃና፡ልጅ፥የኢዮኤል፡ልጅ፥የዐዛርያስ፡ልጅ፥የሶፎንያስ፡ልጅ፥

37የታሐት፡ልጅ፥የአሴር፡ልጅ፥

38የአብያሣፍ፡ልጅ፥የቆሬ፡ልጅ፥የይስዓር፡ልጅ፥የቀአት፡ልጅ፥የሌዊ፡ልጅ፥የእስራኤል፡ልጅ፡ነው።

39በቀኙም፡የቆመ፡ወንድሙ፡አሣፍ፡ነበረ፤አሣፍም፡የበራክያ፡ልጅ፥

40የሳምዓ፡ልጅ፥የሚካኤል፡ልጅ፥የበዓሤያ፡ልጅ፥

41የመልክያ፡ልጅ፥የኤትኒ፡ልጅ፥የዛራ፡ልጅ፥

42የዓዳያ፡ልጅ፥የኤታን፡ልጅ፥የዛማት፡ልጅ፥

43የሰሜኢ፡ልጅ፥የኢኤት፡ልጅ፥የጌድሶን፡ልጅ፥የሌዊ፡ልጅ፡ነው።

44በግራቸውም፡በኩል፡ወንድሞቻቸው፡የሜራሪ፡ልጆች፡ነበሩ፤ኤታን፡የቂሳ፡ልጅ፥የዐብዲ ፡ልጅ፥

45የማሎክ፡ልጅ፥የሐሸብያ፡ልጅ፥የአሜስያስ፡ልጅ፥

46የኬልቅያስ፡ልጅ፥የአማሲ፡ልጅ፥

47የባኒ፡ልጅ፥የሴሜር፡ልጅ፥የሞሖሊ፡ልጅ፥የሙሲ፡ልጅ፥የሜራሪ፡ልጅ፥የሌዊ፡ልጅ።

48ወንድሞቻቸውም፡ሌዋውያን፡ለእግዚአብሔር፡ቤት፡ማደሪያ፡አገልግሎት፡ዅሉ፡ተሰጡ።

49አሮንና፡ልጆቹ፡ግን፡የእግዚአብሔር፡ባሪያ፡ሙሴ፡እንዳዘዘው፡ዅሉ፡ለቅድስተ፡ቅዱሳን፡ሥራ፡ዅሉ፡ ስለ፡እስራኤልም፡ያስተሰርይ፡ዘንድ፡ለሚቃጠለው፡መሥዋዕት፡በሚኾነው፡መሠዊያ፡ላይ፡ይሠዉ፡ ነበር፥በዕጣኑም፡መሠዊያ፡ላይ፡ያጥኑ፡ነበር።

50የአሮንም፡ልጆች፡እነዚህ፡ናቸው፤ልጁ፡አልዓዛር፥ 202 ዕብ.፥እልቃናህ፡(ቀንአ፡እግዚአብሔር፥እግዚአብሔር፡ቀና)። 203 ዕብ.፥አኂሞት፡(እኅወ፡ሞት፥የሞት፡ወንድም)። 204 ሱር.፥ሃይሜን፡(ሃይማኒ•አማኝ)። 205ዕብ.፥ዐብዲይ፥(ዐብድ፥አገልጋይ)። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

51ልጁ፡ፊንሐስ፥ልጁ፡አቢሱ፥ልጁ፡ቡቂ፥

52ልጁ፡ዖዚ፥ልጁ፡ዘራእያ፥ልጁ፡መራዮት፥

53ልጁ፡አማርያ፥ልጁ፡አኪጦብ፥ልጁ፡ሳዶቅ፥ልጁ፡አኪማዐስ።

54ማደሪያዎቻቸውም፡በየሰፈራቸው፡በየዳርቻቸው፡እነዚህ፡ናቸው፤ለአሮን፡ልጆች፡ለቀአት፡ወገኖች፡ አንደኛው፡ዕጣ፡ነበረ።

55ለእነርሱ፡በይሁዳ፡አገር፡ያለችውን፡ኬብሮንን፥በርሷም፡ዙሪያ፡የነበረውን፡መሰምሪያ፡ሰጡ፤

56የከተማዪቱን፡ዕርሻ፡ግን፡መንደሮቿንም፡ለዮፎኒ፡ልጅ፡ለካሌብ፡ሰጡ።

57ለአሮንም፡ልጆች፡የመማፀኛውን፡ከተማዎች፥ኬብሮንን፥ልብናንና፡መሰምሪያዋን፥ደግሞ፡የቲርን፥

58ኤሽትሞዐንና፡መሰምሪያዋን፥ሖሎንንና፡መሰምሪያዋን፥ዳቤርንና፡መሰምሪያዋን፥

59ዓሳንንና፡መሰምሪያዋን፥ቤትሳሚስንና፡መሰምሪያዋን፤

60ከብንያምም፡ነገድ፡ጌባንና፡መሰምሪያዋን፥ጋሌማትንና፡መሰምሪያዋን፥ዐናቶትንና፡መሰምሪያዋን፡ ሰጡ።ከተማዎቻተው፡ዅሉ፡በየወገናቸው፡ዐሥራ፡ሦስት፡ነበሩ።

61ለቀሩትም፡ለቀአት፡ልጆች፡ከነገዱ፡ወገን፡ከምናሴ፡ነገድ፡እኩሌታ፡ዐሥር፡ከተማዎች፡በዕጣ፡ተሰጡ።

62ለጌድሶንም፡ልጆች፡በየወገናቸው፡ከይሳኮር፡ነገድ፥ከአሴርም፡ነገድ፥ከንፍታሌምም፡ነገድ፥በባሳንም፡ ካለው፡ከምናሴ፡ነገድ፥ዐሥራ፡ሦስት፡ከተማዎች፡ተሰጡ።

63ለሜራሪ፡ልጆች፡በየወገናቸው፡ከሮቤል፡ነገድ፥ከጋድም፡ነገድ፥ከዛብሎንም፡ነገድ፥ዐሥራ፡ኹለት፡ ከተማዎች፡በዕጣ፡ተሰጡ።

64የእስራኤልም፡ልጆች፡ለሌዋውያን፡ከተማዎችን፡ከመሰምሪያዎቻቸው፡ጋራ፡ሰጡ።

65ከይሁዳም፡ልጆች፡ነገድ፥ከስምዖንም፡ልጆች፡ነገድ፥ከብንያምም፡ልጆች፡ነገድ፥እነዚህን፡በስማቸው፡ የተጠሩትን፡ከተማዎች፡በዕጣ፡ሰጡ።

66ከቀአትም፡ልጆች፡ወገኖች፡ለአንዳንዶቹ፡ከኤፍሬም፡ነገድ፡ከተማዎች፡ድርሻ፡ነበራቸው።

67በተራራማው፡በኤፍሬም፡አገር፡ያሉትን፡የመማፀኛውን፡ከተማዎች፡ሴኬምንና፡መሰምሪያዋን፥ደግሞም፡ ጌዝርንና፡መሰምሪያዋን፥ዮቅምዓምንና፡መሰምሪያዋን፥

68ቤትሖሮንንና፡መሰምሪያዋን፥

69ኤሎንንና፡መሰምሪያዋን፥ጋትሪሞንንና፡መሰምሪያዋን፡ሰጧቸው።

70ከምናሴም፡ነገድ፡እኩሌታ፡ዐኔርንና፡መሰምሪያዋን፥ቢልዓምንና፡መሰምሪያዋን፡ከቀአት፡ልጆች፡ወገን፡ ለቀሩት፡ሰጡ።

71ለጌድሶን፡ልጆች፡ከምናሴ፡ነገድ፡እኩሌታ፡ወገን፡በባሳን፡ያለችው፡ጎላንና፡መሰምሪያዋ፥ዐስታሮትና፡ መሰምሪያዋ፤

72ከይሳኮርም፡ነገድ፡ቃዴስና፡መሰምሪያዋ፥ዳብራትና፡መሰምሪያዋ፥

73ራሞትና፡መሰምሪያዋ፥ዐኔም ና፡መሰምሪያዋ፤

74ከአሴርም፡ነገድ፡መዓሳልና፡መሰምሪያዋ፥ዐብዶንና፡መሰምሪያዋ፥

75ሑቆቅና፡መሰምሪያዋ፥ረአብና፡መሰምሪያዋ፤

76ከንፍታሌምም፡ነገድ፡በገሊላ፡ያለችው፡ቃዴስና፡መሰምሪያዋ፥ሐሞንና፡መሰምሪያዋ፥ቂርያታይምና፡ መሰምሪያዋ፡ተሰጡ። 206ዕብ.፥ዐኔም፡(አዕይንት•ምንጮች)። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

77ከሌዋውያን፡ለቀሩት፡ለሜራሪ፡ልጆች፡ከዛብሎን፡ነገድ፡ሬሞንና፡መሰምሪያዋ፥ታቦርና፡መሰምሪያዋ፤

78ከሮቤልም፡ነገድ፡በኢያሪኮ፡አንጻር፡በዮርዳኖስ፡ማዶ፡በምሥራቅ፡በኩል፡በምድረ፡በዳ፡ያለችው፡ቦሶርና፡ መሰምሪያዋ፥

79ያሳና፡መሰምሪያዋ፥ቅዴሞትና፡መሰምሪያዋ፥ሜፍዓትና፡መሰምሪያዋ፤

80ከጋድም፡ነገድ፡በገለዓድ፡ያለችው፡ሬማትና፡መሰምሪያዋ፥መሃናይምና፡መሰምሪያዋ፥

81ሐሴቦንና፡መሰምሪያዋ፥ኢያዜርና፡መሰምሪያዋ፡ተሰጡ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source