1የይሳኮርም፡ልጆች፥ቶላ፥ፉዋ፥ያሱብ፡ሺምሮን፥አራት፡ናቸው።
2የቶላም፡ልጆች፥ዖዚ፥ራፋያ፥ይሪኤል፥የሕማይ፥ይብሣም፥ሽሙኤል፥የአባታቸው፡የቶላ፡ቤት፡ አለቃዎች፥በትውልዳቸው፡ጽኑዓን፡ኀያላን፡ሰዎች፡ነበሩ፤በዳዊት፡ዘመን፡ቍጥራቸው፡ኻያ፡ኹለት፡ሺሕ፡ ስድስት፡መቶ፡ነበረ።
3የዖዚም፡ልጆች፡ይዝረሕያ፤የይዝረሕያም፡ልጆች፡ሚካኤል፥ዐብድዩ፥ኢዮኤል፥ይሺያ፡ዐምስት፡ ናቸው፤ዅሉም፡አለቃዎች፡ነበሩ።
4ከነርሱም፡ጋራ፡በየትውልዳቸው፡በያባቶቻቸው፡ቤቶች፡ለሰልፍ፡የተዘጋጁ፡የሰራዊት፡ጭፍራዎች፡ ነበሩ፤ብዙም፡ሴቶችና፡ልጆች፡ነበሯቸውና፡ሠላሳ፡ስድስት፡ሺሕ፡ነበሩ።
5ወንድሞቻቸውም፡በይሳኮር፡ወገኖች፡ዅሉ፡ጽኑዓን፡ኀያላን፡ሰዎች፡በትውልዳቸው፡ዅሉ፡የተቈጠሩ፡ ሰማንያ፡ሰባት፡ሺሕ፡ነበሩ።
6የብንያም፡ልጆች፡ቤላ፥ቤኬር፥ይዲኤል ፡ሦስት፡ነበሩ።
7የቤላም፡ልጆች፥ኤሴቦን፥ዖዚ፥ዑዝኤል፥ኢያሪሙት፥ዒሪ፥ዐምስት፡ነበሩ፤የአባቶቻቸው፡ቤቶች፡ አለቃዎች፥ጽኑዓን፡ኀያላን፡ሰዎች፡ነበሩ፤በትውልድ፡የተቈጠሩ፡ኻያ፡ኹለት፡ሺሕ፡ሠላሳ፡አራት፡ነበሩ።
8የቤኬርም፡ ልጆች፤ዝሚራ፥ኢዮአስ፥አልዓዛር፥ኤልዮዔናይ፥ዖምሪ፥ኢያሪሙት፥አብያ፥ዐናቶት፥ዓሌሜት፤እነዚህ፡ ዅሉ፡የቤኬር፡ልጆች፡ነበሩ።
9በየትውልዳቸው፡መዝገብ፡የተቈጠሩ፥የአባቶቻቸው፡ቤቶች፡አለቃዎች፥ጽኑዓን፡ኀያላን፡ሰዎች፡ኻያ፡ ሺሕ፡ኹለት፡መቶ፡ነበሩ።
10የይዲኤልም፡ልጅ፡ቢልሐን፡ነበረ፤የቢልሐንም፡ልጆች፡ የዑስ፥ብንያም፥ኤሑድ ፥ክንዓና ፥ዜታን ፥ተርሴስ ፥አኪሳአር ፡ነበሩ።
11እነዚህ፡ዅሉ፡የይዲኤል፡ልጆች፡ነበሩ፤በያባቶቻቸው፡ቤቶች፡አለቃዎች፥ጭፍራ፡እየኾኑ፡ወደ፡ሰልፍ፡ የሚወጡ፡ጽኑዓን፡ኀያላን፡ሰዎች፡ዐሥራ፡ሰባት፡ሺሕ፡ኹለት፡መቶ፡ነበሩ።
12ደግሞም፡ሳፊን፥ሑፊም፡የዒር፡ልጆች፥ሑሺም፡የአሔር፡ልጆችም፡ነበሩ።
13የንፍታሌም፡ልጆች፥ያሕጽኤል፥ጉኒ፥ዬጽር፥ሺሌም፥የባላ፡ልጆች፡ነበሩ። 207 ዕብ.፥ይድያዕኤል፡(የድዐ፡እግዚአ፥ጌታን፡ዐወቀ / ደዐተ፡እግዚእ፥ጌታን፡ማወቅ)። 208ዕብ.፥ኤሑድ፡(ዋሕድ•አንድያ)። 209ዕብ.፥ክንዓና፡(የ'ከነዓን'፡አንስት፥ነጋዴ)። 210 ዕብ.፥ዘይታን፡(ወይራ)። 211 ዕብ.፥ተርሺሽ፡(ስመ፡ዕንቍ)። 212 ዕብ.፥አኂሸሐር፡(እኅወ፡ጽባሕ፥የንጋት፡ወንድም)። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
14የምናሴ፡ልጆች፡ሶርያዪቱ፡ቁባቱ፡የወለደችለት፡እስርኤልና፡የገለዓድ፡አባት፡ማኪር፡ናቸው።
15ማኪርም፡ከሑፊምና፡ከሳፊን፡ወገን፡ሚስት፡አገባ፤የእኅቷም፡ስም፡መዓካ፡ነበረ፤የኹለተኛውም፡ስም፡ ሰለጰአድ፡ነበረ፤ለሰለጰዓድም፡ሴቶች፡ልጆች፡ነበሩት።
16የማኪርም፡ሚስት፡መዓካ፡ልጅ፡ወለደች፥ስሙንም፡ፋሬስ፡ብላ፡ጠራችው፤የወንድሙም፡ስም፡ሱሮስ፡ ነበረ፤ልጆቹም፡ኡላም፥ራቄም፡ነበሩ።
17የኡላምም፡ልጅ፡ባዳን፡ነበረ፤እነዚህ፡የምናሴ፡ልጅ፡የማኪር፡ልጅ፡የገለዓድ፡ልጆች፡ነበሩ።
18እኅቱ፡መለኬት፡ኢሱድን፥አቢዔዝርን፥መሕላን፡ወለደች።
19የሸሚዳም፡ልጆች፡አኂያን፥ሴኬም፥ሊቅሒ፥አኒዐም፡ነበሩ።
20የኤፍሬም፡ልጆች፤ሹቱላ፥ልጁ፡ባሬድ፥ልጁ፡ታሐት፥ልጁ፡ኤልዓዳ፥ልጁ፡ታሐት፥ልጁ፡ዛባድ፥ልጁ፡ ሽቱላ፥
21የአገሩም፡ተወላጆች፡የጌት፡ሰዎች፡ከብቶቻቸውን፡ሊወስዱ፡ወርደው፡ነበርና፥የገደሏቸው፡ልጆቹ፡ ኤድርና፡ኤልዓድ፡ነበሩ።
22አባታቸውም፡ኤፍሬም፡ብዙ፡ቀን፡አለቀሰ፥ወንድሞቹም፡ሊያጽናኑት፡መጡ።
23ወደ፡ሚስቱም፡ገባ፥አረገዘችም፥ወንድ፡ልጅም፡ወለደች፤በቤቱም፡መከራ፡ኾኗልና፥ስሙ፡በሪዐ ፡ ብሎ፡ጠራው።
24ሴት፡ልጁም፡ታችኛውንና፡ላይኛውን፡ቤትሖሮንንና፡ኡዜንሼራን፡የሠራች፡ሲአራ፡ነበረች።
25ወንዶች፡ልጆቹም፡ፋፌ፥ሬሴፍ፥ልጁ፡ቴላ፥
26ልጁ፡ታሐን፥ልጁ፡ለአዳን፥ልጁ፡ዐሚሁድ፥ልጁ፡ኤሊሳማ፥
27ልጁ፡ነዌ፥ልጁ፡ኢያሱ።
28ግዛታቸውና፡ማደሪያቸው፡ቤቴልና፡መንደሮቿ፥በምሥራቅም፡በኩል፡ነዓራን፥በምዕራብም፡በኩል፡ጌዝርና፡ መንደሮቿ፥ደግሞ፡ሴኬምና፡መንደሮቿ፡እስከ፡ጋዛና፡እስከ፡መንደሮቿ፡ድረስ፥
29በምናሴም፡ልጆች፡ዳርቻ፡ቤትሳንና፡መንደሮቿ፥ታዕናክና፡መንደሮቿ፥መጊዶና፡መንደሮቿ፥ዶርና፡ መንደሮቿ፡ነበሩ፤በእነዚህ፡የእስራኤል፡ልጅ፡የዮሴፍ፡ልጆች፡ተቀመጡ።
30የአሴር፡ልጆች፡ዪምና፥የሱዋ፥የሱዊ፥በሪዐ፥እኅታቸውም፡ሤራሕ።
31የበሪዐም፡ልጆች፤ሔቤር፥የቢርዛዊት፡አባት፡የነበረው፡መልኪኤል።
32ሔቤርም፡ያፍሌጥ ን፥ሳሜርን፥ኮታም ን፥እኅታቸውንም፡ሶላን፡ወለደ።
33የያፍሌጥም፡ልጆች፡ፋሴክ፥ቢምኻል፥ዐሲት፡ነበሩ፤እነዚህ፡የያፍሌጥ፡ልጆች፡ነበሩ።
34የሳሜርም፡ልጆች፡አኪ፥ሮኦጋ፥ይሑባ፥አራም፡ነበሩ።
35የወንድሙም፡የዔላም፡ልጆች፡ጾፋ፥ይምና፥ሰሌስ፥ዓማል፡ነበሩ።
36የጾፋም፡ልጆች፡ሱዋ፥ሐርኔፍር፥
37ሦጋል፥ቤሪ፥ይምራ፥ቤጼር፥ሆድ፥ሳማ፥ሰሊሳ፥ይትራን፥ብኤራ፡ነበሩ።
38የዬቴር፡ልጆች፡ዮሮኒ ፥ፊሥጳ፥አራ፡ነበሩ። 213 ዕብ.፥በርዒያህ፡(በርዐ•ራደ)። 214 ዕብ.፥ያፍሌጥ፡(ይፈልጥ•ይለያል፥ለይቶ፡ያድናል)። 215 ዕብ.፥ኆታም፡(ማኅተም•በቁሙ፥ማተሚያ)። 216 ዕብ.፥የፉኔህ፡(ይዘጋጃል)። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
39የዑላ፡ልጆች፡ኤራ፥ሐኒኤል፥ሪጽያ፡ነበሩ።
40እነዚህ፡ዅሉ፡የአሴር፡ልጆች፥የአባቶቻቸው፡ቤቶች፡አለቃዎች፥የተመረጡ፡ጽኑዓን፡ኀያላን፡ ሰዎች፥የመኳንንቱ፡አለቃዎች፡ነበሩ።በትውልዳቸውም፡በሰልፍ፡ለመዋጋት፡የተቈጠሩ፡ኻያ፡ስድስት፡ሺሕ፡ ሰዎች፡ነበሩ።