1ንጉሡም፡ዳዊት፡ለጉባኤው፡ዅሉ፡እንዲህ፡አለ፦እግዚአብሔር፡ብቻውን፡የመረጠው፡ልጄ፡ሰሎሞን፡ ገና፡ብላቴና፡ለጋ፡ነው፤ሕንፃው፡ግን፡ለእግዚአብሔር፡ለአምላክ፡ነው፡እንጂ፡ለሰው፡አይደለምና፡ሥራው፡ ታላቅ፡ነው።
2እኔም፡እንደ፡ጕልበቴ፡ዅሉ፡ለአምላኬ፡ቤት፡ለወርቁ፡ዕቃ፡ወርቁን፥ለብሩም፡ዕቃ፡ብሩን፥ለናሱም፡ዕቃ፡ ናሱን፥ለብረቱም፡ዕቃ፡ብረቱን፥ለዕንጨቱም፡ዕቃ፡ዕንጨቱን፥ደግሞም፡መረግድንና፡በፈርጥ፡የሚገባ፡ ድንጋይን፥የሚለጠፍ፡ድንጋይን፥ልዩ፡ልዩ፡መልክ፡ያለውንም፡ድንጋይ፥የከበረውንም፡ድንጋይ፡ ከየዐይነቱ፥ብዙም፡እብነ፡በረድ፡አዘጋጅቻለኹ።
3ከዚህም፡በላይ፡ደግሞ፡የአምላኬን፡ቤት፡ስለ፡ወደድኹ፥ለመቅደሱ፡ካዘጋጀኹት፡ዅሉ፡ሌላ፡የግል፡ ገንዘቤ፡የሚኾን፡ወርቅና፡ብር፡አለኝና፡ለአምላኬ፡ቤት፡ሰጥቼዋለኹ።
4የቤቶቹ፡ግንብ፡ይለበጡበት፡ዘንድ፡ከኦፊር፡ወርቅ፡ሦስት፡ሺሕ፡መክሊት፡ወርቅ፥ሰባት፡ሺሕም፡ መክሊት፡ጥሩ፡ብር፥
5በሠራተኛዎች፡እጅ፡ለሚሠራው፡ሥራ፡ዅሉ፡ለወርቁ፡ዕቃ፡ወርቁን፥ለብሩም፡ዕቃ፡ብሩን፡ ሰጥቻለኹ።ዛሬ፡በፈቃዱ፡ራሱን፡ለእግዚአብሔር፡የሚቀድስ፡ማነው፧
6የአባቶችም፡ቤቶች፡አለቃዎች፥የእስራኤልም፡ነገዶች፡አለቃዎች፥ሻለቃዎችም፥የመቶ፡ አለቃዎችም፥በንጉሡም፡ሥራ፡ላይ፡የተሾሙት፡በፈቃዳቸው፡አቀረቡ።
7ለእግዚአብሔርም፡ቤት፡አገልግሎት፡ዐምስት፡ሺሕ፡መክሊት፡ወርቅና፡ዐሥር፡ሺሕ፡ዳሪክ፥ዐሥር፡ ሺሕም፡መክሊት፡ብር፥ዐሥራ፡ስምንት፡ሺሕም፡መክሊት፡ናስ፥መቶ፡ሺሕም፡መክሊት፡ብረት፡ሰጡ።
8ዕንቍም፡ያለው፡ሰው፡ዅሉ፡ለእግዚአብሔር፡ቤት፡ለኾነው፡ቤተ፡መዛግብት፡በጌድሶናዊው፡በይሒኤል፡ እጅ፡ሰጠ።
9ሕዝቡም፡ፈቅደው፡ሰጥተዋልና፥በፍጹም፡ልባቸውም፡ለእግዚአብሔር፡በፈቃዳቸው፡አቅርበዋልና፥ደስ፡ አላቸው፤ንጉሡም፡ዳዊት፡ደግሞ፡ታላቅ፡ደስታ፡ደስ፡አለው።
10ዳዊትም፡በጉባኤው፡ዅሉ፡ፊት፡እግዚአብሔርን፡ባረከ፤ዳዊትም፡አለ፦አቤቱ፥የአባታችን፡የእስራኤል፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org አምላክ፡ሆይ፥ከዘለዓለም፡እስከ፡ዘለዓለም፡ተባረክ።
11አቤቱ፥በሰማይና፡በምድር፡ያለው፡ዅሉ፡የአንተ፡ነውና፥ታላቅነትና፡ኀይል፥ክብርም፥ድልና፡ግርማ፡ ለአንተ፡ነው፤አቤቱ፥መንግሥት፡የአንተ፡ነው፥አንተም፡በዅሉ፡ላይ፡ከፍ፡ከፍ፡ያልኽ፡ራስ፡ነኽ።
12ባለጠግነትና፡ክብር፡ከአንተ፡ዘንድ፡ነው፥አንተም፡ዅሉን፡ትገዛለኽ፤ኀይልና፡ብርታት፡በእጅኽ፡ ነው፤ታላቅ፡ለማድረግ፥ለዅሉም፡ኀይልን፡ለመስጠት፡በእጅኽ፡ነው።
13አኹንም፡እንግዲህ፥አምላካችን፡ሆይ፥እንገዛልኻለን፥ለክቡር፡ስምኽም፡ምስጋና፡እናቀርባለን።
14ዅሉ፡ከአንተ፡ዘንድ፡ነውና፥ከእጅኽም፡የተቀበልነውን፡ሰጥተንኻልና፥ይህን፡ያኽል፡ችለን፡ልናቀርብልኽ፡ እኔ፡ማን፡ነኝ፧ሕዝቤስ፡ማን፡ነው፧
15አባቶቻችንም፡ዅሉ፡እንደነበሩ፡እኛ፡በፊትኽ፡ስደተኛዎችና፡መጻተኛዎች፡ነን፤ዘመናችንም፡በምድር፡ ላይ፡እንደ፡ጥላ፡ናት፥አትጸናም።
16አቤቱ፡አምላካችን፡ሆይ፥ለቅዱስ፡ስምኽ፡ቤት፡እንሠራ፡ዘንድ፡ይህ፡ያዘጋጀነው፡ባለጠግነት፡ዅሉ፡ ከእጅኽ፡የመጣ፡ነው፥ዅሉም፡የአንተ፡ነው።
17አምላኬ፡ሆይ፥ልብን፡እንድትመረምር፥ቅንነትንም፡እንድትወድ፟፡ዐውቃለኹ፤እኔም፡በልቤ፡ቅንነትና፡ በፈቃዴ፡ይህን፡ዅሉ፡አቅርቤያለኹ፤አኹንም፡በዚህ፡ያለው፡ሕዝብኽ፡በፈቃዱ፡እንዳቀረበልኽ፡በደስታ፡ አይቻለኹ።
18አቤቱ፥የአባቶቻችን፡የአብርሃምና፡የይሥሐቅ፡የእስራኤልም፡አምላክ፡ሆይ፥ይህን፡ዐሳብ፡በሕዝብኽ፡ልብ፡ ለዘለዓለም፡ጠብቅ፥ልባቸውንም፡ወዳንተ፡አቅና።
19ትእዛዝኽንም፡ምስክርኽንም፡ሥርዐትኽንም፡ይጠብቅ፡ዘንድ፥ይህንም፡ነገር፡ዅሉ፡ያደርግ፡ ዘንድ፥ያዘጋጀኹለትንም፡ቤት፡ይሠራ፡ዘንድ፡ለልጄ፡ለሰሎሞን፡ፍጹም፡ልብ፡ስጠው።
20ዳዊትም፡ጉባኤውን፡ዅሉ፦አምላካችኹን፡እግዚአብሔርን፡ባርኩ፡አላቸው።ጉባኤውም፡ዅሉ፡ የአባታቸውን፡አምላክ፡እግዚአብሔርን፡ባረኩ፥ራሳቸውንም፡አዘንብለው፡ለእግዚአብሔርና፡ለንጉሡ፡ሰገዱ።
21በነጋውም፡ለእግዚአብሔር፡መሥዋዕት፡ሠዉ፥የሚቃጠለውንም፡መሥዋዕት፡ለእግዚአብሔር፡ አቀረቡ፤አንድ፡ሺሕ፡ወይፈን፥አንድ፡ሺሕም፡አውራ፡በጎች፥አንድ፡ሺሕም፡የበግ፡ጠቦቶች፥የመጠጥ፡ ቍርባናቸውንም፥ስለ፡እስራኤልም፡ዅሉ፡ብዙ፡መሥዋዕት፡አቀረቡ።
22በዚያም፡ቀን፡በታላቅ፡ደስታ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡በሉ፡ጠጡም።የዳዊትንም፡ልጅ፡ሰሎሞንን፡ኹለተኛ፡ ጊዜ፡አነገሡት፤ርሱንም፡አለቃ፡ይኾን፡ዘንድ፡ለእግዚአብሔር፡ቀቡት፥ሳዶቅንም፡ካህን፡ይኾን፡ዘንድ፡ቀቡት።
23ሰሎሞንም፡በአባቱ፡በዳዊት፡ዙፋን፡ላይ፡ተቀመጠ፥ተከናወነለትም፤እስራኤልም፡ዅሉ፡ታዘዙለት።
24አለቃዎቹም፡ዅሉ፥ኀያላኑም፥ደግሞም፡የንጉሡ፡የዳዊት፡ልጆች፡ዅሉ፡ለንጉሡ፡ለሰሎሞን፡እጅ፡ ሰጡት።
25እግዚአብሔርም፡ሰሎሞንን፡በእስራኤል፡ዅሉ፡ፊት፡እጅግ፡አገነነው፤ከርሱ፡በፊትም፡ለነበሩት፡ ለእስራኤል፡ነገሥታት፡ያልኾነውን፡የመንግሥት፡ክብር፡ሰጠው።
26የእሴይም፡ልጅ፡ዳዊት፡በእስራኤል፡ዅሉ፡ላይ፡ነገሠ።
27በእስራኤልም፡ላይ፡የነገሠበት፡ዘመን፡አርባ፡ዓመት፡ነበረ፤ሰባት፡ዓመት፡በኬብሮን፡ነገሠ፥ሠላሳ፡ ሦስትም፡ዓመት፡በኢየሩሳሌም፡ነገሠ።
28ዕድሜም፥ባለጠግነትም፥ክብርም፡ጠግቦ፡በመልካም፡ሽምግልና፡ሞተ፤ልጁም፡ሰሎሞን፡በርሱ፡ፋንታ፡ ነገሠ።
29የንጉሡም፡የዳዊት፡የፊተኛውና፡የዃለኛው፡ነገር፥እንሆ፥በባለራእዩ፡በሳሙኤል፡ታሪክ፥በነቢዩም፡ በናታን፡ታሪክ፥በባለራእዩም፡በጋድ፡ታሪክ፡ተጽፏል። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
30እንደዚሁም፡የመንግሥቱ፡ነገርና፡ኀይሉ፡ዅሉ፡በርሱም፡በእስራኤልም፡በአገሮችም፡መንግሥታት፡ዅሉ፡ ላይ፡ያለፉት፡ዘመናት፡ተጽፈዋል፨ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org