Skip to content
← 1 Chronicles

Chapter 28 · Amharic

1 Chronicles

1ዳዊትም፡የእስራኤልን፡አለቃዎች፡ዅሉ፥የነገዶቹንም፡አለቃዎች፥ንጉሡንም፡በክፍል፡የሚያገለግሉትን፡ የጭፍራዎች፡አለቃዎች፥ሻለቃዎቹንም፥የመቶ፡አለቃዎችንም፥በንጉሥና፡በልጆች፡ሀብትና፡ግዛት፡ላይ፡ የተሾሙትን፥ጃን፡ደረባዎችንም፥ጽኑዓን፡ኀያላኑንም፡ዅሉ፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ሰበሰበ።

2ንጉሡም፡ዳዊት፡በእግሩ፡ቆሞ፡እንዲህ፡አለ፦ወንድሞቼና፡ሕዝቤ፡ሆይ፥ስሙኝ፤ለእግዚአብሔር፡ ለቃል፡ኪዳኑ፡ታቦትና፡ለአምላካችን፡እግር፡ማረፊያ፡የዕረፍት፡ቤት፡ለመሥራት፡እኔ፡በልቤ፡ ዐስቤያለኹ፤ለሥራም፡የሚያስፈልገውን፡አዘጋጅቻለኹ፤

3እግዚአብሔር፡ግን፦የሰልፍ፡ሰው፡ነኽና፥ደምም፡አፍሰ፟ኻልና፥ለስሜ፡ቤት፡አትሠራም፡ብሎኛል።

4ነገር፡ግን፥የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡በእስራኤል፡ላይ፡የዘለዓለም፡ንጉሥ፡እኾን፡ዘንድ፡ከአባቴ፡ ቤት፡ዅሉ፡መርጦኛል፤ይሁዳም፡አለቃ፡ይኾን፡ዘንድ፡መርጦታል፤ከይሁዳም፡ቤት፡የአባቴን፡ቤት፡ መርጧል፤ከአባቴም፡ልጆች፡መካከል፡በእስራኤል፡ዅሉ፡ላይ፡ያነግሠኝ፡ዘንድ፡ሊመርጠኝ፡ወደደ።

5እግዚአብሔርም፡ብዙ፡ልጆች፡ሰጥቶኛልና፥ከልጆቼ፡ዅሉ፡በእግዚአብሔር፡መንግሥት፡ዙፋን፡ላይ፡ ተቀምጦ፡በእስራኤል፡ላይ፡ይነግሥ፡ዘንድ፡ልጄን፡ሰሎሞንን፡መርጦታል።

6ርሱም፦ልጅ፡ይኾነኝ፡ዘንድ፡መርጬዋለኹና፥እኔም፡አባት፡እኾነዋለኹና፡ልጅኽ፡ሰሎሞን፡ቤቴንና፡ አደባባዮቼን፡ይሠራል።

7ትእዛዜንና፡ፍርዴንም፡በማድረግ፡እንደ፡ዛሬው፡ቢጸና፡መንግሥቱን፡ለዘለዓለም፡አጸናዋለኹ፡አለኝ።

8አኹንም፡የእግዚአብሔር፡ጉባኤ፡እስራኤል፡ዅሉ፡እያዩ፥አምላካችንም፡እየሰማ፥ይህችን፡መልካሚቱን፡ ምድር፡ትወርሱ፡ዘንድ፥ለልጆቻችኹም፡ለዘለዓለም፡ታወርሷት፡ዘንድ፡የአምላካችኹን፡የእግዚአብሔርን፡ ትእዛዝ፡ዅሉ፡ጠብቁ፥ፈልጉም።

9አንተም፥ልጄ፡ሰሎሞን፡ሆይ፥እግዚአብሔር፡ልብን፡ዅሉ፡ይመረምራልና፥የነፍስንም፡ዐሳብ፡ዅሉ፡ ያውቃልና፥የአባትኽን፡አምላክ፡ዕወቅ፤በፍጹም፡ልብና፡በነፍስኽ፡ፈቃድም፡አምልከው፤ብትፈልገው፡ ታገኘዋለኽ፤ብትተወው፡ግን፡ለዘለዓለም፡ይጥልኻል።

10አኹንም፥እንሆ፥እግዚአብሔር፡ለመቅደስ፡የሚኾን፡ቤትን፡ትሠራ፡ዘንድ፡መርጦኻልና፥ጠንክረኽ፡ ፈጽመው።

11ዳዊትም፡ለመቅደሱ፡ወለል፥ለቤቱም፥ለቤተ፡መዛግብቱም፥ለደርቡና፡ለውስጡም፡ጓዳዎች፥ለስርየቱም፡ መክደኛ፡መቀመጫ፡ምሳሌውን፡ለልጁ፡ለሰሎሞን፡ሰጠው።

12ደግሞም፡ለእግዚአብሔር፡ቤት፡አደባባዮችና፡በዙሪያው፡ለሚኾኑ፡ጓዳዎች፥ለእግዚአብሔርም፡ቤት፡ ለሚኾኑ፡ቤተ፡መዛግብት፥ለንዋየ፡ቅድሳቱም፡ለሚኾኑ፡ቤተ፡መዛግብት፡በመንፈሱ፡ላሰበው፡ዅሉ፡ምሳሌን፡ ሰጠው።

14የካህናቱንና፡የሌዋውያኑንም፡ክፍላቸውን፡በእግዚአብሔርም፡ቤት፡በሚያገለግሉበት፡ሥራ፡ዅሉ፡ አስታወቀው።በእግዚአብሔርም፡ቤት፡ለሚያገለግሉበት፡ዕቃ፡ዅሉ፥ለአገልግሎት፡ዅሉ፡ለሚኾነውም፡ለወርቁ፡ ዕቃ፡ወርቁን፡በሚዛን፡ሰጠው፤ለአገልግሎት፡ዅሉ፡ለሚኾነውም፡ለብር፡ዕቃ፡ዅሉ፡ብሩን፡በሚዛን፡ሰጠው፤

15ለወርቁም፡መቅረዞችና፡ለቀንዲሎችም፡ወርቁን፡በየመቅረዙና፡በየቀንዲሉ፡በሚዛን፡ሰጠው፤ለብሩም፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org መቅረዞች፡እንደ፡መቅረዙ፡ዅሉ፡ሥራ፡ዅሉ፡ብሩን፡በየመቅረዙና፡በየቀንዲሉ፡በሚዛን፡ሰጠው፤

16ለገጹ፡ኅብስት፡ገበታዎች፡ወርቁን፡በሚዛን፡ለገበታዎቹ፡ዅሉ፥ብሩንም፡ለብሩ፡ገበታዎች፡ሰጠው፤

17ለሜንጦቹና፡ለድስቶቹ፡ለመቅጃዎቹም፡ጥሩውን፡ወርቅ፥ለወርቁም፡ጽዋዎች፡ወርቁን፡በየጽዋው፡ዅሉ፡ በሚዛን፥ለብሩም፡ጽዋዎች፡ብሩን፡በየጽዋው፡ዅሉ፡በሚዛን፡ሰጠው፤

18ለዕጣኑም፡መሠዊያ፡ጥሩውን፡ወርቅ፡በሚዛን፥ክንፎቻቸውንም፡ዘርግተው፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ኪዳን፡ ታቦት፡የሸፈኑትን፡የኪሩቤልን፡የወርቅ፡ሠረገላ፡ምሳሌ፡ሰጠው።

19ዳዊትም፦የሥራውን፡ዅሉ፡ምሳሌ፡ዐውቅ፡ዘንድ፡ይህ፡ዅሉ፡በእግዚአብሔር፡እጅ፡ተጽፎ፡መጣልኝ፡ አለ።

20ዳዊትም፡ልጁን፡ሰሎሞንን፦ጠንክር፥አይዞኽ፥አድርገውም፤አምላኬ፡እግዚአብሔር፡አምላክ፡ከአንተ፡ ጋራ፡ነውና፥አትፍራ፥አትደንግጥም፤ለእግዚአብሔርም፡ቤት፡አገልግሎት፡የሚኾነው፡ሥራ፡ዅሉ፡እስኪፈጸም፡ ድረስ፡ርሱ፡አይተውኽም፥አይጥልኽምም።

21እንሆም፥ለእግዚአብሔር፡ቤት፡አገልግሎት፡ዅሉ፡የሚኾኑ፡የካህናትና፡የሌዋውያን፡ክፍሎች፡በዚህ፡ አሉ፤ለዅሉም፡ዐይነት፡አገልግሎትና፡ሥር፡በብልኀትና፡በነፍሱ፡ፈቃድ፡የሚሠራ፡ዅሉ፡ከአንተ፡ጋራ፡ ይኾናል፤አለቃዎችና፡ሕዝቡም፡ዅሉ፡ፈጽመው፡ይታዘዙኻል፡አለው።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source