1የእስራኤልም፡ልጆች፡የአባቶች፡ቤቶች፡አለቃዎችና፡የሺሕ፡አለቃዎች፡የመቶ፡አለቃዎችም፡በክፍሎች፡ ነገር፡ዅሉ፡ንጉሡን፡ያገለገሉትም፡ሹማምት፡እንደ፡ቍጥራቸው፡እነዚህ፡ነበሩ።እነዚህም፡ክፍሎች፡ እያንዳንዳቸው፡ኻያ፡አራት፡ሺሕ፡ኾነው፡በዓመት፡ወራት፡ዅሉ፡በየወሩ፡ይገቡና፡ይወጡ፡ነበር።
2ለመዠመሪያው፡ወር፡በአንደኛው፡ክፍል፡ላይ፡የዘብድኤል፡ልጅ፡ያሾብዓም፡ነበረ፤በርሱም፡ክፍል፡ኻያ፡ አራት፡ሺሕ፡ጭፍራ፡ነበረ።
3ርሱ፡ከፋሬስ፡ልጆች፡ነበረ፤ለመዠመሪያው፡ወር፡በጭፍራ፡አለቃዎች፡ዅሉ፡ላይ፡ተሾሞ፡ነበር።
4በኹለተኛውም፡ወር፡ክፍል፡ላይ፡አሖሓዊው፡ዱዲ፡ነበረ፤በርሱም፡ክፍል፡ኻያ፡አራት፡ሺሕ፡ጭፍራ፡ ነበረ።
5ለሦስተኛው፡ወር፡ሦስተኛው፡የጭፍራ፡አለቃ፡የካህኑ፡የዮዳዔ፡ልጅ፡በናያስ፡ነበረ፤በርሱም፡ክፍል፡ኻያ፡ አራት፡ሺሕ፡ጭፍራ፡ነበረ።
6ይህ፡በናያስ፡በሠላሳው፡መካከል፡ኀያል፡ኾኖ፡በሠላሳው፡ላይ፡ነበረ፤በርሱም፡ክፍል፡ልጁ፡ዓሚዛባድ፡ ነበረ።
7ለአራተኛው፡ወር፡አራተኛው፡አለቃ፡የኢዮአብ፡ወንድም፡ዐሳሄል፥ከርሱም፡በዃላ፡ልጁ፡ዝባድያ፡ ነበረ፤በርሱም፡ክፍል፡ኻያ፡አራት፡ሺሕ፡ጭፍራ፡ነበር።
8ለዐምስተኛው፡ወር፡ዐምስተኛው፡አለቃ፡ይዝራዊው፡ሸምሁት፡ነበረ፤በርሱም፡ክፍል፡ኻያ፡አራት፡ሺሕ፡ ጭፍራ፡ነበረ።
9ለስድስተኛው፡ወር፡ስድስተኛው፡አለቃ፡የቴቁሐዊው፡የዒስካ፡ልጅ፡ዒራስ፡ነበረ፤በርሱም፡ክፍል፡ኻያ፡ አራት፡ሺሕ፡ጭፍራ፡ነበረ።
10ለሰባተኛው፡ወር፡ሰባተኛው፡አለቃ፡ከኤፍሬም፡ልጆች፡የኾነ፡ፍሎናዊው፡ሴሌስ፡ነበረ፤በርሱም፡ክፍል፡ ኻያ፡አራት፡ሺሕ፡ጭፍራ፡ነበረ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
11ለስምንተኛው፡ወር፡ስምንተኛው፡አለቃ፡ከዛራውያን፡የነበረው፡ኩሳታዊው፡ሲቦካይ፡ነበረ፤በርሱም፡ክፍል፡ ኻያ፡አራት፡ሺሕ፡ጭፍራ፡ነበረ።
12ለዘጠነኛው፡ወር፡ዘጠነኛው፡አለቃ፡ከብንያማውያን፡የነበረው፡ዓናቶታዊው፡አቢዔዜር፡ነበረ፤በርሱም፡ ክፍል፡ኻያ፡አራት፡ሺሕ፡ጭፍራ፡ነበረ።
13ለዐሥረኛው፡ወር፡ዐሥረኛው፡አለቃ፡ከዛራውያን፡የነበረው፡ነጦፋዊው፡ኖኤሬ፡ነበረ፤በርሱም፡ክፍል፡ ኻያ፡አራት፡ሺሕ፡ጭፍራ፡ነበረ።
14ለዐሥራ፡አንደኛው፡ወር፡ዐሥራ፡አንደኛው፡አለቃ፡ከኤፍሬም፡ልጆች፡የነበረው፡ጲርዓቶናዊው፡በናያስ፡ ነበረ፤በርሱም፡ክፍል፡ኻያ፡አራት፡ሺሕ፡ጭፍራ፡ነበረ።
15ለዐሥራ፡ኹለተኛው፡ወር፡ዐሥራ፡ኹለተኛው፡አለቃ፡ከጎቶንያል፡ወገን፡የነበረው፡ነጦፋዊው፡ሔልዳይ፡ ነበረ፤በርሱም፡ክፍል፡ኻያ፡አራት፡ሺሕ፡ጭፍራ፡ነበረ።
16በእስራኤልም፡ነገዶች፡ላይ፡እነዚህ፡ነበሩ፡በሮቤላውያን፡ላይ፡የዝክሪ፡ልጅ፡አልዓዛር፡አለቃ፡ ነበረ፤በስምዖናውያን፡የመዓካ፡ልጅ፡ሰፋጥያስ፤
17በሌዊ፡ላይ፡የቀሙኤል፡ልጅ፡ሐሸቢያ፤
18በአሮን፡ላይ፡ሳዶቅ፤በይሁዳ፡ላይ፡ከዳዊት፡ወንድሞች፡ኤሊሁ፤በይሳኮር፡ላይ፡የሚካኤል፡ልጅ፡ዖምሪ፤
19በዛብሎን፡ላይ፡የዐብድዩ፡ልጅ፡ይሽማያ፤በንፍታሌም፡ላይ፡የዓዝሪኤል፡ልጅ፡ኢያሪሙት፤
20በኤፍሬም፡ልጆች፡ላይ፡የዓዛዝያ፡ልጅ፡ሆሴዕ፤በምናሴ፡ነገድ፡እኩሌታ፡ላይ፡የፈዳያ፡ልጅ፡ኢዮኤል፤
21በገለዓድ፡ባለው፡በምናሴ፡ነገድ፡እኩሌታ፡ላይ፡የዘካርያስ፡ልጅ፡አዶ፤በብንያም፡ላይ፡የአበኔር፡ልጅ፡ የዕሢኤል፤
22በዳን፡ላይ፡የይሮሐም፡ልጅ፡ዓዛርኤል፤እነዚህ፡የእስራኤል፡ልጆች፡ነገዶች፡አለቃዎች፡ነበሩ።
23እግዚአብሔር፡ግን፡እስራኤልን፡እንደሰማይ፡ከዋክብት፡ያበዛ፡ዘንድ፡ተናግሮ፡ነበርና፥ዳዊት፡ከኻያ፡ ዓመት፡በታች፡የነበሩትን፡አልቈጠረም።
24የጽሩያ፡ልጅ፡ኢዮአብ፡መቍጠር፡ዠመረ፥ነገር፡ግን፥አልፈጸመም፤ስለዚህም፡በእስራኤል፡ላይ፡ቍጣ፡ ኾነ፥ቍጥራቸውም፡በንጉሡ፡በዳዊት፡መዝገብ፡አልተጻፈም።
25በንጉሡም፡ቤተ፡መዛግብት፡ላይ፡የዓዲኤል፡ልጅ፡ዓዝሞት፡ሹም፡ነበረ፤በሜዳውም፡በከተማዎችም፡ በመንደሮችም፡በግንቦችም፡ቤተ፡መዛግብት፡ላይ፡የዖዝያ፡ልጅ፡ዮናታን፡ሹም፡ነበረ፤
26መሬቱን፡የሚያበጃጁትና፡ዕርሻውን፡በሚያርሱት፡ላይ፡የክሉብ፡ልጅ፡ዔዝሪ፡ሹም፡ነበረ፤
27በወይንም፡ቦታዎች፡ላይ፡ራማታዊው፡ሰሜኢ፡ሹም፡ነበረ፤ለወይንም፡ጠጅ፡ዕቃ፡ቤት፡በሚኾነው፡ በወይኑ፡ሰብል፡ላይ፡ሸፋማዊው፡ዘብዲ፡ሹም፡ነበረ፤
28በቈላውም፡ውስጥ፡ባሉት፡በወይራውና፡በሾላው፡ዛፎች፡ላይ፡ጌድራዊው፡በአልሐናን፡ሹም፡ ነበረ፤በዘይቱም፡ቤቶች፡ላይ፡ኢዮአስ፡ሹም፡ነበረ፤
29በሳሮንም፡በሚሰማሩ፡ከብቶች፡ላይ፡ሳሮናዊው፡ሰጥራይ፡ሹም፡ነበረ፤በሸለቆዎቹም፡ውስጥ፡በነበሩት፡ ከብቶች፡ላይ፡የዓድላይ፡ልጅ፡ሻፍጥ፡ሹም፡ነበረ፤
30በግመሎችም፡ላይ፡እስማኤላዊው፡ኡቢያስ፡ሹም፡ነበረ፤በአህያዎቹም፡ላይ፡ሜሮኖታዊው፡ይሕድያ፡ ሹም፡ነበረ፤
31በመንጋዎቹም፡ላይ፡አጋራዊው፡ያዚዝ፡ሹም፡ነበረ።እነዚህ፡ዅሉ፡በንጉሡ፡በዳዊት፡ሀብት፡ላይ፡ ሹሞች፡ነበሩ።
32አስተዋይና፡ጸሓፊ፡የነበረው፡የዳዊት፡አጎት፡ዮናታን፡አማካሪ፡ነበረ፤የሐክሞኒም፡ልጅ፡ይሒኤል፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ከንጉሡ፡ልጆች፡ጋራ፡ነበረ፤
33አኪጦፌልም፡የንጉሡ፡አማካሪ፡ነበረ፤አርካዊውም፡ኩሲ፡የንጉሡ፡ወዳጅ፡ነበረ፤
34ከአኪጦፌልም፡ቀጥሎ፡የበናያስ፡ልጅ፡ዮዳዔና፡አብያታር፡ነበሩ፤ኢዮአብም፡የንጉሡ፡ሰራዊት፡አለቃ፡ ነበረ።