1በረኛዎችም፡እንደዚህ፡ተመደቡ፤ከቆሬያውያን፡ከአሣፍ፡ልጆች፡የቆሬ፡ልጅ፡ሜሱላም።
2ሜሱላም፡ልጆች፡ነበሩት፤በኵሩ፡ዘካርያስ፥ኹለተኛው፡ይዲኤል፥ሦስተኛው፡ዮዛባት፥ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
3አራተኛው፡የትኒኤል፥ዐምስተኛው፡ዔላም፥ስድስተኛው፡ይሆሐናን፥ሰባተኛው፡ኤሊሆዔናይ።
4እግዚአብሔርም፡ባርኮታልና፥ዖቤድኤዶም፡ልጆች፡ነበሩት፤በኵሩ፡ሸማያ፥ኹለተኛው፡ዮዛባት፥ሦስተኛው፡ ኢዮአስ፥አራተኛው፡ሣካር፥ዐምስተኛው፡ናትናኤል፥
5ስድስተኛው፡ዓሚኤል፥ሰባተኛው፡ይሳኮር፥ስምንተኛው፡ፒላቲ።
6ለልጁም፡ለሸማያ፡ደግሞ፡ልጆች፡ተወለዱለት፤ጽኑዓንም፡ኀያላን፡ነበሩና፥በአባታቸው፡ቤት፡ሠለጠኑ።
7ለሸማያ፡ልጆች፡ዖትኒ፥ራፋኤል ፥ዖቤድ፥ወንድሞቹም፡ኀያላን፡የነበሩ፡ኤልዛባድ፥ኤልሁ ፥ሰማክያ።
8እነዚህ፡ዅሉ፡የዖቤድኤዶም፡ልጆች፡ነበሩ፤እነርሱም፡ልጆቻቸውም፡ወንድሞቻቸውም፡ለማገልገል፡ኀያላን፡ የነበሩ፡የዖቤድኤዶም፡ልጆች፡ስድሳ፡ኹለት፡ነበሩ።
9ለሜሱላም፡ኀያላን፡የነበሩ፡ዐሥራ፡ስምንት፡ልጆችና፡ወንድሞች፡ነበሩት።
10ከሜራሪም፡ልጆች፡ለነበረው፡ለሖሳ፡ልጆች፡ነበሩት፤አለቃውም፡ሽምሪ፡ነበረ፤በኵር፡አልነበረም፥አባቱ፡ ግን፡አለቃ፡አደረገው፤
11ኹለተኛውም፡ኬልቅያስ፥ሦስተኛው፡ጥበልያ፥አራተኛው፡ዘካርያስ፡ነበረ፤የሖሳ፡ልጆችና፡ወንድሞች፡ ዅሉ፡ዐሥራ፡ሦስት፡ነበሩ።
12እንደ፡ወንድሞቻቸው፡ኾነው፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡ያገለግሉ፡ዘንድ፡የበረኛዎች፡የአለቃዎች፡ሰሞነኛዎች፡ እነዚህ፡ነበሩ።
13በበሩም፡ዅሉ፡ያገለግሉ፡ዘንድ፡በያባቶቻቸው፡ቤቶች፡ታናሹና፡ታላቁ፡ተካክለው፡ዕጣ፡ተጣጣሉ።
14በምሥራቅም፡በኩል፡ዕጣ፡ለሰሌምያ፡ወደቀ።ለልጁም፡ብልኅ፡መካር፡ለኾነው፡ለዘካርያስ፡ዕጣ፡ ጣሉ፤ዕጣውም፡በሰሜን፡በኩል፡ወጣ።
15ለዖቤድኤዶም፡በደቡብ፡በኩል፥ለልጆቹም፡ለዕቃ፡ቤቱ፡ዕጣ፡ወጣ።
16ለሰፊንና፡ለሖሳ፡በምዕራብ፡በኩል፥በዐቀበቱም፡መንገድ፡ባለው፡በሸሌኬት፡በር፡በኩል፡ጥበቃ፡ከጥበቃ፡ ላይ፡ዕጣ፡ወጣ።
17በምሥራቅ፡በኩል፡ስድስት፡ሌዋውያን፡ነበሩ፤በሰሜን፡በኩል፡ለየዕለቱ፡አራት፥በደቡብ፡በኩል፡ለየዕለቱ፡ አራት፥ለዕቃ፡ቤቱም፡ኹለት፡ኹለት፡ነበሩ።
18በምዕራብ፡በኩል፡በፈርባር፡መንገድ፡ላይ፡አራት፥በፈርባርም፡አጠገብ፡ኹለት፡ነበሩ።
19ከቆሬና፡ከሜራሪ፡ልጆች፡የነበሩ፡የበረኛዎች፡ሰሞን፡ይህ፡ነበረ።
20ከሌዋውያን፡አኪያ፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡በሚኾኑ፡ቤተ፡መዛግብትና፡በንዋየ፡ቅድሳቱ፡ቤተ፡መዛግብት፡ ላይ፡ተሾሞ፡ነበር።
21የለአዳን፡ልጆች፤ለለአዳን፡የኾኑ፡የጌድሶናውያን፡ልጆች፥ለጌድሶናዊ፡ለለአዳን፡የኾኑ፡የአባቶች፡ቤቶች፡ አለቃዎች፡ይሒኤሊ፤
22የይሒኤሊ፡ልጆች፤በእግዚአብሔር፡ቤት፡በሚኾኑ፡ቤተ፡መዛግብት፡ላይ፡የነበሩ፡ዜቶም፥ወንድሙም፡ ኢዮኤል።
23ከዕምበረማውያን፥ከይስዓራውያን፥ከኬብሮናውያን፥ከዑዝኤላውያን፤
24የሙሴ፡ልጅ፡የጌርሳም፡ልጅ፡ሱባኤል፡በቤተ፡መዛግብት፡ላይ፡ተሾሞ፡ነበር።
25ወንድሞቹም፤ከአልዓዛር፡ልጁ፡ረዓብያ፥ልጁም፡የሻያ፥ልጁም፡ኢዮራም፥ልጁም፡ዝክሪ፥ልጁም፡ ሰሎሚት፡መጡ። 230 ዕብ.፥ርፋኤል፡(ረፍአ፡አምላክ•አምላክ፡ፈወሰ፥ጠገነ)። 231 ዕብ.፥ኤሊሁ፡(አምላኩ)። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
26ይህ፡ሰሎሚትና፡ወንድሞቹ፡ንጉሡ፡ዳዊትና፡የአባቶች፡ቤቶች፡አለቃዎች፥ሻለቃዎችና፡የመቶ፡ አለቃዎች፡የሰራዊቱም፡አለቃዎች፥በቀደሱት፡በንዋየ፡ቅድሳቱ፡ቤተ፡መዛግብት፡ዅሉ፡ላይ፡ተሾመው፡ነበር።
27በሰልፍም፡ከተገኘው፡ምርኮ፡የእግዚአብሔርን፡ቤት፡ለማበጀት፡ቀደሱ።
28ባለራእዩም፡ሳሙኤል፥የቂስም፡ልጅ፡ሳኦል፥የኔርም፡ልጅ፡አበኔር፥የጽሩያም፡ልጅ፡ኢዮአብ፡የቀደሱት፡ ንዋየ፡ቅድሳት፡ዅሉ፡ከሰሎሚትና፡ከወንድሞቹ፡እጅ፡በታች፡ነበረ።
29ከይስዓራውያን፡ከናንያና፡ልጆቹ፡ሹማምትና፡ፈራጆች፡ይኾኑ፡ዘንድ፡በውጭው፡ሥራ፡በእስራኤል፡ላይ፡ ተሾመው፡ነበር።
30ከኬብሮናውያን፡ሐሸብያና፡ወንድሞቹ፥ጽኑዓን፡የነበሩት፡ሺሕ፡ሰባት፡መቶ፡ሰዎች፥ለእግዚአብሔር፡ ሥራ፡ዅሉ፡ለንጉሡም፡አገልግሎት፡በዮርዳኖስ፡ማዶ፡በምዕራብ፡በኩል፡ባለው፡በእስራኤል፡ላይ፡ተሾመው፡ ነበር።
31ከኬብሮናውያንም፡እንደ፡አባቶች፡ቤቶች፡ትውልዶች፡የኬብሮናውያን፡አለቃ፡ይርያ፡ነበረ።ዳዊት፡በነገሠ፡ በአርባኛው፡ዓመት፡ይፈልጓቸው፡ነበር፤በእነርሱም፡መካከል፡በገለዓድ፡ኢያዜር፡ጽኑዓን፡ኀያላን፡ሰዎች፡ ተገኙ፤
32ወንድሞቹም፡ጽኑዓን፡የነበሩት፡የአባቶች፡ቤቶች፡አለቃዎች፡ኹለት፡ሺሕ፡ሰባት፡መቶ፡ነበሩ።ንጉሡም፡ ዳዊት፡ለእግዚአብሔር፡ጕዳይ፡ዅሉና፡ለንጉሡ፡ጕዳይ፡በሮቤላውያንና፡በጋዳውያን፡በምናሴም፡ነገድ፡እኩሌታ፡ ላይ፡ሹሞች፡አደረጋቸው።