Skip to content
← 1 Chronicles

Chapter 25 · Amharic

1 Chronicles

1ዳዊትና፡የሰራዊቱ፡አለቃዎችም፡ከአሣፍና፡ከኤማን፡ከኤዶታም፡ልጆች፡በመሰንቆና፡በበገና፡በጸናጽልም፡ ትንቢት፡የሚናገሩትን፡ሰዎች፡ለማገልገል፡ለዩ፤በአገልግሎታቸውም፡ሥራ፡የሠሩ፡ሰዎች፡ቍጥር፡ይህ፡ነበረ።

2ከአሣፍ፡ልጆች፤ዘኩር፥ዮሴፍ፥ነታንያ፥አሸርኤላ፤እነዚህ፡የአሣፍ፡ልጆች፡በንጉሡ፡ትእዛዝ፡ትንቢት፡ ከተናገረው፡ከአሣፍ፡እጅ፡በታች፡ነበሩ።

3ከኤዶታም፡የኤዶታም፡ልጆች፤ጎዶልያስ፥ጽሪ፥የሻያ፥ሰሜኢ፥ሐሸብያ፥መቲትያ፥እነዚህ፡ስድስቱ፡ ለእግዚአብሔር፡ምስጋናና፡ክብር፡በመሰንቆ፡ትንቢት፡ከተናገረው፡ከአባታቸው፡ከኤዶታም፡እጅ፡በታች፡ነበሩ።

4ከኤማን፡የኤማን፡ ልጆች፤ቡቅያ፥መታንያ፥ዓዛርዔል፥ሱባኤል፥ኢያሪሙት፥ሐናንያ፥ሐናኒ፥ኤልያታ፥ጊዶልቲ፥ሮማንቲዔዘር፥ዮ ሽብቃሻ፥መሎቲ፥ሆቲር፥መሐዝዮት፤

5እነዚህ፡ዅሉ፡ቀንደ፡መለከቱን፡ከፍ፡ያደርጉ፡ዘንድ፡በእግዚአብሔር፡ቃል፡የንጉሡ፡ባለራእይ፡የኾነው፡ የኤማን፡ልጆች፡ነበሩ።እግዚአብሔርም፡ለኤማን፡ዐሥራ፡አራት፡ወንዶች፡ልጆችንና፡ሦስት፡ሴቶች፡ልጆችን፡ ሰጠው። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

6እነዚህ፡ዅሉ፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡በጸናጽልና፡በበገና፡በመሰንቆም፡ይዘምሩ፡ዘንድ፥በእግዚአብሔርም፡ ቤት፡ያገለግሉ፡ዘንድ፡ከአባታቸው፡እጅ፡በታች፡ነበሩ፤አሣፍም፡ኤዶታምም፡ኤማንም፡ከንጉሡ፡ትእዛዝ፡ በታች፡ነበሩ።

7የብልኀተኛዎቹም፡ቍጥር፡እግዚአብሔርን፡ለማመስገን፡ከሚያውቁ፡ከወንድሞቻቸው፡ጋራ፡ኹለት፡መቶ፡ ሰማንያ፡ስምንት፡ነበረ።

8ዅሉም፡ተካክለው፥ታናሹ፡እንደ፡ታላቁ፥አስተማሪውም፡እንደ፡ተማሪው፥ለሰሞናቸው፡ዕጣ፡ተጣጣሉ።

9የፊተኛው፡ዕጣ፡ከአሣፍ፡ወገን፡ለነበረው፡ለዮሴፍ፡ወጣ፤ኹለተኛው፡ለጎዶልያስ፡ወጣ፤ርሱ፡ ወንድሞቹም፡ልጆቹም፡ዐሥራ፡ኹለት፡ነበሩ፤

10ሦስተኛው፡ለዘኩር፡ለልጆቹም፡ለወንድሞቹም፡ለዐሥራ፡ኹለቱ፤

11አራተኛው፡ለይጽሪ፡ለልጆቹም፡ለወንድሞቹም፡ለዐሥራ፡ኹለቱ፤

12ዐምስተኛው፡ለነታንያ፡ለልጆቹም፡ለወንድሞቹም፡ለዐሥራ፡ኹለቱ፤

13ስድስተኛው፡ለቡቅያ፡ለልጆቹም፡ለወንድሞቹም፡ለዐሥራ፡ኹለቱ፤

14ሰባተኛው፡ለይሽርኤል፡ለልጆቹም፡ለወንድሞቹም፡ለዐሥራ፡ኹለቱ፤

15ስምንተኛው፡ለየሻያ፡ለልጆቹም፡ለወንድሞቹም፡ለዐሥራ፡ኹለቱ፤

16ዘጠነኛው፡ለመታንያ፡ለልጆቹም፡ለወንድሞቹም፡ለዐሥራ፡ኹለቱ፤

17ዐሥረኛው፡ለሰሜኢ፡ለልጆቹም፡ለወንድሞቹም፡ለዐሥራ፡ኹለቱ፤

18ዐሥራ፡አንደኛው፡ለዓዛርኤል፡ለልጆቹም፡ለወንድሞቹም፡ለዐሥራ፡ኹለቱ፤

19ዐሥራ፡ኹለተኛው፡ለሐሸብያ፡ለልጆቹም፡ለወንድሞቹም፡ለዐሥራ፡ኹለቱ፤

20ዐሥራ፡ሦስተኛው፡ለሱባኤል፡ለልጆቹም፡ለወንድሞቹም፡ለዐሥራ፡ኹለቱ፤

21ዐሥራ፡አራተኛው፡ለመቲትያ፡ለልጆቹም፡ለወንድሞቹም፡ለዐሥራ፡ኹለቱ፤

22ዐሥራ፡ዐምስተኛው፡ለኢያሪሙት፡ለልጆቹም፡ለወንድሞቹም፡ለዐሥራ፡ኹለቱ፤

23ዐሥራ፡ስድስተኛው፡ለሐናንያ፡ለልጆቹም፡ለወንድሞቹም፡ለዐሥራ፡ኹለቱ፤

24ዐሥራ፡ሰባተኛው፡ለዮሽብቃሻ፡ለልጆቹም፡ለወንድሞቹም፡ለዐሥራ፡ኹለቱ፤

25ዐሥራ፡ስምንተኛው፡ለሐናኒ፡ለልጆቹም፡ለወንድሞቹም፡ለዐሥራ፡ኹለቱ፤

26ዐሥራ፡ዘጠነኛው፡ለመሎቲ፡ለልጆቹም፡ለወንድሞቹም፡ለዐሥራ፡ኹለቱ፤

27ኻያኛው፡ለኤልያታ፡ለልጆቹም፡ለወንድሞቹም፡ለዐሥራ፡ኹለቱ፤

28ኻያ፡አንደኛው፡ለሆቲር፡ለልጆቹም፡ለወንድሞቹም፡ለዐሥራ፡ኹለቱ፤

29ኻያ፡ኹለተኛው፡ለጊዶልቲ፡ለልጆቹም፡ለወንድሞቹም፡ለዐሥራ፡ኹለቱ፤

30ኻያ፡ሦስተኛው፡ለመሐዚዮት፡ለልጆቹም፡ለወንድሞቹም፡ለዐሥራ፡ኹለቱ፤

31ኻያ፡አራተኛው፡ለሮማንቲዔዘር፡ለልጆቹም፡ለወንድሞቹም፡ለዐሥራ፡ኹለቱ፡ወጣ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source