Skip to content
← 1 Chronicles

Chapter 24 · Amharic

1 Chronicles

1የአሮንም፡ልጆች፡ሰሞን፡ይህ፡ነው።የአሮን፡ልጆች፡ናዳብ፥አብዩድ፥አልዓዛር፥ኢታምር፡ነበሩ።

2ናዳብና፡አብዩድ፡ግን፡ልጆች፡ሳይወልዱ፡ከአባታቸው፡በፊት፡ሞቱ፤አልዓዛርና፡ኢታምርም፡ካህናት፡ኾኑ።

3ዳዊትም፡ከአልዓዛር፡ልጆች፡ከሳዶቅ፡ጋራ፥ከኢታምርም፡ልጆች፡ከአቢሜሌክ፡ጋራ፡ኾኖ፡እንደ፡ አገልግሎታቸው፡ሥርዐት፡ከፍሎ፡መደባቸው።

4የአልዓዛርም፡ልጆች፡አለቃዎች፡ከኢታምርም፡ልጆች፡አለቃዎች፡በልጠው፡ተገኙ፤እንዲህም፡ ተመደቡ፤ከአልዓዛር፡ልጆች፡እንደ፡አባቶቻቸው፡ቤቶች፡ዐሥራ፡ስድስት፥ከኢታምርም፡ልጆች፡እንደ፡ አባቶቻቸው፡ቤቶች፡ስምንት፡አለቃዎች፡ነበሩ።

5ከአልዓዛርና፡ከኢታምርም፡ልጆች፡መካከል፡የመቅደሱና፡የእግዚአብሔር፡አለቃዎች፡ነበሩና፥እነዚህና፡ እነዚያ፡እንዲህ፡በዕጣ፡ተመደቡ።

6ከሌዋውያንም፡ወገን፡የነበረው፡የናትናኤል፡ልጅ፡ጸሓፊው፡ሸማያ፡በንጉሡና፡በአለቃዎቹ፡ፊት፥በካህኑ፡ በሳዶቅና፡በአብያታርም፡ልጅ፡በአቢሜሌክ፡ፊት፥በካህናቱና፡በሌዋውያኑ፡አባቶች፡ቤቶች፡አለቃዎች፡ፊት፡ ጻፋቸው፤አንዱንም፡የአባት፡ቤት፡ለአልዓዛር፥አንዱንም፡ለኢታምር፡ጻፈ።

7መዠመሪያውም፡ዕጣ፡ለዮአሪብ፡ወጣ፥ኹለተኛው፡ለዮዳዔ ፥

8ሦስተኛው፡ለካሪም፥

9አራተኛው፡ለሥዖሪም፥ዐምስተኛው፡ለመልክያ፥

10ስድስተኛው፡ለሚያሚን፥ሰባተኛው፡ለአቆስ፥

11ስምንተኛው፡ለአብያ፥ዘጠነኛው፡ለኢያሱ፥ 229ዕብ.፥ይዳዕያህ፡(ይዳዕ፡እግዚእ•ጌታ፡ዐወቀ)። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

12ዐሥረኛው፡ለሴኬንያ፥ዐሥራ፡አንደኛው፡ለኤልያሴብ፥ዐሥራ፡ኹለተኛው፡ለያቂም፥

13ዐሥራ፡ሦስተኛው፡ለኦፓ፥ዐሥራ፡አራተኛው፡ለየሼብአብ፥

14ዐሥራ፡ዐምስተኛው፡ለቢልጋ፥ዐሥራ፡ስድስተኛው፡ለኢሜር፥

15ዐሥራ፡ሰባተኛው፡ለኤዚር፥ዐሥራ፡ስምንተኛው፡ለሃፊጼጽ፥

16ዐሥራ፡ዘጠነኛው፡ለፈታያ፥

17ኻያኛው፡ለኤዜቄል፥ኻያ፡አንደኛው፡ለያኪን፥ኻያ፡ኹለተኛው፡ለጋሙል፥

18ኻያ፡ሦስተኛው፡ለድላያ፥ኻያ፡አራተኛው፡ለመዓዝያ።

19የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዳዘዘ፥አባታቸው፡አሮን፡እንደ፡ሰጣቸው፡ሥርዐት፡ ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡የሚገቡበት፡የአገልግሎታቸው፡ሥርዐት፡ይህ፡ነበረ።

20ከቀሩትም፡የሌዊ፡ልጆች፤ከዕምበረም፡ልጆች፡ሱባኤል፤ከሱባኤል፡ልጆች፡ዬሕድያ፤

22ከረዓብያ፡ልጆች፡አለቃው፡ይሺያ፤ከይስዓራውያን፡ሰሎሚት፤ከሰሎሚት፡ልጆች፡ያሐት፤

23ከኬብሮንም፡ልጆች፡አለቃው፡ይሪያ፥ኹለተኛው፡አማርያ፥ሦስተኛው፡የሕዚኤል፥አራተኛው፡ይቀምዓም፤

24የዑዝኤል፡ልጅ፡ሚካ፤

25የሚካ፡ልጅ፡ሻሚር፤የሚካ፡ወንድም፡ይሺያ፤

26ከይሺያ፡ልጆች፡ዘካርያስ፤የሜራሪ፡ልጆች፡ሞሖሊ፥ሙሲ፤ከያዝያ፡ልጅ፡በኖ፤

27የሜራሪ፡ልጆች፤ከያዝያ፡በኖ፥ሾሃም፥ዘኩር፥ዔብሪ፤

28ከሞሖሊ፡አልዓዛር፥ርሱም፡ልጆች፡አልነበሩት፤

29ከቂስ፤የቂስ፡ልጅ፡ይረሕምኤል፤የሙሲም፡ልጆች፤ሞሖሊ፥ዔዳር፥ኢያሪሙት።

30እነዚህ፡እንደ፡አባቶቻቸው፡ቤቶች፡የሌዋውያን፡ልጆች፡ነበሩ።

31እነዚህም፡ደግሞ፡በንጉሡ፡በዳዊትና፡በሳዶቅ፡በአቢሜሌክም፡በሌዋውያንና፡በካህናት፡አባቶች፡ቤቶች፡ አለቃዎች፡ፊት፥ታላቁም፡እንደ፡ታናሹ፥እንደ፡ወንድሞቻቸው፡እንደ፡አሮን፡ልጆች፡ዕጣ፡ተጣጣሉ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source