Skip to content
← 1 Kings

Chapter 1 · Amharic

1 Kings

1ንጉሡ፡ዳዊትም፡ሸመገለ፥ዕድሜውም፡በዛ፤ልብስም፡ደረቡለት፥ነገር፡ግን፥አይሞቀውም፡ነበር።

2ባሪያዎቹም፦ለጌታችን፣ለንጉሡ፡ድንግል፡ትፈለጋለች፤በንጉሡም፡ፊት፡ቆማ፡ታገልግለው፥በጌታችንም፡ በንጉሡ፡ብብት፡ተኝታ፡ታሙቀው፡አሉት።

3በእስራኤልም፡አገር፡ዅሉ፡የተዋበች፡ቈንዦ፡ፈለጉ፤ሱነማዪቱን፡አቢሳንም፡አገኙ፥ወደ፡ንጉሡም፡ ይዘዋት፡መጡ።

4ቈንዦዪቱም፡እጅግ፡ውብ፡ነበረች፤ንጉሡንም፡ትረዳውና፡ታገለግለው፡ነበር፥ንጉሡ፡ግን፡አያውቃትም፡ ነበር።

5የአጊትም፡ልጅ፡አዶንያስ፦ንጉሥ፡እኾናለኹ፡ብሎ፡ተነሣ፤ሠረገላዎችንና፡ፈረሰኛዎችን፣በፊቱም፡ የሚሮጡ፡ዐምሳ፡ሰዎች፡አዘጋጀ።

6አባቱም፡ከቶ፡በሕይወቱ፡ሳለ፦እንዲህ፡ለምን፡ታደርጋለኽ፧ብሎ፡አልተቈጣውም፡ነበር፤ርሱ፡ደግሞ፡ እጅግ፡ያማረ፡ሰው፡ነበረ፤ከአቤሴሎምም፡በዃላ፡ተወልዶ፡ነበር።

7ሤራውም፡ከጽሩያ፡ልጅ፡ከኢዮአብና፡ከካህኑ፡ከአብያታር፡ጋራ፡ነበረ፥እነርሱም፡አዶንያስን፡ተከትለው፡ ይረዱት፡ነበር።

8ነገር፡ግን፥ካህኑ፡ሳዶቅና፡የዮዳዔ፡ልጅ፡በናያስ፣ነቢዩም፡ናታን፣ሳሚም፣ሬሲም፣የዳዊትም፡ኀያላን፡ ከአዶንያስ፡ጋራ፡አልነበሩም።

9አዶንያስም፡በጎችንና፡በሬዎችን፣ፍሪዳዎችንም፡በዐይንሮጌል፡አጠገብ፡ባለችው፡በዞሔሌት፡ድንጋይ፡ዘንድ፡ ሠዋ፤የንጉሡንም፡ልጆች፡ወንድሞቹን፡ዅሉ፥የንጉሡንም፡ባሪያዎች፥የይሁዳን፡ሰዎች፡ዅሉ፡ጠራ።

10ነገር፡ግን፥ነቢዩን፡ናታንን፥በናያስንም፥ኀያላኑንም፥ወንድሙንም፡ሰሎሞንን፡አልጠራም።

11ናታንም፡የሰሎሞንን፡እናት፡ቤርሳቤሕን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገራት፦ጌታችን፡ዳዊት፡ሳያውቅ፥የአጊት፡ ልጅ፡አዶንያስ፡እንደ፡ነገሠ፡አልሰማሽምን፧

12አኹንም፡ነዪ፥የልጅሽን፡የሰሎሞንን፡ነፍስና፡የአንቺን፡ነፍስ፡እንድታድኚ፡እመክርሻለኹ።

13ኼደሽ፡ወደ፡ንጉሡ፡ወደ፡ዳዊት፡ግቢና፦ጌታዬ፡ንጉሥ፡ሆይ፥ለእኔ፡ለባሪያኽ፦ልጅሽ፡ሰሎሞን፡ ከእኔ፡በዃላ፡ይነግሣል፥በዙፋኔም፡ይቀመጣል፡ብለኽ፡አልማልኽልኝምን፧ስለ፡ምንስ፡አዶንያስ፡ ይነግሣል፧በዪው።

14እንሆ፥አንቺ፡በዚያ፡ለንጉሥ፡ስትነግሪ፥እኔ፡ከአንቺ፡በዃላ፡እገባለኹ፥ቃልሽንም፡አጸናለኹ።

15ቤርሳቤሕም፡ወደ፡ንጉሡ፡ወደ፡ዕልፍኝ፡ገባች፤ንጉሡም፡እጅግ፡ሸምግሎ፡ነበር፥ሱነማዪቱም፡አቢሳ፡ ታገለግለው፡ነበር።

16ቤርሳቤሕም፡አጐንብሳ፡ለንጉሡ፡እጅ፡ነሣች፤ንጉሡም፦ምን፡ትፈልጊያለሽ፧አለ።

17ርሷም፡አለችው፦ጌታዬ፡ሆይ፥አንተ፡ለባሪያኽ፦ልጅሽ፡ሰሎሞን፡ከእኔ፡በዃላ፡ይነግሣል፥በዙፋኔም፡ ይቀመጣል፡ብለኽ፥በአምላክኽ፡በእግዚአብሔር፡ምለኽልኛል፤

18አኹንም፥እንሆ፥አዶንያስ፡መንገሡ፡ነው፤አንተም፡ጌታዬ፡ንጉሥ፡ይህን፡አታውቅም፤ http://www.gzamargna.net

19ርሱም፡ብዙ፡በሬዎችንና፡ፍሪዳዎችን፣በጎችንም፡ሠውቷል፥የንጉሡንም፡ልጆች፡ዅሉ፣ካህኑንም፡ አብያታርን፣የሰራዊቱንም፡አለቃ፡ኢዮአብን፡ጠርቷል፤ባሪያኽን፡ሰሎሞንን፡ግን፡አልጠራውም።

20አኹንም፥ጌታዬ፡ንጉሥ፡ሆይ፥ከአንተ፡በዃላ፡በጌታዬ፡በንጉሥ፡ዙፋን፡ላይ፡የሚቀመጠውን፡ ትነግራቸው፡ዘንድ፥የእስራኤል፡ዅሉ፡ዐይን፡ይመለከትኻል።

21ይህ፡ባይኾን፥ጌታዬ፡ከአባቶችኽ፡ጋራ፡ባንቀላፋኽ፡ጊዜ፥እኔና፡ልጄ፡ሰሎሞን፥እንደ፡ኀጢአተኛዎች፡ እንቈጠራለን።

22እንሆም፥ለንጉሡ፡ስትናገር፡ነቢዩ፡ናታን፡ገባ።

23ለንጉሡም፦እንሆ፥ነቢዩ፡ናታን፡መጥቷል፡ብለው፡ነገሩት፤ርሱም፡ወደ፡ንጉሡ፡ፊት፡በገባ፡ጊዜ፡ በግንባሩ፡በምድር፡ላይ፡ተደፍቶ፡ለንጉሡ፡እጅ፡ነሣ።

24ናታንም፡አለ፦ጌታዬ፡ንጉሥ፡ሆይ፥አንተ፦ከእኔ፡በዃላ፡አዶንያስ፡ይነግሣል፥በዙፋኔም፡ላይ፡ ይቀመጣል፡ብለኻልን፧

25ርሱ፡ዛሬ፡ወርዶ፡ብዙ፡በሬዎችንና፡ፍሪዳዎችን፡በጎችንም፡ሠውቷል፥የንጉሡንም፡ልጆች፡ ዅሉ፥የሰራዊትንም፡አለቃ፡ኢዮአብን፥ካህኑንም፡አብያታርን፡ጠርቷል፤እንሆም፥በፊቱ፡እየበሉና፡ እየጠጡ፦አዶንያስ፡ሺሕ፡ዓመት፡ይንገሥ፡ይላሉ።

26ነገር፡ግን፥እኔን፡ባሪያኽን፥ካህኑንም፡ሳዶቅን፥የዮዳዔንም፡ልጅ፡በናያስን፥ባሪያኽንም፡ሰሎሞንን፡ አልጠራም።

27በእውኑ፡ይህ፡ነገር፡ከጌታዬ፡ከንጉሡ፡የተደረገ፡ነውን፧ለባሪያኽም፡ከአንተ፡በዃላ፡በጌታዬ፡በንጉሡ፡ ዙፋን፡ላይ፡የሚቀመጠውን፡አልነገርኽምን፧

28ንጉሡም፡ዳዊት፦ቤርሳቤሕን፡ጥሩልኝ፡ብሎ፡መለሰ።ወደ፡ንጉሡም፡ገባች፥በንጉሡም፡ፊት፡ቆመች።

29ንጉሡም፦ነፍሴን፡ከመከራ፡ዅሉ፡ያዳነኝ፡ሕያው፡እግዚአብሔርን!

30በእውነት፦ልጅሽ፡ሰሎሞን፡ከእኔ፡በዃላ፡ይነግሣል፥በእኔም፡ፋንታ፡በዙፋኔ፡ላይ፡ይቀመጣል፡ብዬ፡ በእስራኤል፡አምላክ፡በእግዚአብሔር፡እንደ፡ማልኹልሽ፥እንዲሁ፡ዛሬ፡በእውነት፡አደርጋለኹ፡ብሎ፡ማለ።

31ቤርሳቤሕም፡በግንባሯ፡በምድር፡ላይ፡ተደፍታ፡ለንጉሡ፡እጅ፡ነሣችና፦ጌታዬ፡ንጉሥ፡ዳዊት፡ ለዘለዓለም፡በሕይወት፡ይኑር፡አለች።

32ንጉሡም፡ዳዊት፦ካህኑን፡ሳዶቅንና፡ነቢዩን፡ናታንን፣የዮዳዔንም፡ልጅ፡በናያስን፡ጥሩልኝ፡ አለ።ወደንጉሡም፡ፊት፡ገቡ።

33ንጉሡም፡አላቸው፦የጌታችኹን፡ባሪያዎች፡ይዛችኹ፡ኺዱ፥ልጄንም፡ሰሎሞንን፡በበቅሎዬ፡ላይ፡ አስቀምጡት፥ወደ፡ግዮንም፡አውርዱት፤

34በዚያም፡ካህኑ፡ሳዶቅና፡ነቢዩ፡ናታን፡በእስራኤል፡ላይ፡ንጉሥ፡አድርገው፡ይቅቡት፤ቀንደ፡መለከትም፡ ነፍታችኹ፦ሰሎሞን፡ሺሕ፡ዓመት፡ይንገሥ፡በሉ።

35በዃላውም፡ተከትላችኹ፡ውጡ፤ርሱም፡መጥቶ፡በዙፋኔ፡ላይ፡ይቀመጥ፥በእኔም፡ፋንታ፡ ይንገሥ፤በእስራኤልና፡በይሁዳም፡ላይ፡አለቃ፡ይኾን፡ዘንድ፡አዝዣለኹ።

36የዮዳዔም፡ልጅ፡በናያስ፡መልሶ፡ለንጉሡ፡አለ፥ያበጅ፡ያድርግ፤የጌታዬም፡የንጉሥ፡አምላክ፡ይህን፡ ይናገር።

37እግዚአብሔር፡ከጌታዬ፡ከንጉሥ፡ጋራ፡እንደ፡ነበረ፡እንዲሁ፡ከሰሎሞን፡ጋራ፡ይኹን፥ዙፋኑንም፡ከጌታዬ፡ ከንጉሡ፡ዳዊት፡ዙፋን፡የበለጠ፡ያድርግ።

38ካህኑም፡ሳዶቅና፡ነቢዩ፡ናታን፣የዮዳዔም፡ልጅ፡በናያስ፣ከሊታውያንና፡ፈሊታውያንም፡ ወረዱ፥ሰሎሞንንም፡በንጉሡ፡በዳዊት፡በቅሎ፡ላይ፡አስቀምጠው፡ወደ፡ግዮን፡አመጡት። http://www.gzamargna.net

39ካህኑም፡ሳዶቅ፡ከድንኳኑ፡የቅብዓቱን፡ቀንድ፡ወስዶ፡ሰሎሞንን፡ቀባ፤ቀንደ፡መለከትም፡ነፉ፤ሕዝቡም፡ ዅሉ፦ሰሎሞን፡ሺሕ፡ዓመት፡ይንገሥ፡አሉ።

40ሕዝቡም፡ዅሉ፡ርሱን፡ተከትለው፡ወጡ፥ሕዝቡም፡ዘፈን፡ይዘፍኑ፡ነበር፥በታላቅም፡ደስታ፡ደስ፡ አላቸው፤ከጩኸታቸውም፡የተነሣ፡ምድር፡ተናወጠች።

41አዶንያስና፡ርሱም፡የጠራቸው፡ዅሉ፡መብሉና፡መጠጡ፡ተፈጽሞ፡ሳለ፡ሰሙ፤ኢዮአብም፡የቀንደ፡ መለከት፡ድምፅ፡በሰማ፡ጊዜ፦ይህ፡በከተማ፡ውስጥ፡ያለ፡የሽብር፡ድምፅ፡ምንድር፡ነው፧አለ።

42ርሱም፡ይህን፡ሲናገር፡የካህኑ፡የአብያታር፡ልጅ፡ዮናታን፡መጣ፤አዶንያስም፦አንተ፡መልካም፡ሰው፡ ነኽና፥መልካም፡ታወራልናለኽና፡ግባ፡አለ።

43ዮናታንም፡ለአዶንያስ፡እንዲህ፡ብሎ፡መለሰ፦በእውነት፡ጌታችን፡ንጉሥ፡ዳዊት፡ሰሎሞንን፡አነገሠው።

44ንጉሡም፡ከርሱ፡ጋራ፡ካህኑን፡ሳዶቅንና፡ነቢዩን፡ናታንን፡የዮዳዔንም፡ልጅ፡በናያስን፡ከሊታውያንንና፡ ፈሊታውያንንም፡ሰደደ፥በንጉሡም፡በቅሎ፡ላይ፡አስቀመጡት።

45ካህኑም፡ሳዶቅና፡ነቢዩ፡ናታን፡በግዮን፡ንጉሥ፡አድርገው፡ቀቡት፤ከዚያም፡ደስ፡ብሏቸው፡ ወጡ፥ከተማዪቱም፡አስተጋባች፤የሰማችኹትም፡ድምፅ፡ይህ፡ነው።

46ደግሞም፡ሰሎሞን፡በመንግሥቱ፡ዙፋን፡ላይ፡ተቀምጧል።

47የንጉሡም፡ባሪያዎች፡ገብተው፦እግዚአብሔር፡የሰሎሞንን፡ስም፡ከስምኽ፡ዙፋኑንም፡ከዙፋንኽ፡የበለጠ፡ ያድርግ፡ብለው፡ጌታችንን፡ንጉሡን፡ዳዊትን፡ባረኩ፤ንጉሡም፡በዐልጋው፡ላይ፡ኾኖ፡ሰገደ።

48ንጉሡም፡ደግሞ፦ዐይኔ፡እያየ፡ዛሬ፡በዙፋኔ፡ላይ፡የሚቀመጠውን፡የሰጠኝ፡የእስራኤል፡አምላክ፡ እግዚአብሔር፡ይመስገን፡አለ።

49አዶንያስም፡የጠራቸው፡ዅሉ፡ፈሩ፥ተነሥተውም፡እያንዳንዳቸው፡በየመንገዳቸው፡ኼዱ።

50አዶንያስም፡ሰሎሞንን፡ፈራ፥ተነሥቶም፡ኼደ፥የመሠዊያውንም፡ቀንድ፡ያዘ።

51ለሰሎሞንም፦እንሆ፥አዶንያስ፡ንጉሡን፡ሰሎሞንን፡ፈርቶ፦ንጉሡ፡ሰሎሞን፡ባሪያውን፡በሰይፍ፡ እንዳይገድለኝ፡ዛሬ፡ይማልልኝ፡ብሎ፡የመሠዊያውን፡ቀንድ፡ይዟል፡አሉት።

52ሰሎሞንም፦ርሱ፡አካኼዱን፡ያሳመረ፡እንደ፡ኾነ፡ከርሱ፡አንዲት፡ጠጕር፡እንኳ፡በምድር፡ላይ፡ አትወድቅም፤ነገር፡ግን፥ክፋት፡የተገኘበት፡እንደ፡ኾነ፡ይሞታል፡አለ።

53ንጉሡ፡ሰሎሞንም፡ላከ፥ከመሠዊያውም፡አወረዱት፤መጥቶም፡ለንጉሡ፡ለሰሎሞን፡እጅ፡ ነሣ፥ሰሎሞንም፦ወደ፡ቤትኽ፡ኺድ፡አለው።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source