Skip to content
← 1 Kings

Chapter 2 · Amharic

1 Kings

1ዳዊትም፡የሚሞትበት፡ቀን፡ቀረበ፤ልጁንም፡ሰሎሞንን፡እንዲህ፡ሲል፡አዘዘው።

2እኔ፡የምድሩን፡ዅሉ፡መንገድ፡እኼዳለኹ፤

3በርታ፡ሰውም፡ኹን፤የምታደርገውንና፡የምትኼድበትን፡ዅሉ፡ታከናውን፡ዘንድ፥በሙሴ፡ሕግ፡እንደ፡ ተጻፈ፡ሥርዐቱንና፡ትእዛዛቱን፡ፍርዱንና፡ምስክሩንም፡ትጠብቅ፡ዘንድ፥በመንገዱም፡ትኼድ፡ ዘንድ፥የአምላክኽን፡የእግዚአብሔርን፡ትእዛዝ፡ጠብቅ።

4ይኸውም፡ደግሞ፡እግዚአብሔር፡ስለ፡እኔ፦ልጆችኽ፡መንገዳቸውን፡ቢጠብቁ፥በፊቴም፡በፍጹም፡ ልባቸውና፡በፍጹም፡ነፍሳቸው፡በእውነት፡ቢኼዱ፡ከእስራኤል፡ዙፋን፡ሰው፡አይቈረጥብኽም፡ብሎ፡ የተናገረውን፡ቃል፡ያጸና፡ዘንድ፡ነው።

5አንተም፡ደግሞ፡የጽሩያ፡ልጅ፡ኢዮአብ፥ኹለቱን፡የእስራኤልን፡ጭፍራ፡አለቃዎች፡የኔር፡ልጅ፡አበኔርን፡ http://www.gzamargna.net የዬቴሩንም፡ልጅ፡ዐማሳይን፡ገድሎ፥በእኔ፡ላይ፡ያደረገውን፡ታውቃለኽ፤የሰልፉንም፡ደም፡በሰላም፡ አፈሰሰ፥በወገቡም፡ባለው፡ድግና፡በእግሩ፡ባለው፡ጫማ፡ንጹሕ፡ደም፡አኖረ።

6አንተም፡እንደ፡ጥበብኽ፡አድርግ፥ሽበቱንም፡በሰላም፡ወደ፡መቃብር፡አታውርደው።

7ከወንድምኽ፡ከአቤሴሎም፡ፊት፡በሸሸኹ፡ጊዜ፡ቀርበውኛልና፥ለገለዓዳዊው፡ለቤርዜሊ፡ልጆች፡መልካም፡ ቸርነት፡አድርግላቸው፥በማእድኽም፡ከሚበሉት፡መካከል፡ይኹኑ።

8እኔም፡ወደ፡መሃናይም፡በኼድኹ፡ጊዜ፡ብርቱ፡ርግማን፡የረገመኝ፡የብራቂም፡አገር፡ሰው፡የብንያማዊው፡ የጌራ፡ልጅ፡ሳሚ፥እንሆ፥ባንተ፡ዘንድ፡ነው፤ርሱ፡ግን፡ዮርዳኖስን፡በተሻገርኹ፡ጊዜ፡ሊቀበለኝ፡ ወረደ፥እኔም፦በሰይፍ፡አልገድልኽም፡ብዬ፡በእግዚአብሔር፡ምዬለታለኹ።

9አንተ፡ግን፡ጥበበኛ፡ሰው፡ነኽና፥ያለቅጣት፡አትተወው፤የምታደርግበትንም፡አንተ፡ታውቃለኽ፥ሽበቱንም፡ ከደም፡ጋራ፡ወደ፡መቃብር፡አውርድ።

10ዳዊትም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡አንቀላፋ፥በዳዊትም፡ከተማ፡ተቀበረ።

11ዳዊትም፡በእስራኤል፡ላይ፡የነገሠው፡ዘመን፡አርባ፡ዓመት፡ነበረ።በኬብሮን፡ሰባት፡ዓመት፡ ነገሠ፤በኢየሩሳሌምም፡ሠላሳ፡ሦስት፡ዓመት፡ነገሠ።

12ሰሎሞንም፡በአባቱ፡በዳዊት፡ዙፋን፡ተቀመጠ፤መንግሥቱም፡እጅግ፡ጸና።

13የአጊት፡ልጅ፡አዶንያስም፡ወደሰሎሞን፡እናት፡ወደ፡ቤርሳቤሕ፡መጣ፤ርሷም፦ወደ፡እኔ፡መምጣትኽ፡ በሰላም፡ነውን፧አለች፤

14ርሱም፦በሰላም፡ነው፡አለ።ደግሞም፦ከአንቺ፡ጋራ፡ጕዳይ፡አለኝ፡አለ፤ርሷም፦ተናገር፡አለች።

15ርሱም፦መንግሥቱ፡ለእኔ፡እንደ፡ነበረ፥እስራኤልም፡ዅሉ፡ንጉሥ፡እኾን፡ዘንድ፡ፊታቸውን፡ወደ፡እኔ፡ አድርገው፡እንደ፡ነበረ፡አንቺ፡ታውቂያለሽ፤ነገር፡ግን፥ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ኾኖለታልና፥መንግሥቱ፡ ከእኔ፡ዐልፎ፡ለወንድሜ፡ኾኗል።

16አኹንም፡አንዲት፡ልመና፡እለምንሻለኹ፤አታሳፍሪኝ፡አለ።ርሷም፦ተናገር፡አለችው።

17ርሱም፦አያሳፍርሽምና፡ሱነማዪቱን፡አቢሳን፡ይድርልኝ፡ዘንድ፡ለንጉሡ፡ለሰሎሞን፡እንድትነግሪው፡ እለምንሻለኹ፡አለ።

18ቤርሳቤሕም፦መልካም፡ነው፥ስለ፡አንተ፡ለንጉሡ፡እነግረዋለኹ፡አለች።

19ቤርሳቤሕም፡የአዶንያስን፡ነገር፡ትነግረው፡ዘንድ፡ወደ፡ንጉሡ፡ወደ፡ሰሎሞን፡ገባች፤ንጉሡም፡ ሊቀበላት፡ተነሣ፡ሳማትም፥በዙፋኑም፡ተቀመጠ፤ለንጉሡም፡እናት፡ወንበር፡አስመጣላት፥በቀኙም፡ ተቀመጠች።

20ርሷም፦አንዲት፡ታናሽ፡ልመና፡እለምንኻለኹ፤አታሳፍረኝ፡አለች።ንጉሡም፦እናቴ፡ ሆይ፥አላሳፍርሽምና፡ለምኝ፡አላት።

21ርሷም፦ሱነማዪቱ፡አቢሳ፡ለወንድምኽ፡ለአዶንያስ፡ትዳርለት፡አለች።

22ንጉሡም፡ሰሎሞን፡ለእናቱ፡መልሶ፦ሱነማዪቱን፡አቢሳን፡ለአዶንያስ፡ለምን፡ትለምኝለታለሽ፧ታላቅ፡ ወንድሜ፡ነውና፥መንግሥትን፡ደግሞ፡ለምኚለት፤ካህኑም፡አብያታርና፡የጽሩያ፡ልጅ፡ኢዮአብ፡ደግሞ፡ከርሱ፡ ጋራ፡ናቸው፡አላት።

23ንጉሡም፡ሰሎሞን፦አዶንያስ፡ይህን፡ቃል፡በሕይወቱ፡ላይ፡አለመናገሩ፡እንደ፡ኾነ፡እግዚአብሔር፡ ይህን፡ያድርግብኝ፥ይህንም፡ይጨምርብኝ።

24አኹንም፡ያጸናኝ፥በአባቴም፡በዳዊት፡ዙፋን፡ላይ፡ያስቀመጠኝ፥እንደ፡ተናገረውም፡ቤትን፡የሠራልኝ፡ ሕያው፡እግዚአብሔርን! ዛሬ፡አዶንያስ፡ፈጽሞ፡ይገደላል፡ብሎ፡በእግዚአብሔር፡ማለ።

25ንጉሡም፡ሰሎሞን፡የዮዳዔን፡ልጅ፡በናያስን፡ላከ፤ርሱም፡ወደቀበት፥ሞተም። http://www.gzamargna.net

26ንጉሡም፡ካህኑን፡አብያታርን፦አንተ፡ዛሬ፡የሞት፡ሰው፡ነበርኽ፤ነገር፡ግን፥የአምላክን፡ የእግዚአብሔርን፡ታቦት፡በአባቴ፡በዳዊት፡ፊት፡ስለ፡ተሸከምኽ፥አባቴም፡የተቀበለውን፡መከራ፡ዅሉ፡አንተ፡ ስለ፡ተቀበልኽ፡አልገድልኽምና፡በዐናቶት፡ወዳለው፡ወደ፡ዕርሻኽ፡ኺድ፡አለው።

27በሴሎም፡በዔሊ፡ቤት፡ላይ፡የተናገረው፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ይፈጸም፡ዘንድ፡ሰሎሞን፡አብያታርን፡ ከእግዚአብሔር፡ክህነት፡አወጣው።

28ለኢዮአብም፡ወሬ፡ደረሰለት፤ኢዮአብም፡አቤሴሎምን፡አልተከተለም፡ነበር፡እንጂ፡አዶንያስን፡ተከትሎ፡ ነበር።ኢዮአብም፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ድንኳን፡ሸሽቶ፡የመሠዊያውን፡ቀንድ፡ያዘ።

29ንጉሡም፡ሰሎሞን፡ኢዮአብ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ድንኳን፡ሸሽቶ፡መሠዊያውን፡እንደ፡ያዘ፡ ሰማ፤ሰሎሞንም፡የዮዳዔን፡ልጅ፡በናያስን፥ኺድ፡ውደቅበት፡ብሎ፡አዘዘው።

30በናያስም፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ድንኳን፡መጥቶ፦ንጉሡ፦ውጣ፡ይልኻል፡አለው፤ርሱም፦በዚህ፡ እሞታለኹ፡እንጂ፡አልወጣም፡አለ።በናያስም፦ኢዮአብ፡የተናገረው፡ቃል፡የመለሰልኝም፡እንዲህ፡ነው፡ብሎ፡ ወደ፡ንጉሡ፡ወሬ፡አመጣ።

31ንጉሡም፡አለው፦እንደ፡ነገረኽ፡አድርግ፤ኢዮአብም፡በከንቱ፡ያፈሰሰውን፡ደም፡ከእኔና፡ከአባቴ፡ቤት፡ ታርቅ፡ዘንድ፡ገድለኽ፡ቅበረው።

32አባቴ፡ዳዊት፡ሳያውቅ፡ከርሱ፡የሚሻሉትን፡ኹለቱን፡ጻድቃን፡ሰዎች፥የእስራኤልን፡ሰራዊት፡አለቃ፡ የኔርን፡ልጅ፡አበኔርን፥የይሁዳንም፡ሰራዊት፡አለቃ፡የዬቴርን፡ልጅ፡ዐማሳይን፥በሰይፍ፡ ገድሏልና፥እግዚአብሔር፡ደሙን፡በራሱ፡ላይ፡ይመልሰው።

33ደማቸውም፡በኢዮአብ፡ራስና፡በዘሩ፡ራስ፡ላይ፡ለዘለዓለም፡ይመለስ፤ለዳዊት፡ግን፡ለዘሩና፡ለቤቱ፡ ለዙፋኑም፡የእግዚአብሔር፡ሰላም፡ለዘለዓለም፡ይኹን።

34የዮዳዔም፡ልጅ፡በናያስ፡ወጥቶ፡ወደቀበት፡ገደለውም፤በምድረ፡በዳም፡ባለው፡በቤቱ፡ተቀበረ።

35ንጉሡም፡በርሱ፡ፋንታ፡የዮዳዔን፡ልጅ፡በናያስን፡የሰራዊቱ፡አለቃ፡አደረገ፤በአብያታርም፡ፋንታ፡ካህኑን፡ ሳዶቅን፡አደረገ።

36ንጉሡም፡ልኮ፡ሳሚን፡አስጠራውና።በኢየሩሳሌም፡ቤት፡ሠርተኽ፡ተቀመጥ፥ወዲህና፡ወዲያም፡ አትውጣ።

37በወጣኽበትም፡ቀን፥የቄድሮንንም፡ፈፋ፡በተሻገርኽበት፡ቀን፡ፈጽመኽ፡እንድትሞት፡ዕወቅ፤ደምኽ፡ በራስኽ፡ላይ፡ይኾናል፡አለው።

38ሳሚም፡ንጉሡን፦ነገሩ፡መልካም፡ነው፤ጌታዬ፡ንጉሥ፡እንደ፡ተናገረ፡ባሪያኽ፡እንዲሁ፡ያደርጋል፡ አለው፤ሳሚም፡በኢየሩሳሌም፡ብዙ፡ቀን፡ተቀመጠ።

39ከሦስት፡ዓመትም፡በዃላ፡ከሳሚ፡ባሪያዎች፡ኹለቱ፡ወደጌት፡ንጉሥ፡ወደመዓካ፡ልጅ፡ወደ፡አንኩስ፡ ኰበለሉ፤ሳሚንም፦እንሆ፥ባሪያዎችኽ፡በጌት፡ናቸው፡ብለው፡ነገሩት።

40ሳሚም፡ተነሣ፥አህያውንም፡ጭኖ፡ባሪያዎቹን፡ይሻ፡ዘንድ፡ወደ፡ጌት፡ወደ፡አንኩስ፡ዘንድ፡ ኼደ፤ሳሚም፡ኼዶ፡ባሪያዎቹን፡ከጌት፡አመጣ።

41ሰሎሞንም፡ሳሚ፡ከኢየሩሳሌም፡ወደ፡ጌት፡ኼዶ፡እንደ፡ተመለሰ፡ሰማ።

42ንጉሡም፡ልኮ፡ሳሚን፡አስጠራና።ወዲህና፡ወዲያ፡ለመኼድ፡በወጣኽ፡ቀን፡ፈጽመኽ፡እንድትሞት፡ ዕወቅ፡ብዬ፡በእግዚአብሔር፡አላስማልኹኽምን፧ወይስ፡አላስመሰከርኹብኽምን፧አንተም፦ቃሉ፡መልካም፡ ነው፥ሰምቻለኹ፡አልኸኝ።

43የእግዚአብሔርን፡መሐላ፡እኔስ፡ያዘዝኹኽን፡ትእዛዝ፡ስለ፡ምን፡አልጠበቅኽም፧አለው።

44ንጉሡም፡ደግሞ፡ሳሚን፦አንተ፡በአባቴ፡በዳዊት፡ላይ፡የሠራኸውን፡ልብኽም፡ያሰበውን፡ክፋት፡ዅሉ፡ http://www.gzamargna.net ታውቃለኽ፤እግዚአብሔርም፡ክፋትኽን፡በራስኽ፡ላይ፡ይመልሳል።

45ንጉሡ፡ሰሎሞን፡ግን፡የተባረከ፡ይኾናል፥የዳዊትም፡ዙፋን፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ለዘለዓለም፡ይጸናል፡ አለው።

46ንጉሡም፡የዮዳዔን፡ልጅ፡በናያስን፡አዘዘው፥ወጥቶም፡ወደቀበት፥ሞተም።መንግሥትም፡በሰሎሞን፡እጅ፡ ጸና።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source