Skip to content
← 1 Kings

Chapter 22 · Amharic

1 Kings

1ሶርያና፡እስራኤልም፡ሳይዋጉ፡ሦስት፡ዓመት፡ተቀመጡ።

2በሦስተኛውም፡ዓመት፡የይሁዳ፡ንጉሥ፡ኢዮሳፍጥ፡ወደእስራኤል፡ንጉሥ፡ወረደ።

3የእስራኤልም፡ንጉሥ፡ባሪያዎቹን፦ሬማት፡ዘገለዓድ፡የእኛ፡እንደ፡ኾነች፥እኛም፡ከሶርያ፡ንጉሥ፡እጅ፡ ሳንወስዳት፡ዝም፡እንዳልን፡ታውቃላችኹን፧አላቸው።

4ኢዮሳፍጥንም፦በሬማት፡ዘገለዓድ፡እንዋጋ፡ዘንድ፡ከእኔ፡ጋራ፡ትመጣለኽን፧አለው።ኢዮሳፍጥም፡ የእስራኤልን፡ንጉሥ፦እኔ፡እንደ፡አንተ፥ሕዝቤም፡እንደ፡ሕዝብኽ፥ፈረሶቼም፡እንደ፡ፈረሶችኽ፡ናቸው፡ አለው።

5ኢዮሳፍጥም፡የእስራኤልን፡ንጉሥ፦የእግዚአብሔርን፡ቃል፡አስቀድመኽ፡ትጠይቅ፡ዘንድ፡እለምንኻለኹ፡ አለው።

6የእስራኤልም፡ንጉሥ፡ነቢያቱን፡አራት፡መቶ፡የሚያኽሉትን፡ሰዎች፡ሰብስቦ፦ወደ፡ሬማት፡ዘገለዓድ፡ ለሰልፍ፡ልኺድን፧ወይስ፡ልቅር፧አላቸው።እነርሱም፦እግዚአብሔር፡በንጉሥ፡እጅ፡አሳልፎ፡ ይሰጣታልና፥ውጣ፡አሉት።

7ኢዮሳፍጥ፡ግን፦እንጠይቀው፡ዘንድ፡ሌላ፡የእግዚአብሔር፡ነቢይ፡በዚህ፡አይገኝምን፧አለ።

8የእስራኤልም፡ንጉሥ፡ኢዮሳፍጥን፦እግዚአብሔርን፡የምንጠይቅበት፡የይምላ፡ልጅ፡ሚክያስ ፡የሚባል፡ አንድ፡ሰው፡አለ፤ነገር፡ግን፥ክፉ፡እንጂ፡መልካም፡ትንቢት፡አይናገርልኝምና፡እጠላዋለኹ፡ አለው።ኢዮሳፍጥም፦ንጉሥ፡እንዲህ፡አይበል፡አለ።

9የእስራኤልም፡ንጉሥ፡አንዱን፡ጃን፡ደረባ፡ጠርቶ፦የይምላን፡ልጅ፡ሚክያስን፡ፈጥነኽ፡አምጣ፡አለው።

10የእስራኤል፡ንጉሥና፡የይሁዳ፡ንጉሥ፡ኢዮሳፍጥ፡ልብሰ፡መንግሥት፡ለብሰው፡በሰማርያ፡በር፡መግቢያ፡ አጠገብ፡በአደባባይ፡በዙፋኖቻቸው፡ላይ፡ተቀምጠው፡ነበር፤ነቢያቱም፡ዅሉ፡በፊታቸው፡ትንቢት፡ይናገሩ፡ ነበር።

11የክንዓና፡ልጅ፡ሴዴቅያስም፡የብረት፡ቀንዶች፡ሠርቶ፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እስኪጠፉ፡ድረስ፡ በእነዚህ፡ሶርያውያንን፡ትወጋለኽ፡አለ።

12ነቢያትም፡ዅሉ፦እግዚአብሔር፡በንጉሡ፡እጅ፡አሳልፎ፡ይሰጣታልና፥ወደ፡ሬማት፡ዘገለዓድ፡ኺድና፡ ተከናወን፡እያሉ፡እንዲህ፡ትንቢት፡ይናገሩ፡ነበር።

13ሚክያስንም፡ሊጠራ፡የኼደ፡መልእክተኛ፦እንሆ፥ነቢያት፡ዅሉ፡ባንድ፡አፍ፡ኾነው፡ለንጉሡ፡ መልካምን፡ይናገራሉ፤ቃልኽም፡እንደ፡ቃላቸው፡እንዲኾን፡መልካም፡እንድትናገር፡እለምንኻለኹ፡አለው።

14ሚክያስም፦ሕያው፡እግዚአብሔርን! እግዚአብሔር፡የሚነግረኝን፡ርሱን፡እናገራለኹ፡አለ።

15ወደ፡ንጉሡም፡በመጣ፡ጊዜ፡ንጉሡ፦ሚክያስ፡ሆይ፥ወደ፡ሬማት፡ዘገለዓድ፡ለሰልፍ፡ እንኺድን፧ወይስ፡እንቅር፧አለው፤ርሱም፦ውጣና፡ተከናወን፤እግዚአብሔርም፡በንጉሡ፡እጅ፡አሳልፎ፡ ይሰጣታል፡ብሎ፡መለሰለት።

16ንጉሡም፦ከእውነት፡በቀር፡በእግዚአብሔር፡ስም፡እንዳትነግረኝ፡ስንት፡ጊዜ፡አምልኻለኹ፧አለው።

17ርሱም፦እስራኤል፡ዅሉ፡ጠባቂ፡እንደሌላቸው፡በጎች፡በተራራዎች፡ላይ፡ተበትነው፡ 166 ዕብ.፥ሚከያህ፡(ማን፡እንደ፡እግዚአብሔር፧)። http://www.gzamargna.net አየኹ፤እግዚአብሔርም፦ለእነዚህ፡ጌታ፡የላቸውም፡እያንዳንዱም፡በሰላም፡ወደ፡ቤቱ፡ይመለስ፡አለ፡ብሎ፡ ተናገረ።

18የእስራኤልም፡ንጉሥ፡ኢዮሳፍጥን፦ክፉ፡እንጂ፡መልካም፡እንደማይናገርልኝ፡አላልኹኽምን፧አለው።

19ሚክያስም፡አለ፦እንግዲህ፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስማ፤እግዚአብሔር፡በዙፋኑ፡ተቀምጦ፥የሰማይም፡ ሰራዊት፡ዅሉ፡በቀኙና፡በግራው፡ቆመው፡አየኹ።

20እግዚአብሔርም፦ወጥቶ፡በሬማት፡ዘገለዓድ፡ይወድቅ፡ዘንድ፡አክአብን፡የሚያሳስት፡ማን፡ ነው፧አለ።አንዱም፡እንዲህ፡ያለ፡ነገር፥ሌላውም፡እንዲያ፡የለ፡ነገር፡ተናገረ።

21መንፈስም፡ወጣ፡በእግዚአብሔርም፡ፊት፡ቆሞ፦እኔ፡አሳስተዋለኹ፡አለ።

22እግዚአብሔርም፦በምን፧አለው፤ርሱም፦ወጥቼ፡በነቢያቱ፡ዅሉ፡አፍ፡ሐሰተኛ፡መንፈስ፡እኾናለኹ፡ አለ።እግዚአብሔርም፦ማሳሳትስ፡ታሳስተዋለኽ፥ይኾንልኻልም፤ውጣ፥እንዲሁም፡አድርግ፡አለ።

23አኹንም፦እንሆ፥እግዚአብሔር፡በእነዚህ፡በነቢያትኽ፡ዅሉ፡አፍ፡ሐሰተኛ፡መንፈስ፡ አድርጓል፤እግዚአብሔርም፡በላይኽ፡ክፉ፡ተናግሮብኻል።

24የክንዓናም፡ልጅ፡ሴዴቅያስ፡ቀረበ፥ሚክያስንም፡ጕንጩን፡በጥፊ፡መታውና።አንተን፡ሊናገር፡ የእግዚአብሔር፡መንፈስ፡በምን፡መንገድ፡ከእኔ፡ዐለፈ፧አለ።

25ሚክያስም፦እንሆ፥በዚያ፡ቀን፡ልትሸሸግ፡ወደ፡ዕልፍኝኽ፡በኼድኽ፡ጊዜ፡ታያለኽ፡አለ።

26የእስራኤልም፡ንጉሥ፦ሚክያስን፡ውሰዱ፥ወደከተማዪቱም፡ሹም፡ወደ፡ዐሞን፡ወደንጉሡም፡ልጅ፡ወደ፡ ኢዮአስ፡መልሳችኹ፦ንጉሡ፡እንዲህ፡ይላል፦

27በደኅና፡እስክመለስ፡ድረስ፡ይህን፡ሰው፡በግዞት፡አኑሩት፥የመከራም፡እንጀራ፡መግቡት፥የመከራም፡ ውሃ፡አጠጡት፡በሉ፡አለ።

28ሚክያስም፦በደኅና፡ብትመለስ፡እግዚአብሔር፡በእኔ፡የተናገረ፡አይደለም፡አለ።ደግሞም፦አሕዛብ፡ ዅሉ፡ሆይ፥ስሙኝ፡አለ።

29የእስራኤልም፡ንጉሥና፡የይሁዳ፡ንጉሥ፡ኢዮሳፍጥ፡ወደ፡ሬማት፡ዘገለዓድ፡ወጡ።

30የእስራኤልም፡ንጉሥ፡ኢዮሳፍጥን፦ልብሴን፡ለውጬ፡ወደ፡ሰልፍ፡እገባለኹ፤አንተ፡ግን፡ልብስኽን፡ ልበስ፡አለው።የእስራኤልም፡ንጉሥ፡ልብሱን፡ለውጦ፡ወደ፡ሰልፍ፡ገባ።

31የሶርያም፡ንጉሥ፡ሠላሳ፡ኹለቱን፡የሠረገላዎች፡አለቃዎች፦ከእስራኤል፡ንጉሥ፡በቀር፥ታናሽ፡ቢኾን፡ ወይም፡ታላቅ፡ከማናቸውም፡ጋራ፡አትግጠሙ፡ብሎ፡አዞ፟፡ነበር።

32የሠረገላዎች፡አለቃዎችም፡ኢዮሳፍጥን፡ባዩ፡ጊዜ፦በእውነት፡የእስራኤል፡ንጉሥ፡ነው፡ አሉ፤ይገጥሙትም፡ዘንድ፡ከበቡት፤ኢዮሳፍጥም፡ጮኸ።

33የሠረገላዎች፡አለቃዎችም፡የእስራኤል፡ንጉሥ፡እንዳልኾነ፡ባዩ፡ጊዜ፡ርሱን፡ከማሳደድ፡ተመለሱ።

34አንድ፡ሰውም፡ቀስቱን፡ድንገት፡ገትሮ፡የእስራኤልን፡ንጉሥ፡በጥሩሩ፡ልብስ፡መጋጠሚያ፡በኩል፡ ወጋው፤ሠረገለኛውንም፦መልሰኽ፡ንዳ፥ተወግቻለኹና፡ከሰልፍ፡ውስጥ፡አውጣኝ፡አለው።

35በዚያም፡ቀን፡ሰልፍ፡በረታ፤ንጉሡም፡በሶርያውያን፡ፊት፡በሠረገላው፡ላይ፡ተደግፎ፡ነበር፥ማታም፡ ሞተ፤የቍስሉም፡ደም፡በሠረገላው፡ውስጥ፡ፈሰሰ።

36በሰራዊቱም፡መካከል፡ፀሓይ፡ስትገባ፦ንጉሡ፡ሞቷልና፥እያንዳንዱ፡ወደ፡ከተማው፥እያንዳንዱም፡ወደ፡ አገሩ፡ይኺድ፡የሚል፡ጩኸት፡ኾነ።

37ወደ፡ሰማርያም፡መጡ፥ንጉሡንም፡በሰማርያ፡ቀበሩት።

38አመንዝራዎች፡በታጠቡባት፡በሰማርያ፡ኵሬ፡ሠረገላውን፡ዐጠቡት፥እግዚአብሔርም፡እንደተናገረው፡ቃል፡ http://www.gzamargna.net ውሻዎች፡ደሙን፡ላሱት።

39የቀረውም፡የአክአብ፡ነገር፥ያደረገውም፡ዅሉ፥ከዝኆን፡ጥርስም፡የሠራው፡ቤት፥የሠራቸውም፡ ከተማዎች፡ዅሉ፥በእስራኤል፡ነገሥታት፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡የተጻፈ፡አይደለምን፧

40አክአብም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡አንቀላፋ፥በርሱም፡ፋንታ፡ልጁ፡አካዝያስ ፡ነገሠ።

41አክአብም፡በነገሠ፡በአራተኛው፡ዓመት፡የአሣ፡ልጅ፡ኢዮሳፍጥ፡በይሁዳ፡ላይ፡ነገሠ።

42ኢዮሳፍጥ፡መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡የሠላሳ፡ዐምስት፡ዓመት፡ጐበዝ፡ነበረ፤በኢየሩሳሌምም፡ኻያ፡ ዐምስት፡ዓመት፡ነገሠ።እናቱም፡ዓዙባ፡የተባለች፡የሺልሒ፡ልጅ፡ነበረች።

43በአባቱም፡በአሣ፡መንገድ፡ዅሉ፡ኼደ፥ከርሱም፡ፈቀቅ፡አላለም፥በእግዚአብሔርም፡ፊት፡ቅን፡ አደረገ፤ነገር፡ግን፥በኰረብታዎች፡ላይ፡ያሉትን፡መስገጃዎች፡አላራቀም፤ሕዝቡ፡ገና፡በኰረብታዎቹ፡ላይ፡ ባሉት፡መስገጃዎች፡ይሠዋና፡ያጥን፡ነበር።

44ኢዮሳፍጥም፡ከእስራኤል፡ንጉሥ፡ጋራ፡ታረቀ።

45የቀረውም፡የኢዮሳፍጥ፡ነገር፥የሠራውም፡ጭከና፥እንዴትም፡እንደ፡ተወጋ፥በይሁዳ፡ነገሥታት፡ታሪክ፡ መጽሐፍ፡የተጻፈ፡አይደለምን፧

46ከአባቱ፡ከአሣ፡ዘመን፡የተረፉትን፡ሰዶማውያን፡ከምድር፡አጠፋ።

47በኤዶምያስም፡ንጉሥ፡አልነበረም፤ሹሙም፡እንደ፡ንጉሥ፡ነበረ።

48ኢዮሳፍጥም፡ወደ፡ኦፊር፡ኼደው፡ወርቅ፡ያመጡ፡ዘንድ፡የተርሴስን፡መርከቦች፡ሠራ፤ነገር፡ ግን፥መርከቦቹ፡በዔጽዮንጋብር፡ተሰበሩ፡እንጂ፡አልኼዱም።

49የአክአብም፡ልጅ፡አካዝያስ፡ኢዮሳፍጥን፦ባሪያዎቼ፡ከባሪያዎችኽ፡ጋራ፡በመርከብ፡ይኺዱ፡ አለው፤ኢዮሳፍጥ፡ግን፡አልወደደም።

50ኢዮሳፍጥም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡አንቀላፋ፥በአባቱም፡በዳዊት፡ከተማ፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡ተቀበረ፤በርሱም፡ ፋንታ፡ልጁ፡ኢዮራም ፡ነገሠ።

51በይሁዳም፡ንጉሥ፡በኢዮሳፍጥ፡በዐሥራ፡ሰባተኛው፡ዓመት፡የአክአብ፡ልጅ፡አካዝያስ፡በእስራኤል፡ላይ፡ በሰማርያ፡መንገሥ፡ዠመረ፤በእስራኤልም፡ላይ፡ኹለት፡ዓመት፡ነገሠ።

52በእግዚአብሔርም፡ፊት፡ክፉ፡አደረገ፥በአባቱና፡በእናቱም፡መንገድ፥እስራኤልንም፡ባሳተው፡በናባጥ፡ ልጅ፡በኢዮርብዓም፡መንገድ፡ኼደ።

53በዓልንም፡አመለከ፡ሰገደለትም፤አባቱም፡እንዳደረገ፡ዅሉ፡የእስራኤልን፡አምላክ፡እግዚአብሔርን፡ አስቈጣ፨ 167 ዕብ.፥አኀዝያህ። 168 ዕብ.፥የውራም። http://www.gzamargna.net

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source