1የሶርያም፡ንጉሥ፡ወልደ፡አዴር፡ጭፍራውን፡ዅሉ፡ሰበሰበ፤ከርሱም፡ጋራ፡ሠላሳ፡ኹለት፡ነገሥት፡ ነበሩ፥ፈረሶችና፡ሠረገላዎችም፡ነበሩ፤ወጥቶም፡ሰማርያን፡ከበበ፥ወጋትም።
2ወደእስራኤልም፡ንጉሥ፡ወደ፡አክአብ።
3ወልደ፡አዴር፡እንዲህ፡ይላል፦ብርኽና፡ወርቅኽ፡ለእኔ፡ነው፤ሴቶችኽና፡መልካካሞቹም፡ልጆችኽ፡ለእኔ፡ ናቸው፡ብሎ፡ወደ፡ከተማዪቱ፡መልእክተኛዎችን፡ላከ። http://www.gzamargna.net
4የእስራኤልም፡ንጉሥ፡መልሶ፦ጌታዬ፡ንጉሥ፡ሆይ፥አንተ፡እንዳልኽ፡ነው፤እኔ፡ለኔም፡የኾነው፡ዅሉ፡ የአንተ፡ነው፡አለ።
5ደግሞም፡መልእክተኛዎች፡ተመልሰው፦ወልደ፡አዴር፡እንዲህ፡ይላል፦ቀድሞ፡ብርኽንና፡ወርቅኽን፡ ሴቶችኽንና፡ልጆችኽንም፡ትሰጠኛለኽ፡ብዬ፡ልኬብኽ፡ነበር፤
6ነገም፡በዚህ፡ጊዜ፡ባሪያዎቼን፡እልክብኻለኹ፥ቤትኽንም፡የባሪያዎችኽንም፡ቤቶች፡ይበረብራሉ፤ደስ፡ የሚያሠኛቸውንም፡ዅሉ፡በእጃቸው፡አድርገው፡ይወስዳሉ፡አሉ።
7የእስራኤልም፡ንጉሥ፡የአገሩን፡ሽማግሌዎች፡ዅሉ፡ጠርቶ፦ተመልከቱ፥ይህም፡ሰው፡ክፉ፡እንዲሻ፡ እዩ፤ስለ፡ሴቶቼ፡ስለ፡ልጆቼ፡ስለ፡ብሬና፡ወርቄም፡ላከብኝ፥እንቢም፡አላልኹም፡አለ።
8ሽማግሌዎችም፡ዅሉ፡ሕዝቡም፡ዅሉ፦አትስማው፥ዕሺም፡አትበለው፡አሉት።
9ለወልደ፡አዴርም፡መልእክተኛዎች፦ለጌታዬ፡ለንጉሥ፦ለእኔ፡ለባሪያኽ፡በመዠመሪያ፡የላክኽብኝን፡ ዅሉ፡አደርጋለኹ፤ይህን፡ግን፡ኣደርገው፡ዘንድ፡አይቻለኝም፡በሉት፡አላቸው።መልእክተኛዎችም፡ተመልሰው፡ ይህን፡አወሩለት።
10ወልደ፡አዴርም፦ለሚከተለኝ፡ሕዝብ፡የሰማርያ፡ትቢያ፡ጭብ፟ጥ፡ጭብ፟ጥ፡ይበቃው፡እንደ፡ ኾነ፥አማልክት፡ይህን፡ያድርጉብኝ፡ይህን፡ይጨምሩብኝ፡ብሎ፡ላከበት።
11የእስራኤልም፡ንጉሥ፡መልሶ፦በቃ፤ለሰልፍ፡የሚታጠቅ፡ጋሻ፡ጦሩን፡እንደሚያወልቅ፡አይመካ፡አለው።
12ወልደ፡አዴርም፡ያን፡ነገር፡በሰማ፡ጊዜ፡ከነገሥታቱ፡ጋራ፡በድንኳኑ፡ውስጥ፡ይጠጣ፡ ነበር፤ባሪያዎቹንም፦ተሰለፉ፡አላቸው፤እነርሱም፡በከተማዪቱ፡ትይዩ፡ተሰለፉ።
13እንሆም፥ነቢይ፡ወደእስራኤል፡ንጉሥ፡ወደ፡አክአብ፡ቀርቦ፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ይህን፡ብዙ፡ ጭፍራ፡ዅሉ፡ታያለኽን፧እንሆ፥ዛሬ፡በእጅኽ፡አሳልፌ፡እሰጠዋለኹ፥እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ ታውቃለኽ፡አለ።
14አክአብም፦በማን፧አለ፤ርሱም፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በአውራጃዎቹ፡አለቃዎች፡ ጕልማሳዎች፥አለ፤ርሱም፦ሰልፉን፡ማን፡ይዠምራል፧አለ፤ርሱም፦አንተ፡አለው።
15የአውራጃዎቹንም፡አለቃዎች፡ጕልማሳዎች፡ቈጠረ፥ኹለት፡መቶም፡ሠላሳ፡ኹለት፡ነበሩ፤ከነርሱም፡ በዃላ፡ሕዝቡን፡ዅሉ፥የእስራኤልን፡ልጆች፡ዅሉ፥ቈጠረ፥ሰባትም፡ሺሕ፡ነበሩ።
16ቀትርም፡በኾነ፡ጊዜ፡ወጡ፤ወልደ፡አዴር፡ረዳቶቹም፡ሠላሳ፡ኹለቱ፡ነገሥታት፡እየጠጡ፡በድንኳን፡ ውስጥ፡ይሰክሩ፡ነበር።
17የአውራጃዎቹም፡አለቃዎች፡ጕልማሳዎች፡አስቀድመው፡ወጡ፤ወልደ፡አዴርም፡መልእክተኛዎችን፡ ላከ፥እነርሱም፦ሰዎች፡ከሰማርያ፡ወጥተዋል፡ብለው፡ነገሩት።
18ርሱም፦ለዕርቅ፡ወይም፡ለሰልፍ፡መጥተው፡እንደ፡ኾነ፡በሕይወታቸው፡ያዟቸው፥አለ።
19እነዚህም፡የአውራጃዎች፡አለቃዎች፡ጕልማሳዎች፡ከከተማዪቱ፡ወጡ፥ሰራዊትም፡ተከተላቸው።
20ዅሉም፡በያንዳንዱ፡በፊቱ፡የነበረውን፡ሰው፡ገደለ፥ሶርያውያንም፡ሸሹ፤እስራኤልም፡ አሳደዷቸው፥የሶርያም፡ንጉሥ፡ወልደ፡አዴር፡በፈረሱ፡አመለጠ።
21የእስራኤል፡ንጉሥም፡ወጥቶ፡ፈረሶቹንና፡ሠረገላዎቹን፡ያዘ፥ሶርያውያንንም፡በታላቅ፡ውጊት፡ገደላቸው።
22ነቢዩም፡ወደእስራኤል፡ንጉሥ፡ቀርቦ፦የሶርያ፡ንጉሥ፡በሚመጣው፡ዓመት፡ ይመጣብኻልና፥ኺድ፥በርታ፥የምታደርገውንም፡ተመልከትና፡ዕወቅ፡አለው።
23የሶርያም፡ንጉሥ፡ባሪያዎች፡እንዲህ፡አሉት፦አምላካቸው፡የተራራዎች፡አምላክ፡ ነው፤ስለዚህ፥በርትተውብን፡ነበር፤ነገር፡ግን፥በሜዳ፡ላይ፡ከነርሱ፡ጋራ፡ብንዋጋ፡በርግጥ፡እንበረታባቸዋለን።
24ይህንም፡አድርግ፤ከጭፍራዎችኽ፡ነገሥታቱን፡አርቅ፥በፋንታቸውም፡አለቃዎችን፡ሹም። http://www.gzamargna.net
25አንተም፡ቀድሞ፡እንደ፡ጠፋብኽ፡ሰራዊት፥ፈረሱን፡በፈረስ፡ፋንታ፥ሠረገላውንም፡በሠረገላ፡ ፋንታ፥ሰራዊትን፡ቍጠር፤በሜዳም፡ላይ፡ከነርሱ፡ጋራ፡እንዋጋለን፥በርግጥም፡ እንበረታባቸዋለን።ምክራቸውንም፡ሰማ፥እንዲሁም፡አደረገ።ፕ፡
26በሚመጣውም፡ዓመት፡ወልደ፡አዴር፡ሶርያውያንን፡አሰለፈ፥ከእስራኤልም፡ጋራ፡ይዋጋ፡ዘንድ፡ወደ፡ አፌቅ፡ወጣ።
27የእስራኤልም፡ልጆች፡ተሰለፉ፥ሊገጥሟቸውም፡ወጡ፤የእስራኤልም፡ልጆች፡እንደ፡ኹለት፡ትናንሾች፡ የፍየል፡መንጋዎች፡ኾነው፡በፊታቸው፡ሰፈሩ፤ሶርያውያን፡ግን፡ምድሩን፡ሞልተው፡ነበር።
28የእግዚአብሔርም፡ሰው፡ቀርቦ፡የእስራኤልን፡ንጉሥ፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ ይላል፦ሶርያውያን፦እግዚአብሔር፡የተራራዎች፡አምላክ፡ነው፡እንጂ፡የሸለቆ፡አምላክ፡አይደለም፡ ብለዋልና፥ይህን፡ታላቅ፡ጭፍራ፡ዅሉ፡በእጅኽ፡አሳልፌ፡እሰጠዋለኹ፥እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ ታውቃላችኹ፡አለው።
29እነዚህም፡በእነዚያ፡ትይዩ፡ሰባት፡ቀን፡ያኽል፡ሰፈሩ፤በሰባተኛውም፡ቀን፡ተጋጠሙ፥የእስራኤልም፡ ልጆች፡ከሶርያውያን፡ባንድ፡ቀን፡መቶ፡ሺሕ፡እግረኛ፡ገደሉ።
30የቀሩትም፡ወደ፡አፌቅ፡ወደ፡ከተማዪቱ፡ውስጥ፡ሸሹ፤ቅጥሩም፡በቀሩት፡በኻያ፡ሰባት፡ሺሕ፡ሰዎች፡ ላይ፡ወደቀ።ወልደ፡አዴርም፡ሸሽቶ፡ወደ፡ከተማዪቱ፡ወደ፡ዕልፍኙ፡ውስጥ፡ገባ።
31ባሪያዎቹም፦እንሆ፥የእስራኤል፡ቤት፡ነገሥታት፡መሓሪዎች፡እንደ፡ኾኑ፡ሰምተናል፤በወገባችን፡ማቅ፡ እንታጠቅ፥በራሳችንም፡ገመድ፡እንጠምጥም፥ወደእስራኤልም፡ንጉሥ፡እንውጣ፤ምናልባት፡ነፍስኽን፡ ይምራታል፡አሉት።
32ወገባቸውንም፡በማቅ፡ታጠቁ፥በራሳቸውም፡ገመድ፡ጠመጠሙ፥ወደእስራኤልም፡ንጉሥ፡ መጥተው፦ባሪያኽ፡ወልደ፡አዴር፦ነፍሴን፡ትምራት፡ዘንድ፡እለምንኻለኹ፡ብሏል፡አሉት።ርሱም፦ገና፡ በሕይወቱ፡አለን፧ወንድሜ፡ነው፥አለ።
33ሰዎቹም፡የደግ፡ምልክት፡አደረጉትና፡ቃሉን፡ከአፉ፡ተቀብለው።ወንድምኽ፡ወልደ፡አዴር፡አለ፡ አሉት።ርሱም፦ኺዱ፥አምጡት፡አለ።ወልደ፡አዴርም፡ወደ፡ርሱ፡ወጣ፥በሠረገላውም፡ላይ፡አስቀመጠው።
34ወልደ፡አዴርም፦አባቴ፡ከአባትኽ፡የወሰዳቸውን፡ከተማዎች፡እመልስልኻለኹ፤አባቴ፡በሰማርያ፡ እንዳደረገ፡አንተ፡በደማስቆ፡ገበያ፡ታደርጋለኽ፡አለው።አክአብም፦እኔም፡በዚህ፡ቃል፡ኪዳን፡እሰድ፟ኻለኹ፡ አለ።ከርሱም፡ጋራ፡ቃል፡ኪዳን፡አድርጎ፡ሰደደው።
35ከነቢያትም፡ወገን፡አንድ፡ሰው፡በእግዚአብሔር፡ቃል፡ባልንጀራውን፦ምታኝ፡አለው።ሰውዮውም፡ ይመታው፡ዘንድ፡እንቢ፡አለ።
36ርሱም፦የእግዚአብሔርን፡ቃል፡አልሰማኽምና፥እንሆ፥ከእኔ፡በራቅኽ፡ጊዜ፡አንበሳ፡ይገድልኻል፡ አለው።ከርሱም፡በራቀ፡ጊዜ፡አንበሳ፡አግኝቶ፡ገደለው።
37ደግሞም፡ሌላ፡ሰው፡አግኝቶ፦ምታኝ፡አለው።ሰውዮውም፡መታው፥በመምታቱም፡አቈሰለው።
38ነቢዩም፡ኼዶ፡በመንገድ፡አጠገብ፡ንጉሡን፡ቈየው፤ዐይኖቹንም፡በቀጸላው፡ሸፍኖ፡ተሸሸገ።
39ንጉሡም፡ባለፈ፡ጊዜ፡ወደ፡ርሱ፡ጮኸ፦ባሪያኽ፡ወደ፡ሰልፍ፡መካከል፡ወጣ፤እንሆም፥አንድ፡ሰው፡ ፈቀቅ፡ብሎ፡ወደ፡እኔ፡አንድ፡ሰው፡አመጣና፦ይህን፡ሰው፡ጠብቅ፥ቢኰበልልም፡ነፍስኽ፡በነፍሱ፡ፋንታ፡ ትኾናለች፥ወይም፡አንድ፡መክሊት፡ብር፡ትከፍላለኽ፡አለኝ።
40ባሪያኽም፡ወዲህና፡ወዲያ፡ሲመለከት፡ጠፋ፡አለው።የእስራኤልም፡ንጉሥ፦ፍርድኽ፡እንዲሁ፡ ይኾናል፤አንተ፡ፈርደኸዋል፡አለው።
41ፈጥኖም፡ቀጸላውን፡ከዐይኑ፡አነሣ፡የእስራኤልም፡ንጉሥ፡ከነቢያት፡ወገን፡እንደ፡ኾነ፡ዐወቀው።
42ርሱም፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እኔ፡ዕርም፡ያልኹትን፡ሰው፡ከእጅኽ፡አውጥተኻልና፥ነፍስኽ፡ http://www.gzamargna.net በነፍሱ፡ፋንታ፡ሕዝብኽም፡በሕዝቡ፡ፋንታ፡ይኾናሉ፡አለው።
43የእስራኤልም፡ንጉሥ፡እየተቈጣና፡እየተናደደ፡ወደ፡ቤቱ፡ተመለሰ፥ወደ፡ሰማርያም፡መጣ።