Skip to content
← 1 Kings

Chapter 20 · Amharic

1 Kings

1ለኢይዝራኤላዊውም፡ለናቡቴ፡በሰማርያ፡ንጉሥ፡በአክአብ፡ቤት፡አጠገብ፡የወይን፡ቦታ፡ነበረው።

2አክአብም፡ናቡቴን፦በቤቴ፡አቅራቢያ፡ነውና፥የአትክልት፡ቦታ፡ኣደርገው፡ዘንድ፡የወይን፡ቦታኽን፡ ስጠኝ፤ስለ፡ርሱም፡ከርሱ፡የተሻለ፡የወይን፡ቦታ፡እሰጥኻለኹ፤ወይም፡ብትወድ፟፡ግምቱን፡ገንዘብ፡ እሰጥኻለኹ፡ብሎ፡ተናገረው።

3ናቡቴም፡አክአብን፦የአባቶቼን፡ርስት፡እሰጥኽ፡ዘንድ፡እግዚአብሔር፡ያርቅልኝ፡አለው።

4ኢይዝራኤላዊውም፡ናቡቴ፦የአባቶቼን፡ርስት፡አልሰጥኽም፡ብሎ፡ስለተናገረው፡አክአብ፡ተቈጥቶና፡ተናዶ፟፡ ወደ፡ቤቱ፡ገባ።በዐልጋውም፡ላይ፡ተጋድሞ፡ፊቱን፡ተሸፋፈነ፥እንጀራም፡አልበላም።

5ሚስቱም፡ኤልዛቤል፡ወደ፡ርሱ፡መጥታ፦ልብኽ፡የሚያዝን፡እንጀራስ፡የማትበላ፡ስለ፡ምንድር፡ ነው፧አለችው።

6ርሱም፦ኢይዝራኤላዊውን፡ናቡቴን፦የወይንኽን፡ቦታ፡በገንዘብ፡ስጠኝ፤ወይም፡ብትወድ፟፡በፋንታው፡ ሌላ፡የወይን፡ቦታ፡እሰጥኻለኹ፡ብዬ፡ተናገርኹት፤ርሱ፡ግን፦የወይን፡ቦታዬን፡አልሰጥኽም፡ብሎ፡ስለ፡ መለሰልኝ፡ነው፡አላት።

7ሚስቱም፡ኤልዛቤል።አንተ፡አኹን፡የእስራኤልን፡መንግሥት፡ትገዛለኽን፧ተነሣ፡እንጀራም፡ብላ፥ልብኽም፡ ደስ፡ይበላት፤የኢይዝራኤላዊውን፡የናቡቴን፡የወይን፡ቦታ፡እሰጥኻለኹ፡አለችው።

8በአክአብም፡ስም፡ደብዳቤ፡ጻፈች፥በማኅተሙም፡አተመችው፤በከተማው፡ወደ፡ነበሩትና፡ከናቡቴም፡ጋራ፡ ወደተቀመጡት፡ሽማግሌዎችና፡ከበርቴዎች፡ደብዳቤውን፡ላከች።

9በደብዳቤውም፦ስለ፡ጾም፡ዐዋጅ፡ንገሩ፥ናቡቴንም፡በሕዝቡ፡ፊት፡አስቀምጡት፤

10ኹለትም፡ምናምንቴ፡ሰዎች፡በፊቱ፡አስቀምጡና፦እግዚአብሔርንና፡ንጉሡን፡ሰድቧል፡ብለው፡ ይመስክሩበት፤አውጥታችኹም፡እስኪሞት፡ድረስ፡ውገሩት፡ብላ፡ጻፈች።

11በከተማውም፡የተቀመጡት፡የከተማው፡ሰዎችና፡ሽማግሌዎች፡ከበርቴዎችም፡ኤልዛቤል፡እንዳዘዘቻቸውና፡ ወደ፡እነርሱ፡በተላከው፡ደብዳቤ፡እንደ፡ተጻፈ፡እንዲሁ፡አደረጉ።

12የጾም፡ዐዋጅ፡ነገሩ፥ናቡቴንም፡በሕዝቡ፡ፊት፡አስቀመጡት።

13ኹለቱም፡ምናምንቴ፡ሰዎች፡ገብተው፡በፊቱ፡ተቀመጡ፤ምናምንቴዎቹ፡ሰዎችም፡በሕዝቡ፡ፊት።ናቡቴ፡ እግዚአብሔርንና፡ንጉሡን፡ሰድቧል፡ብለው፡በናቡቴ፡ላይ፡መሰከሩ።የዚያን፡ጊዜም፡ከከተማ፡አውጥተው፡ እስኪሞት፡ድረስ፡ወገሩት። http://www.gzamargna.net

14ወደ፡ኤልዛቤልም፦ናቡቴ፡ተወግሮ፡ሞተ፡ብለው፡ላኩ።

15ኤልዛቤልም፡ናቡቴ፡ተወግሮ፡እንደ፡ሞተ፡በሰማች፡ጊዜ፡ኤልዛቤል፡አክአብን፦ናቡቴ፡ሞቷል፡እንጂ፡ በሕይወት፡አይደለምና፡በገንዘብ፡ይሰጥኽ፡ዘንድ፡እንቢ፡ያለውን፡የኢይዝራኤላዊውን፡የናቡቴን፡የወይን፡ቦታ፡ ተነሥተኽ፡ውረስ፡አለችው።

16አክአብም፡ናቡቴ፡እንደ፡ሞተ፡በሰማ፡ጊዜ፡ይወርሰው፡ዘንድ፡ወደ፡ኢይዝራኤላዊው፡ወደናቡቴ፡ወይን፡ ቦታ፡ሊወርድ፡ተነሣ።

17የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡ቴስብያዊው፡ወደ፡ኤልያስ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦

18ተነሥተኽ፡በሰማርያ፡የሚኖረውን፡የእስራኤልን፡ንጉሥ፡አክአብን፡ትገናኝ፡ዘንድ፡ ውረድ፤እንሆ፥ይወርሰው፡ዘንድ፡በወረደበት፡በናቡቴ፡የወይን፡ቦታ፡ውስጥ፡አለ።

19አንተም፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፡ገድለኽ፡ወረስኸውን፧ብለኽ፡ ንገረው።ደግሞም፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ውሻዎች፡የናቡቴን፡ደም፡በላሱበት፡ስፍራ፡የአንተን፡ ደም፡ደግሞ፡ውሻዎች፡ይልሱታል፡ብለኽ፡ንገረው።

20አክአብም፡ኤልያስን፦ጠላቴ፡ሆይ፥አገኘኸኝን፧አለው።ርሱም፡እንዲህ፡ብሎ፡ መለሰለት፦አግኝቼኻለኹ፤በእግዚአብሔር፡ፊት፡ክፉ፡ለማድረግ፡ራስኽን፡ሽጠኻልና።

21እንሆ፥ክፉ፡ነገር፡አመጣብኻለኹ፥ፈጽሞም፡እጠርግኻለኹ፥ከአክአብም፡በእስራኤል፡ዘንድ፡የታሰረውንና፡ የተለቀቀውን፡ወንድ፡ዅሉ፡አጠፋለኹ፤

22በሥራኽም፡አስቈጥተኸኛልና፥እስራኤልንም፡አስተኻልና፥ቤትኽን፡እንደ፡ናባጥ፡ልጅ፥እንደ፡ኢዮርብዓም፡ ቤት፥እንደ፡አኪያም፡ልጅ፥እንደ፡ባኦስ፡ቤት፡አደርገዋለኹ።

23ደግሞ፡እግዚአብሔር፡ስለ፡ኤልዛቤል፦በኢይዝራኤል፡ቅጥር፡አጠገብ፡ኤልዛቤልን፡ውሻዎች፡ይበሏታል፡ ብሎ፡ተናገረ።

24ከአክአብም፡ወገን፡በከተማዪቱ፡ውስጥ፡የሞተውን፡ውሻዎች፡ይበሉታል፤በሜዳውም፡የሞተውን፡የሰማይ፡ ወፎች፡ይበሉታል።

25በእግዚአብሔር፡ፊት፡ክፋት፡ለመሥራት፡ራሱን፡እንደ፡ሸጠ፥ሚስቱም፡ኤልዛቤል፡እንደ፡ ነዳችው፥እንደ፡አክአብ፡ያለ፡ሰው፡አልነበረም።

26እግዚአብሔር፡ከእስራኤል፡ልጆች፡ፊት፡ያጠፋቸው፡አሞራውያን፡እንደ፡ሠሩት፡ዅሉ፥ጣዖታትን፡ በመከተል፡እጅግ፡ርኩስ፡ነገር፡ሠራ።

27አክአብም፡ይህን፡ቃል፡በሰማ፡ጊዜ፡ልብሱን፡ቀዶ፟፡ገላውን፡ማቅ፡አለበሰ፥ጾመም፥በማቅ፡ላይም፡ ተኛ፥ቅስስ፡ብሎም፡ኼደ።

29ደግሞም፦አክአብ፡በፊቴ፡እንደ፡ተዋረደ፡አየኽን፧በፊቴ፡የተዋረደ፡ስለ፡ኾነ፡በልጁ፡ዘመን፡ በቤቱ፡ላይ፡ክፉ፡ነገር፡አመጣለኹ፡እንጂ፡በርሱ፡ዘመን፡ክፉ፡ነገር፡አላመጣም፡የሚል፡የእግዚአብሔር፡ ቃል፡ወደ፡ቴስብያዊው፡ወደ፡ኤልያስ፡መጣ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source