Skip to content
← 1 Kings

Chapter 19 · Amharic

1 Kings

1አክአብም፡ኤልያስ፡ይህን፡ዅሉ፡እንዳደረገ፥ነቢያትንም፡ዅሉ፡በሰይፍ፡እንደ፡ገደለ፡ለኤልዛቤል፡ነገራት።

2ኤልዛቤልም፦ነገ፡በዚህ፡ጊዜ፡ነፍስኽን፡ከነዚህ፡እንደ፡አንዲቱ፡ነፍስ፡ባላደርጋት፥አማልክት፡ይህን፡ ያድርጉብኝ፡ይህንም፡ይጨምሩብኝ፡ብላ፡ወደ፡ኤልያስ፡መልእክተኛ፡ላከች።

3ኤልያስም፡ፈርቶ፡ተነሣ፥ነፍሱንም፡ሊያድን፡ኼደ፥በይሁዳም፡ወዳለው፡ወደ፡ቤርሳቤሕ፡መጥቶ፡ ብላቴናውን፡በዚያ፡ተወ።

4ርሱም፡አንድ፡ቀን፡የሚያኽል፡መንገድ፡በምድረ፡በዳ፡ኼደ፤መጥቶም፡ከክትክታ፡ዛፍ፡በታች፡ ተቀመጠና፦ይበቃኛል፤አኹንም፥አቤቱ፥እኔ፡ከአባቶቼ፡አልበልጥምና፡ነፍሴን፡ውሰድ፡ብሎ፡እንዲሞት፡ ለመነ።

5በክትክታውም፡ዛፍ፡በታች፡ተጋደመ፡እንቅልፍም፡አንቀላፋ፤እንሆም፥መልአክ፡ዳሰሰውና።ተነሥተኽ፡ ብላ፡አለው።

6ሲመለከትም፥እንሆ፥በራሱ፡አጠገብ፡የተጋገረ፡ዕንጐቻና፡በማሰሮ፡ውሃ፡አገኘ።በላም፡ ጠጣም፥ተመልሶም፡ተኛ።

7የእግዚአብሔር፡መልአክ፡ደግሞ፡ኹለተኛ፡ጊዜ፡መጥቶ፡ዳሰሰውና።የምትኼድበት፡መንገድ፡ሩቅ፡ ነውና፥ተነሥተኽ፡ብላ፡አለው።

8ተነሥቶም፡በላ፡ጠጣም፤በዚያም፡ምግብ፡ኀይል፡እስከእግዚአብሔር፡ተራራ፡እስከ፡ኰሬብ፡ድረስ፡አርባ፡ ቀንና፡አርባ፡ሌሊት፡ኼደ።

9እዚያም፡ወዳለ፡ዋሻ፡መጣ፥በዚያም፡ዐደረ፤እንሆም፦ኤልያስ፡ሆይ፥በዚህ፡ምን፡ታደርጋለኽ፧የሚል፡ የእግዚአብሔር፡ቃል፡ወደ፡ርሱ፡መጣ።

10ርሱም፦ለሰራዊት፡አምላክ፡ለእግዚአብሔር፡እጅግ፡ቀንቻለኹ፤የእስራኤል፡ልጆች፡ቃል፡ኪዳንኽን፡ ትተዋልና፥መሠዊያዎችኽንም፡አፍርሰዋልና፥ነቢያትኽንም፡በሰይፍ፡ገድለዋልና፤እኔም፡ብቻዬን፡ ቀርቻለኹ፤ነፍሴንም፡ሊወስዷት፡ይሻሉ፡አለ።

11ርሱም፦ውጣ፥በተራራውም፡ላይ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ቁም፡አለ።እንሆም፥እግዚአብሔር፡ ዐለፈ፥በእግዚአብሔርም፡ፊት፡ትልቅና፡ብርቱ፡ነፋስ፡ተራራዎቹን፡ሰነጠቀ፡አለቶቹንም፡ሰባበረ፥እግዚአብሔር፡ ግን፡በነፋሱ፡ውስጥ፡አልነበረም።ከነፋሱም፡በዃላ፡የምድር፡መናወጥ፡ኾነ፥እግዚአብሔር፡ግን፡በምድር፡ መናወጥ፡ውስጥ፡አልነበረም።

12ከምድር፡መናወጥ፡በዃላ፡እሳት፡ኾነ፥እግዚአብሔር፡ግን፡በእሳቱ፡ውስጥ፡አልነበረም።ከእሳቱም፡በዃላ፡ ትንሽ፡የዝምታ፡ድምፅ፡ኾነ።

13ኤልያስም፡ያን፡በሰማ፡ጊዜ፡ፊቱን፡በመጐናጸፊያው፡ሸፈነ፥ወጥቶም፡በዋሻው፡ደጃፍ፡ ቆመ።እንሆ፦ኤልያስ፡ሆይ፥በዚህ፡ምን፡ታደርጋለኽ፧የሚል፡ድምፅ፡ወደ፡ርሱ፡መጣ።

14ርሱም፦ለሰራዊት፡አምላክ፡ለእግዚአብሔር፡እጅግ፡ቀንቻለኹ፤የእስራኤል፡ልጆች፡ቃል፡ኪዳንኽን፡ ትተዋልና፥መሠዊያዎችኽንም፡አፍርሰዋልና፥ነቢያትኽንም፡በሰይፍ፡ገድለዋልና፤እኔም፡ብቻዬን፡ ቀርቻለኹ፤ነፍሴንም፡ሊወስዷት፡ይሻሉ፡አለ።

15እግዚአብሔርም፡አለው፦ኺድ፥በመጣኽበትም፡መንገድ፡በምድረ፡በዳ፡ወደ፡ደማስቆ፡ ተመለስ፤ከዚያም፡በደረስኽ፡ጊዜ፡በሶርያ፡ላይ፡ንጉሥ፡ይኾን፡ዘንድ፡አዛሄልን፡ቅባው፤

16በእስራኤልም፡ላይ፡ንጉሥ፡ይኾን፡ዘንድ፡የናሜሲን፡ልጅ፡ኢዩን፡ቅባው፤በፋንታኽም፡ነቢይ፡ይኾን፡ http://www.gzamargna.net ዘንድ፡የአቤልምሖላን፡ሰው፡የሣፋጥን፡ልጅ፡ኤልሳዕን፡ቅባው፥ከአዛሄልም፡ሰይፍ፡ያመለጠውን፡ዅሉ።

17ኢዩ፡ይገድለዋል፤ከኢዩም፡ሰይፍ፡ያመለጠውን፡ዅሉ፡ኤልሳዕ፡ይገድለዋል።

18እኔም፡ከእስራኤል፡ጕልበታቸውን፡ለበዓል፡ያላንበረከኩትን፡ዅሉ፥በአፋቸውም፡ያልሳሙትን፡ዅሉ፥ሰባት፡ ሺሕ፡ሰዎች፡ለእኔ፡አስቀራለኹ።

19ከዚያም፡ኼደ፥የሣፋጥንም፡ልጅ፡ኤልሳዕን፡በዐሥራ፡ኹለት፡ጥማድ፡በሬዎች፡ሲያርስ፥ርሱም፡ከዐሥራ፡ ኹለተኛው፡ጋራ፡ኾኖ፡አገኘው።ኤልያስም፡ወደ፡ርሱ፡ዐልፎ፡መጐናጸፊያውን፡ጣለበት።

20በሬዎቹንም፡ተወ፥ከኤልያስም፡በዃላ፡ሮጦ፦አባቴንና፡እናቴን፡እስማቸው፡ ዘንድ፥እባክኽ፥ተወኝ፥ከዚያም፡በዃላ፡እከተልኻለኹ፡አለው።ርሱም፦ኺድና፡ተመለስ፤ምን፡ አድርጌልኻለኹ፧አለው።

21ከርሱም፡ዘንድ፡ተመልሶ፡ኹለቱን፡በሬዎች፡ወስዶ፡አረዳቸው፥ሥጋቸውንም፡በበሬዎቹ፡ዕቃ፡ ቀቀለው፥ለሕዝቡም፡ሰጣቸው፥በሉም፤ርሱም፡ተነሥቶ፡ኤልያስን፡ተከትሎ፡ኼደ፥ያገለግለውም፡ነበር።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source