1ከብዙ፡ቀንም፡በዃላ፡በሦስተኛው፡ዓመት።ኺድ፥ለአክአብ፡ተገለጥ፥በምድር፡ላይም፡ዝናብ፡እሰጣለኹ፡ የሚል፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ወደ፡ኤልያስ፡መጣ።
2ኤልያስም፡ለአክአብ፡ይገለጥ፡ዘንድ፡ኼደ፤በሰማርያም፡ራብ፡ጸንቶ፡ነበር።
3አክአብም፡የቤቱን፡አዛዥ፡ዐብድዩ ን፡ጠራ፤ዐብድዩ፡እግዚአብሔርን፡እጅግ፡ይፈራ፡ነበር።
4ኤልዛቤልም፡የእግዚአብሔርን፡ነቢያት፡ባስገደለች፡ጊዜ፡ርሱ፡መቶውን፡ነቢያት፡ወስዶ፡ዐምሳ፡ዐምሳውን፡ በዋሻ፡ውስጥ፡ሸሽጎ፡እንጀራና፡ውሃ፡ይመግባቸው፡ነበር።
5አክአብም፡ዐብድዩን፦በአገሩ፡መካከል፡ወደውሃው፡ምንጭ፡ዅሉና፡ወደ፡ወንዝ፡ዅሉ፡ ኺድ፤እንስሳዎችም፡ዅሉ፡እንዳይጠፉ፡ፈረሶችንና፡በቅሎዎችን፡የምናድንበት፡ሣር፡ምናልባት፡እናገኛለን፡ አለው።
6ኹለቱም፡የሚመለሱበትን፡አገር፡ተካፈሉ፤አክአብም፡ለብቻው፡ባንድ፡መንገድ፡ዐብድዩም፡ለብቻው፡ በሌላ፡መንገድ፡ኼዱ። 165 ዕብ.፥ዖባድያህ፡(ዐብደ፡እግዚእ፥የጌታ፡አገልጋይ)። http://www.gzamargna.net
7ዐብድዩም፡በመንገድ፡ሲኼድ፥እንሆ፥ኤልያስ፡ተገናኘው፤ዐብድዩም፡ዐወቀው፥በግንባሩም፡ ተደፍቶ፦ጌታዬ፡ሆይ፥ኤልያስ፡አንተ፡ነኽን፧አለ።
8ኤልያስም፦እኔ፡ነኝ፡ኼደኽ፡ለጌታኽ፦ኤልያስ፡ተገኝቷል፡በል፡አለው።
9ዐብድዩም፡አለ፦እኔን፡ባሪያኽን፡እንዲገድል፡በአክአብ፡እጅ፡አሳልፈኽ፡ትሰጠኝ፡ዘንድ፡ምን፡ኀጢአት፡ አድርጌያለኹ፧
10አምላክኽ፡ሕያው፡እግዚአብሔርን! ጌታዬ፡ይፈልግኽ፡ዘንድ፡ያልላከበት፡ሕዝብ፡ወይም፡መንግሥት፡ የለም፤ዅሉም፦በዚህ፡የለም፡ባሉ፡ጊዜ፡አንተን፡እንዳላገኙ፡መንግሥቱንና፡ሕዝቡን፡አምሏቸው፡ነበር።
11አኹንም፥እንሆ፦ኺድ፥ኤልያስ፡ተገኘ፡ብለኽ፡ለጌታኽ፡ንገር፡ትለኛለኽ።
12እኔም፡ከአንተ፡ጥቂት፡ራቅ፡ስል፡የእግዚአብሔር፡መንፈስ፡አንሥቶ፡ወደማላውቀው፡ስፍራ፡ ይወስድኻል፤እኔም፡ገብቼ፡ለአክአብ፡ስናገር፥ባያገኝኽ፡ይገድለኛል፤እኔም፡ባሪያኽ፡ከትንሽነቴ፡ዠምሬ፡ እግዚአብሔርን፡እፈራ፡ነበር።
13ኤልዛቤል፡የእግዚአብሔርን፡ነቢያት፡ባስገደለች፡ጊዜ፥መቶውን፡የእግዚአብሔር፡ነቢያት፡ወስጄ፥ዐምሳ፡ ዐምሳውንም፡በዋሻ፡ውስጥ፡ሸሽጌ፥እንጀራና፡ውሃ፡የመገብዃቸው፥ይህ፡ያደርግኹት፡ነገር፡በእውኑ፡ ለጌታዬ፡አልታወቀኽምን፧
14አኹንም፥ኼደኽ፦ኤልያስ፡ተገኘ፡ብለኽ፡ለጌታኽ፡ንገር፡ትላለኽ፤ርሱም፡ይገድለኛል።
15ኤልያስም፦በፊቱ፡የቆምኹት፡የሰራዊት፡ጌታ፡ሕያው፡እግዚአብሔርን! እኔ፡ዛሬ፡ለርሱ፡እገለጣለኹ፡ አለ።
16ዐብድዩም፡አክአብን፡ሊገናኘው፡ኼደ፥ነገረውም፤አክአብም፡ኤልያስን፡ሊገናኘው፡መጣ።
17አክአብም፡ኤልያስን፡ባየው፡ጊዜ፦እስራኤልን፡የምትገለባብጥ፡አንተ፡ነኽን፧አለው።
18ኤልያስም፦እስራኤልን፡የምትገለባብጡ፥የእግዚአብሔርን፡ትእዛዝ፡ትታችኹ፡በዓሊምን፡ የተከተላችኹ፥አንተና፡የአባትኽ፡ቤት፡ናችኹ፡እንጂ፡እኔ፡አይደለኹም።
19አኹንም፡ልከኽ፡እስራኤልን፡ዅሉ፥በኤልዛቤልም፡ማእድ፡የሚበሉትን፡አራት፡መቶ፡ዐምሳ፡የበዓልን፡ ነቢያት፥አራት፡መቶም፡የማምለኪያ፡ዐጸድን፡ነቢያት፡ወደ፡እኔ፡ወደቀርሜሎስ፡ተራራ፡ሰብስብ፡አለ።
20አክአብም፡ወደእስራኤል፡ልጆች፡ዅሉ፡ልኮ፡ነቢያቱን፡ዅሉ፡ወደቀርሜሎስ፡ተራራ፡ሰበሰበ።
21ኤልያስም፡ወደ፡ሕዝቡ፡ዅሉ፡ቀርቦ፦እስከ፡መቼ፡ድረስ፡በኹለት፡ዐሳብ፡ታነክሳላችኹ፧እግዚአብሔር፡ አምላክ፡ቢኾን፡ርሱን፡ተከተሉ፤በዓል፡ግን፡አምላክ፡ቢኾን፡ርሱን፡ተከተሉ፡አለ።ሕዝቡም፡አንዲት፡ቃል፡ አልመለሱለትም።
22ኤልያስም፡ሕዝቡን፡አለ፦ከእግዚአብሔር፡ነቢያት፡እኔ፡ብቻ፡ቀርቻለኹ፤የበዓል፡ነቢያት፡ግን፡አራት፡ መቶ፡ዐምሳ፡ሰዎች፡ናቸው።
23ኹለት፡ወይፈኖች፡ይሰጡን፤እነርሱም፡አንድ፡ወይፈን፡ይምረጡ፥እየብልቱም፡ይቍረጡት፥በዕንጨትም፡ ላይ፡ያኑሩት፥በበታቹም፡እሳት፡አይጨምሩ፤እኔም፡ኹለተኛውን፡ወይፈን፡አዘጋጃለኹ፥በዕንጨቱም፡ላይ፡ አኖረዋለኹ፥በበታቹም፡እሳት፡አልጨምርም።
24እናንተም፡የአምላካችኹን፡ስም፡ጥሩ፥እኔም፡የእግዚአብሔርን፡ስም፡እጠራለኹ፤ሰምቶም፡በእሳት፡ የሚመልስ፡አምላክ፥ርሱ፡አምላክ፡ይኹን።ሕዝቡም፡ዅሉ፦ይህ፡ነገር፡መልካም፡ነው፡ብለው፡መለሱ።
25ኤልያስም፡የበዓልን፡ነቢያት፦እናንተ፡ብዙዎች፡ናችኹና፥አስቀድማችኹ፡አንድ፡ወይፈን፡ምረጡና፡ አዘጋጁ፤የአምላካችኹንም፡ስም፡ጥሩ፥በበታቹም፡እሳት፡አትጨምሩ፡አላቸው።
26ወይፈኑንም፡ወስደው፡አዘጋጁ፥ከጧትም፡እስከ፡ቀትር፡ድረስ፦በዓል፡ሆይ፥ስማን፡እያሉ፡የበዓልን፡ ስም፡ጠሩ።ድምፅም፡አልነበረም፥የሚመልስም፡አልነበረም፤በሠሩትም፡መሠዊያ፡ዙሪያ፡እያነከሱ፡ያሸበሽቡ፡ http://www.gzamargna.net ነበር።
27በቀትርም፡ጊዜ፡ኤልያስ።አምላክ፡ነውና፥በታላቅ፡ቃል፡ጩኹ፤ምናልባት፡ዐሳብ፡ይዞታል፥ወይም፡ ፈቀቅ፡ብሏል፥ወይም፡ወደ፡መንገድ፡ኼዷል፥ወይም፡ተኝቶ፡እንደ፡ኾነ፡መቀስቀስ፡ያስፈልገዋል፡እያለ፡ አላገጠባቸው።
28በታላቅም፡ቃል፡ይጮኹ፥እንደ፡ልማዳቸውም፡ደማቸው፡እስኪፈስ፟፡ድረስ፡ገላቸውን፡በካራና፡በቀጭኔ፡ ይቧጭሩ፡ነበር።
29ቀትርም፡ካለፈ፡በዃላ፡መሥዋዕተ፡ሠርክ፡እስኪደርስ፡ትንቢት፡ይናገሩ፡ነበር፤ድምፅም፡ አልነበረም፥የሚመልስና፡የሚያደምጥም፡አልነበረም።
30ኤልያስም፡ሕዝቡን፡ዅሉ፦ወደ፡እኔ፡ቅረቡ፡አላቸው።ሕዝቡም፡ዅሉ፡ወደ፡ርሱ፡ቀረቡ።ፈርሶ፡ የነበረውንም፡የእግዚአብሔርን፡መሠዊያ፡አበጀ።
31ኤልያስም፦ስምኽ፡እስራኤል፡ይኾናል፡የሚል፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡እንደ፡ደረሰለት፡እንደ፡ያዕቆብ፡ ልጆች፡ነገድ፡ቍጥር፡ዐሥራ፡ኹለቱን፡ድንጋዮች፡ወሰደ።
32ከድንጋዮችም፡ለእግዚአብሔር፡ስም፡መሠዊያ፡ሠራ፤በመሠዊያውም፡ዙሪያ፡ኹለት፡መስፈሪያ፡እኽል፡ የሚያዝ፡ጕድጓድ፡ቈፈረ።
33ዕንጨቱንም፡በተርታ፡አደረገ፥ወይፈኑንም፡በብልት፡በብልቱ፡ቈረጠ፥በዕንጨቱም፡ላይ፡አኖረና።
34አራት፡ጋን፡ውሃ፡ሙሉ፡በሚቃጠለው፡መሥዋዕትና፡በዕንጨቱ፡ላይ፡አፍሱ፟፡አሉ።ደግሞም፦ድገሙ፡ አለ፤እነርሱም፡ደገሙ።ርሱም፦ሦስተኛ፡አድርጉ፡አለ፤ሦስተኛም፡አደረጉ።
35ውሃውም፡በመሠዊያው፡ዙሪያ፡ፈሰሰ፤ደግሞም፡ጕድጓዱን፡በውሃ፡ሞላው።
36መሥዋዕተ፡ሠርክ፡በሚቀርብበት፡ጊዜ፡ነቢዩ፡ኤልያስ፡ቀርቦ፦አቤቱ፥የአብርሃምና፡የይሥሐቅ፡ የእስራኤልም፡አምላክ፡ሆይ፥አንተ፡በእስራኤል፡ላይ፡አምላክ፡እንደ፡ኾንኽ፥እኔም፡ባሪያኽ፡እንደ፡ ኾንኹ፥ይህንም፡ዅሉ፡በቃልኽ፡እንዳደረግኹ፡ዛሬ፡ይገለጥ።
37አንተ፥አቤቱ፥አምላክ፡እንደ፡ኾንኽ፥ልባቸውንም፡ደግሞ፡እንደ፡መለስኽ፡ይህ፡ሕዝብ፡ያውቅ፡ዘንድ፡ ስማኝ፥አቤቱ፥ስማኝ፡አለ።
38የእግዚአብሔርም፡እሳት፡ወደቀች፥የሚቃጠለውን፡መሥዋዕቱንም፡ዕንጨቱንም፡ድንጋዮቹንም፡ዐፈሩንም፡ በላች፥በጕድጓዱም፡ውስጥ፡ያለውን፡ውሃ፡ላሰች።
39ሕዝቡም፡ዅሉ፡ያንን፡ባዩ፡ጊዜ፡በግንባራቸው፡ተደፍተው።እግዚአብሔር፡ርሱ፡አምላክ፡ነው፡አሉ።
40ኤልያስም፦ከበዓል፡ነቢያት፡አንድ፡ሰው፡እንዳያመልጥ፡ያዙ፡አላቸው።ያዟቸውም፤ኤልያስም፡ወደቂሶን፡ ወንዝ፡ወስዶ፡በዚያ፡አሳረዳቸው።
41ኤልያስም፡አክአብን፦የዝናቡ፡ውሽንፍር፡እጅግ፡ነውና፥ተነሥተኽ፡ውጣ፥ብላም፡ጠጣም፡አለው።
42አክአብም፡ሊበላና፡ሊጠጣ፡ወጣ፤ኤልያስም፡ወደቀርሜሎስ፡ዐናት፡ወጣ፤ፊቱንም፡በጕልበቱ፡መካከል፡ አድርጎ፡በግንባሩ፡ተደፋ።
43ብላቴናውንም፦ወጥተኽ፡ወደ፡ባሕሩ፡ተመልከት፡አለው።ወጥቶም፡ተመልክቶም፦ምንም፡የለም፡ አለ።ርሱም፦ሰባት፡ጊዜ፡ተመላለስ፡አለው።ብላቴናውም፡ሰባት፡ጊዜ፡ተመላለሰ።
44በሰባተኛውም፡ጊዜ፦እንሆ፥የሰው፡እጅ፡የምታኽል፡ታናሽ፡ደመና፡ከባሕር፡ወጣች፡ አለ።ርሱም፦ወጥተኽ፡አክአብን፦ዝናብ፡እንዳይከለክልኽ፡ሠረገላን፡ጭነኽ፡ውረድ፡በለው፡አለ።
45ከጥቂትም፡ጊዜ፡በዃላ፡ሰማዩ፡ከደመናውና፡ከነፋሱ፡የተነሣ፡ጨለመ፥ብዙም፡ዝናብ፡ኾነ፤አክአብም፡ በሠረገላው፡ተቀምጦ፡ወደ፡ኢይዝራኤል፡ኼደ።
46የእግዚአብሔርም፡እጅ፡በኤልያስ፡ላይ፡ነበረች፤ወገቡንም፡አሸንፍጦ፡ወደ፡ኢይዝራኤል፡እስኪገባ፡ http://www.gzamargna.net ድረስ፡በአክአብ፡ፊት፡ይሮጥ፡ነበር።