1በገለዓድ፡ቴስቢ፡የነበረው፡ቴስብያዊው፡ኤልያስ፡አክአብን፦በፊቱ፡የቆምኹት፡የእስራኤል፡አምላክ፡ ሕያው፡እግዚአብሔርን! ከአፌ፡ቃል፡በቀር፡በእነዚህ፡ዓመታት፡ጠልና፡ዝናብ፡አይኾንም፡አለው።
2የእግዚአብሔርም፡ቃል፡እንዲህ፡ሲል፡ለርሱ፡መጣለት።
3ከዚህ፡ተነሥተኽ፡ወደ፡ምሥራቅ፡ኺድ፥በዮርዳኖስም፡ትይዩ፡ባለው፡በኮራት፡ፈፋ፡ውስጥ፡ተሸሸግ።
4ከወንዙም፡ትጠጣለኽ፥ቍራዎችም፡በዚያ፡ይመግቡኽ፡ዘንድ፡አዝዣለኹ።
5ኼደም፥እንደእግዚአብሔር፡ቃልም፡አደረገ።ኼዶም፡በዮርዳኖስ፡ትይዩ፡ባለው፡በኮራት፡ፈፋ፡ውስጥ፡ ተቀመጠ።
6ቍራዎቹም፡በየጧትና፡በየማታው፡እንጀራና፡ሥጋ፡ያመጡለት፡ነበር፤ከወንዙም፡ይጠጣ፡ነበር።
7ከብዙ፡ቀንም፡በዃላ፡በምድር፡ላይ፡ዝናብ፡አልነበረምና፡ወንዙ፡ደረቀ።
8ተነሥተኽም፡በሲዶና፡አጠገብ፡ወዳለችው፡ወደ፡ሰራጵታ፡ኺድ፥በዚያም፡ተቀመጥ፤
9እንሆም፥ትመግብኽ፡ዘንድ፡አንዲት፡ባልቴት፡አዝዣለኹ፡የሚል፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡መጣለት።
10ተነሥቶም፡ወደ፡ሰራጵታ፡ኼደ፤ወደከተማዪቱም፡በር፡በደረሰ፡ጊዜ፡አንዲት፡ባልቴት፡በዚያ፡ዕንጨት፡ ትለቅም፡ነበር፤ርሱም፡ጠርቶ፦የምጠጣው፡ጥቂት፡ውሃ፡በጽዋ፡ታመጭልኝ፡ዘንድ፡እለምንሻለኹ፡አላት።
11ውሃም፡ልታመጣለት፡በኼደች፡ጊዜ፡ወደ፡ርሷ፡ጠርቶ፥ቍራሽ፡እንጀራ፡በእጅሽ፡ይዘሽ፡ትመጪ፡ ዘንድ፡እለምንሻለኹ፡አላት።
12ርሷም፦አምላክኽ፡ሕያው፡እግዚአብሔርን! በማድጋ፡ካለው፡ከዕፍኝ፡ዱቄት፥በማሰሮም፡ካለው፡ከጥቂት፡ 163 ዕብ.፥አኅአብ፡(እኅወ፡አብ፥ያባት፡ወንድም)። 164 ዕብ.፥ሐይኤል፡(ሕያው፡እግዚአብሔር)። http://www.gzamargna.net ዘይት፡በቀር፡እንጀራ፡የለኝም፤እንሆም፥ገብቼ፡ለኔና፡ለልጄ፡እጋግረው፡ዘንድ፡በልተነውም፡እንሞት፡ዘንድ፡ ጥቂት፡ዕንጨት፡እሰበስባለኹ፡አለች።
13ኤልያስም፡አላት፦አትፍሪ፤ይልቅስ፡ኼደሽ፡እንዳልሺው፡አድርጊ፤አስቀድመሽ፡ግን፡ከዱቄቱ፡ለእኔ፡ ታናሽ፡ዕንጐቻ፡አድርገሽ፡አምጪልኝ፥ከዚያም፡በዃላ፡ለአንቺና፡ለልጅሽ፡አድርጊ፤
14የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላልና፦በምድር፡ላይ፡እግዚአብሔር፡ዝናብ፡እስከሚሰጥበት፡ ቀን፡ድረስ፥ዱቄቱ፡ከማድጋ፡አይጨረስም፥ዘይቱም፡ከማሰሮው፡አይጐድልም።
15ርሷም፡ኼዳ፡እንደ፡ኤልያሳ፡ቃል፡አደረገች፤ርሷና፡ርሱ፡ቤቷም፡ብዙ፡ቀን፡በሉ።
16በኤልያስም፡እጅ፡እንደተናገረው፡እንደእግዚአብሔር፡ቃል፡ዱቄቱ፡ከማድጋው፡አልተጨረሰም፥ዘይቱም፡ ከማሰሮው፡አልጐደለም።
17ከዚያም፡በዃላ፡የባለቤቲቱ፡ልጅ፡ታመመ፤ትንፋሹም፡እስኪታጣ፡ድረስ፡ደዌው፡እጅግ፡ከባድ፡ነበረ።
18ርሷም፡ኤልያስን፦የእግዚአብሔር፡ሰው፡ሆይ፥ከአንተ፡ጋራ፡ምን፡አለኝ፧ኀጢአቴንስ፡ታሳስብ፡ ዘንድ፥ልጄንስ፡ትገድል፡ዘንድ፡ወደ፡እኔ፡መጥተኻልን፧አለችው።
19ኤልያስም፦ልጅሽን፡ስጪኝ፡አላት።ከብብቷም፡ወስዶ፡ተቀምጦበት፡ወደነበረው፡ሰገነት፡አወጣው፡ በዐልጋውም፡ላይ፡አጋደመው።
20ወደ፡እግዚአብሔርም፦አቤቱ፡አምላኬ፡ሆይ፥ልጇን፡በመግደልኽ፡ይህችን፡ትቀልበኝ፡የነበረቺቱን፡ ባልቴት፡እንዲህ፡ደግሞ፡አስጨነቅኻትን፧ብሎ፡ጮኸ።
21በብላቴናውም፡ላይ፡ሦስት፡ጊዜ፡ተዘረጋበት፥ወደ፡እግዚአብሔርም፦አቤቱ፡አምላኬ፡ሆይ፥የዚህ፡ ብላቴና፡ነፍስ፡ወደ፡ርሱ፡ትመለስ፡ዘንድ፡እለምንኻለኹ፡ብሎ፡ጮኸ።
22እግዚአብሔርም፡የኤልያስን፡ቃል፡ሰማ፤የብላቴናው፡ነፍስ፡ወደ፡ርሱ፡ተመለሰች፥ርሱም፡ዳነ።
23ኤልያስም፡ብላቴናውን፡ይዞ፡ከሰገነቱ፡ወደ፡ቤት፡አወረደው፥ኤልያስም፦እንሆ፥ልጅሽ፡በሕይወት፡ ይኖራል፡ብሎ፡ለእናቱ፡ሰጣት።
24ሴቲቱም፡ኤልያስን፦የእግዚአብሔር፡ሰው፡እንደ፡ኾንኽ፥የእግዚአብሔርም፡ቃል፡በአፍኽ፡እውነት፡ እንደ፡ኾነ፡አኹን፡ዐወቅኹ፡አለችው።