Skip to content
← 1 Kings

Chapter 16 · Amharic

1 Kings

1የእግዚአብሔርም፡ቃል፡በባኦስ፡ላይ፡እንዲህ፡ብሎ፡ወደዐናኒ፡ልጅ፡ወደ፡ኢዩ ፡መጣ።

2እኔ፡ከመሬት፡አስነሥቼ፡በሕዝቤ፡በእስራኤል፡ላይ፡አለቃ፡አድርጌኻለኹ፤አንተ፡ግን፡በኢዮርብዓም፡ መንገድ፡ኼደኻል፥በኀጢአታቸውም፡ያስቈጡኝ፡ዘንድ፡ሕዝቤን፡እስራኤልን፡አስተኻቸዋል።

3ስለዚህም፥እንሆ፥ባኦስንና፡ቤቱን፡ፈጽሜ፡እጠርጋለኹ፤ቤትኽንም፡እንደ፡ናባጥ፡ልጅ፡እንደ፡ ኢዮርብዓም፡ቤት፡አደርጋለኹ።

4ከባኦስም፡ወገን፡በከተማዪቱ፡ውስጥ፡የሚሞተውን፡ውሻዎች፡ይበሉታል፤በሜዳውም፡የሚሞተውን፡የሰማይ፡ 162 ዕብ.፥የሁ፡(ያምላክ)። http://www.gzamargna.net ወፎች፡ይበሉታል።

5የቀረውም፡የባኦስ፡ነገር፥ሥራውና፡ጭከናውም፥በእስራኤል፡ነገሥታት፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡የተጻፈ፡ አይደለምን፧

6ባኦስም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡አንቀላፋ፥በቴርሳም፡ተቀበረ፤ልጁም፡ኤላ፡በፋንታው፡ነገሠ።

7በእጁም፡ሥራ፡ያስቈጣው፡ዘንድ፥እንደ፡ኢዮርብዓም፡ቤት፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ስላደረገው፡ክፋት፡ ዅሉ፡ርሱንም፡ስለ፡ገደለው፥የእግዚአብሔር፡ቃል፡በባኦስና፡በቤቱ፡ላይ፡ወደዐናኒ፡ልጅ፡ወደ፡ነቢዩ፡ወደ፡ ኢዩ፡መጣ።

8በይሁዳም፡ንጉሥ፡በአሣ፡በኻያ፡ስድስተኛው፡ዓመት፡የባኦስ፡ልጅ፡ኤላ፡በእስራኤል፡ላይ፡በቴርሳ፡ኹለት፡ ዓመት፡ነገሠ።

9የእኩሌቶቹም፡ሠረገላዎች፡አለቃ፡ዘምሪ፡ተማማለበት፤ዔላም፡በቴርሳ፡ነበረ፥በቴርሳም፡በነበረው፡በቤት፡ አሽከሮች፡አለቃ፡በኦሳ፡ቤት፡ይሰክር፡ነበር።

10በይሁዳም፡ንጉሥ፡በአሣ፡በኻያ፡ሰባተኛው፡ዓመት፡ዘምሪ፡ገብቶ፡መታው፡ገደለውም፥በፋንታውም፡ ነገሠ።

11ንጉሥም፡በኾነ፡ጊዜ፥በዙፋኑም፡በተቀመጠ፡ጊዜ፥የባኦስን፡ቤት፡ዅሉ፡መታ፤ከዘመዶችና፡ከወዳጆች፡ ዅሉ፡አንድ፡ወንድ፡እንኳ፡አልቀረም።

13ባኦስና፡ልጁ፡ኤላ፡ስለሠሩት፡ኀጢአት፡ዅሉ፥በምናምንቴም፡ሥራቸው፡የእስራኤልን፡አምላክ፡ እግዚአብሔርን፡ያስቈጡት፡ዘንድ፡እስራኤልን፡ስላሳቱበት፡ኀጢአት፥በነቢዩ፡በኢዩ፡እጅ፡በባኦስ፡ላይ፡ እንደተናገረው፡እንደእግዚአብሔር፡ቃል፡ዘምሪ፡የባኦስን፡ቤት፡ዅሉ፡እንዲሁ፡አጠፋ።

14የቀረውም፡የኤላ፡ነገር፥ያደረገውም፡ዅሉ፥በእስራኤል፡ነገሥታት፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡የተጻፈ፡አይደለምን፧

15በይሁዳ፡ንጉሥ፡በአሣ፡በኻያ፡ሰባተኛው፡ዓመት፡ዘምሪ፡በቴርሳ፡ሰባት፡ቀን፡ነገሠ።ሕዝቡም፡ በፍልስጥኤም፡አገር፡የነበረው፡ገባቶንን፡ከበ፟ው፡ነበር።

16ከተማዪቱንም፡ከበ፟ው፡የነበሩ፡ሕዝብ፡ዘምሪ፡እንደ፡ዐመፀ፥ንጉሡንም፡እንደ፡ገደለ፡ሰሙ፤እስራኤልም፡ ዅሉ፡በዚያ፡ቀን፡በሰፈሩ፡ውስጥ፡የሰራዊቱን፡አለቃ፡ዘንበሪን፡አነገሡ።

17ዘንበሪም፡ከርሱም፡ጋራ፡እስራኤል፡ዅሉ፡ከገባቶን፡ወጥተው፡ቴርሳን፡ከበቡ።

18ዘምሪም፡ከተማዪቱ፡እንደ፡ተያዘች፡ባየ፡ጊዜ፡ወደንጉሡ፡ቤት፡ግንብ፡ውስጥ፡ገባ፥የንጉሡንም፡ቤት፡ በራሱ፡ላይ፡በእሳት፡አቃጠለ፤

19ስላደረገውም፡ኀጢአት፥እስራኤልንም፡ስላሳተበት፡ኀጢአት፥በእግዚአብሔር፡ፊት፡ክፉ፡ አድርጓልና፥በኢዮርብዓምም፡መንገድ፡ኼዷልና፥ሞተ።

20የቀረውም፡የዘምሪ፡ነገር፥ያደረገውም፡ዐመፅ፥በእስራኤል፡ነገሥታት፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡የተጻፈ፡ አይደለምን፧

21በዚያም፡ጊዜ፡የእስራኤል፡ሕዝብ፡በኹለት፡ተከፈለ፤የሕዝቡም፡እኩሌታ፡የጎናትን፡ልጅ፡ታምኒን፡ ያነግሡት፡ዘንድ፡ተከተለው፤እኩሌታውም፡ዘንበሪን፡ተከተለ።

22ዘንበሪንም፡የተከተለ፡ሕዝብ፡የጎናትን፡ልጅ፡ታምኒን፡በተከተለ፡ሕዝብ፡ላይ፡በረታ፤ታምኒም፡ ሞተ፥ዘንበሪም፡ነገሠ።

23በይሁዳ፡ንጉሥ፡በአሣ፡በሠላሳ፡አንደኛው፡ዓመት፡ዘንበሪ፡በእስራኤል፡ላይ፡ዐሥራ፡ኹለት፡ዓመት፡ ነገሠ።በቴርሳም፡ስድስት፡ዓመት፡ነገሠ።

24ከሳምርም፡በኹለት፡መክሊት፡ብር፡የሰማርያን፡ተራራ፡ገዛ፤በተራራውም፡ላይ፡ሠራ፥የሠራውንም፡ ከተማ፡በተራራው፡ባለቤት፡በሳምር፡ስም፡ሰማርያ፡ብሎ፡ጠራው። http://www.gzamargna.net

25ዘንበሪም፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ክፉ፡አደረገ፥ከርሱም፡አስቀድሞ፡ከነበሩት፡ይልቅ፡እጅግ፡ከፋ፟።

26በናባጥም፡ልጅ፡በኢዮርብዓም፡መንገድ፡ዅሉ፡በምናምንቴም፡ነገራቸው፡የእስራኤልን፡አምላክ፡ እግዚአብሔርን፡ያስቈጡት፡ዘንድ፡እስራኤልን፡ባሳተበት፡ኀጢአት፡ኼደ።

27የቀረውም፡ዘንበሪ፡ያደረገው፡ነገር፥የሠራውም፡ጭከና፥በእስራኤል፡ነገሥታት፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡የተጻፈ፡ አይደለምን፧

28ዘንበሪም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡አንቀላፋ፥በሰማርያም፡ተቀበረ፤ልጁም፡አክአብ ፡በፋንታው፡ነገሠ።

29በይሁዳም፡ንጉሥ፡በአሣ፡በሠላሳ፡ስምንተኛው፡ዓመት፡የዘንበሪ፡ልጅ፡አክአብ፡በእስራኤል፡ላይ፡ ነገሠ፤የዘንበሪም፡ልጅ፡አክአብ፡በእስራኤል፡ላይ፡በሰማርያ፡ኻያ፡ኹለት፡ዓመት፡ነገሠ።

30የዘንበሪም፡ልጅ፡አክአብ፡ከርሱ፡በፊት፡ከነበሩት፡ዅሉ፡ይልቅ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ክፉ፡አደረገ።

31በናባጥም፡ልጅ፡በኢዮርብዓም፡ኀጢአት፡መኼድ፡ታናሽ፡ነገር፡መሰለው፥የሲዶናውያንንም፡ንጉሥ፡ የኤትበዓልን፡ልጅ፡ኤልዛቤልን፡አገባ፥ኼዶም፡በዓልን፡አመለከ፡ሰገደለትም።

32በሰማርያም፡በሠራው፡በበዓል፡ቤት፡ውስጥ፡ለበዓል፡መሠዊያ፡አቆመ።

33አክአብም፡የማምለኪያ፡ዐጸድ፡ተከለ፤አክአብም፡ከርሱ፡በፊት፡ከነበሩት፡ዅሉ፡ይልቅ፡የእስራኤልን፡ አምላክ፡እግዚአብሔርን፡የሚያስቈጣውን፡ነገር፡አበዛ።

34በርሱም፡ዘመን፡የቤቴል፡ሰው፡አኪኤል ፡ኢያሪኮን፡ሠራ፤በነዌም፡ልጅ፡በኢያሱ፡እጅ፡እንደተነገረው፡ እንደእግዚአብሔር፡ቃል፥በበኵር፡ልጅ፡በአቢሮን፡መሠረቷን፡አደረገ፥በታናሹ፡ልጁም፡በሰጉብ፡በሮቿን፡ አቆመ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source