1የናባጥ፡ልጅ፡ኢዮርብዓም፡በነገሠ፡በዐሥራ፡ስምንተኛው፡ዓመት፡አብያም፡በይሁዳ፡ላይ፡ንጉሥ፡ኾነ።
2በኢየሩሳሌምም፡ሦስት፡ዓመት፡ነገሠ፤እናቱም፡መዓካ፡የተባለች፡የአቤሴሎም፡ልጅ፡ነበረች።
3ከርሱ፡አስቀድሞ፡ባደረገው፡በአባቱ፡ኀጢአት፡ዅሉ፡ኼደ፤ልቡም፡እንደ፡አባቱ፡እንደ፡ዳዊት፡ልብ፡ ከአምላኩ፡ከእግዚአብሔር፡ጋራ፡ፍጹም፡አልነበረም።
4ነገር፡ግን፥ልጁን፡ከርሱ፡በዃላ፡ያስነሣ፡ዘንድ፥ኢየሩሳሌምንም፡ያጸና፡ዘንድ፡አምላኩ፡እግዚአብሔር፡ ስለ፡ዳዊት፡በኢየሩሳሌም፡መብራት፡ሰጠው፤
5ዳዊት፡በዘመኑ፡ዅሉ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ቅን፡ነገር፡አድርጎ፡ነበርና፥ካዘዘውም፡ነገር፡ዅሉ፡ፈቀቅ፡ አላለም፡ነበርና።
6በኢዮርብዓምና፡በሮብዓም፡ልጅ፡በአብያም፡መካከል፡በዘመኑ፡ዅሉ፡ጠብ፡ነበረ።
7የቀረውም፡የአብያም፡ነገር፥ያደርገውም፡ዅሉ፥በይሁዳ፡ነገሥታት፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡የተጻፈ፡ አይደለምን፧በአብያምና፡በኢዮርብዓምም፡መካከል፡ሰልፍ፡ነበረ።
8አብያምም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡አንቀላፋ፥በዳዊትም፡ከተማ፡ቀበሩት።ልጁም፡አሣ፡በፋንታው፡ነገሠ።
9በእስራኤል፡ንጉሥ፡በኢዮርብዓም፡በኻያኛውም፡ዓመት፡አሣ፡በይሁዳ፡ላይ፡ነገሠ።
10በኢየሩሳሌምም፡አርባ፡አንድ፡ዓመት፡ነገሠ፤እናቱም፡መዓካ፡የተባለች፡የአቤሴሎም፡ልጅ፡ነበረች።
11አሣ፡እንደ፡አባቱ፡እንደ፡ዳዊት፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ቅን፡ነገር፡አደረገ።
12ከአገሩም፡ሰዶማውያንን፡አስወገደ፥አባቶቹም፡ያደረጉትን፡ጣዖታትን፡ዅሉ፡አራቀ።
13በማምለኪያ፡ዐጸድ፡ጣዖት፡ስለ፡ሠራች፡እናቱን፡መዓካን፡እቴጌ፡እንዳትኾን፡ሻራት፤ጣዖቷንም፡ ሰበረው፥በቄድሮንም፡ፈፋ፡አጠገብ፡አቃጠለው።
14ነገር፡ግን፥በኰረብታዎች፡ላይ፡ያሉትን፡መስገጃዎች፡አላራቀም፤የአሣ፡ልብ፡ግን፡በዘመኑ፡ዅሉ፡ ከእግዚአብሔር፡ጋራ፡ፍጹም፡ነበረ።
15አባቱ፡የቀደሰውንና፡ርሱም፡የቀደሰውን፡ወርቅና፡ብር፡ዕቃውንም፡ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡አገባው።
16በአሣና፡በእስራኤል፡ንጉሥ፡በባኦስ፡መካከል፥በዘመናቸው፡ዅሉ፡ሰልፍ፡ነበረ።
17የእስራኤልም፡ንጉሥ፡ባኦስ፡በይሁዳ፡ላይ፡ወጣ፤ከይሁዳ፡ንጉሥ፡ከአሣ፡ዘንድ፡ማንም፡ እንዳይወጣ፥ወደ፡ርሱም፡ማንም፡እንዳይገባ፡አድርጎ፡ራማን፡ሠራ።
18አሣም፡በእግዚአብሔር፡ቤትና፡በንጉሥ፡ቤት፡መዛግብት፡የቀረውን፡ብርና፡ወርቅ፡ዅሉ፡ወስዶ፡ በባሪያዎቹ፡እጅ፡ሰጣቸው፤ንጉሡም፡አሣ፡በደማስቆ፡ለተቀመጠው፡ለዐዚን፡ልጅ፡ለጠብሪሞን፡ልጅ፡ለሶርያ፡ http://www.gzamargna.net ንጉሥ፡ለወልደ፡አዴር፦
19በእኔና፡ባንተ፡መካከል፡በአባቴና፡በአባትኽም፡መካከል፡ቃል፡ኪዳን፡ጸንቷል፤እንሆ፥ብርና፡ወርቅ፡ገጸ፡ በረከት፡ሰድጄልኻለኹ፤ርሱ፡ከእኔ፡ዘንድ፡እንዲርቅ፡ኼደኽ፡ከእስራኤል፡ንጉሥ፡ከባኦስ፡ጋራ፡ያለኽን፡ቃል፡ ኪዳን፡አፍርስ፡ብሎ፡ሰደደ።
20ወልደ፡አዴርም፡ለንጉሡ፡ለአሣ፡ዕሺ፡አለው፤የሰራዊቱንም፡አለቃዎች፡በእስራኤል፡ከተማዎች፡ላይ፡ ሰዶ፟፡ዒዮንንና፡ዳንን፥አቤልቤት፡መዓካንና፡ኪኔሬትን፡ዅሉ፡የንፍታሌምንም፡አገር፡ዅሉ፡መታ።
21ባኦስም፡ያን፡በሰማ፡ጊዜ፡ራማን፡መሥራት፡ትቶ፡በቴርሳ፡ተቀመጠ።
22ንጉሡም፡አሣ፡በይሁዳ፡ዅሉ፡ላይ፡ዐዋጅ፡ነገረ፤ማንም፡ነጻ፡አልነበረም፤ባኦስም፡የሠራበትን፡የራማን፡ ድንጋይና፡ዕንጨት፡ወሰዱ፥ንጉሡም፡አሣ፡የብንያምን፡ጌባንና፡ምጽጳን፡ሠራበት።
23የቀረውም፡የአሣ፡ነገር፡ዅሉ፥ጭከናውም፡ዅሉ፥ያደረገውም፡ዅሉ፥የሠራቸውም፡ከተማዎች፥በይሁዳ፡ ነገሥት፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡የተጻፈ፡አይደለምን፧ነገር፡ግን፡በሸመገለ፡ጊዜ፡እግሮቹ፡ታመሙ።
24አሣም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡አንቀላፋ፥በአባቱም፡በዳዊት፡ከተማ፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡ተቀበረ።ልጁም፡ኢዮሳፍጥ፡ በፋንታው፡ነገሠ።
25በይሁዳም፡ንጉሥ፡በአሣ፡በኹለተኛው፡ዓመት፡የኢዮርብዓም፡ልጅ፡ናዳብ፡በእስራኤል፡ላይ፡ ነገሠ፤በእስራኤልም፡ላይ፡ኹለት፡ዓመት፡ነገሠ።
26በእግዚአብሔርም፡ፊት፡ክፉ፡አደረገ፥በአባቱም፡መንገድ፡እስራኤልንም፡ባሳተበት፡ኀጢአት፡ኼደ።
27ከይሳኮርም፡ቤት፡የኾነ፡የአኪያ፡ልጅ፡ባኦስ፡ተማማለበት፤ናዳብና፡እስራኤልም፡ዅሉ፡ገባቶንን፡ከበ፟ው፡ ነበርና፥ባኦስ፡በፍልስጥኤም፡አገር፡ባለው፡በገባቶን፡ገደለው።
28በይሁዳ፡ንጉሥ፡በአሣ፡በሦስተኛው፡ዓመት፡ባኦስ፡ናዳብን፡ገደለው፥በፋንታውም፡ነገሠ።
30ንጉሥም፡በኾነ፡ጊዜ፡የኢዮርብዓምን፡ቤት፡ዅሉ፡መታ፤ኢዮርብዓምም፡ስለሠራው፡ ኀጢአት፥እስራኤልንም፡ስላሳተበት፥የእስራኤልንም፡አምላክ፡እግዚአብሔርን፡ስላስቈጣበት፡ማስቈጫ፥በባሪያው፡ በሴሎናዊው፡በአኪያ፡እጅ፡እንደተናገረው፡እንደእግዚአብሔር፡ቃል፥እስኪያጠፋው፡ድረስ፡ከኢዮርብዓም፡ አንድ፡ትንፋሽ፡ያለው፡አላስቀረም።
31የቀረውም፡የናዳብ፡ነገርና፡ያደረገው፡ዅሉ፥ (
32)፡በእስራኤል፡ነገሥታት፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡የተጻፈ፡አይደለምን፧
33በይሁዳም፡ንጉሥ፡በአሣ፡በሦስተኛው፡ዓመት፡የአኪያ፡ልጅ፡ባኦስ፡በእስራኤል፡ዅሉ፡ላይ፡በቴርሳ፡ ንጉሥ፡ኾኖ፡ኻያ፡አራት፡ዓመት፡ነገሠ።
34በእግዚአብሔርም፡ፊት፡ክፉ፡አደረገ፥በኢዮርብዓምም፡መንገድ፡እስራኤልንም፡ባሳተበት፡ኀጢአት፡ኼደ።