Skip to content
← 1 Kings

Chapter 14 · Amharic

1 Kings

1በዚያም፡ወራት፡የኢዮርብዓም፡ልጅ፡አብያ፡ታመመ።

2ኢዮርብዓምም፡ሚስቱን፦ተነሺ፥የኢዮርብዓምም፡ሚስት፡እንደ፡ኾንሽ፡እንዳትታወቂ፡ልብስሽን፡ለውጪና፡ ወደ፡ሴሎ፡ኺጂ፤እንሆ፥በዚህ፡ሕዝብ፡ላይ፡እንድነግሥ፡የነገረኝ፡ነቢዩ፡አኪያ፡በዚያ፡አለ።

3በእጅሽም፡ዐሥር፡እንጀራና፡ዕንጐቻዎች፡አንድም፡ምንቸት፡ማር፡ይዘሽ፡ወደ፡ርሱ፡ኺጂ፤በልጁም፡ የሚኾነውን፡ይነግርሻል፡አላት።

4የኢዮርብዓምም፡ሚስት፡እንዲሁ፡አደረገች፥ተነሥታም፡ወደ፡ሴሎ፡ኼደች፤ወደአኪያም፡ቤት፡ መጣች።አኪያም፡ስለ፡መሸምገሉ፡ዐይኖቹ፡ፈዘ፟ው፡ነበርና፤ማየት፡አልቻለም።

5እግዚአብሔርም፡አኪያን፦እንሆ፥ስለታመመው፡ልጇ፡ትጠይቅኽ፡ዘንድ፡የኢዮርብዓም፡ሚስት፡ ትመጣለች፤ሌላ፡ሴትም፡መስላ፡ተሰውራለችና፡በገባች፡ጊዜ፡እንዲህና፡እንዲህ፡በላት፡አለው።

6ርሷም፡በደጅ፡ስትገባ፡አኪያ፡የእግሯን፡ኰቴ፡ሰማ፥እንዲህም፡አለ፦የኢዮርብዓም፡ሚስት፡ ሆይ፥ግቢ፤ስለ፡ምንስ፡ሌላ፡ሴት፡መሰልሽ፧እኔም፡ብርቱ፡ወሬ፡ይዤ፡ተልኬልሻለኹ።

7ኺጂ፥ለኢዮርብዓምም፡እንዲህ፡በዪው፦የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ከሕዝብ፡ መካከል፡ለይቼ፡ከፍ፡አድርጌኽ፡ነበር፥በሕዝቤም፡በእስራኤል፡ላይ፡አለቃ፡አድርጌኽ፡ነበር፥

8ከዳዊትም፡ቤት፡መንግሥቱን፡ቀድጄ፡ሰጥቼኽ፡ነበር፤ነገር፡ግን፥በፍጹም፡ልቡ፡እንደ፡ ተከተለኝ፥በፊቴም፡ቅን፡ነገር፡ብቻ፡እንዳደረገ፥ትእዛዜንም፡እንደ፡ጠበቀ፡እንደ፡ባሪያዬ፡እንደ፡ዳዊት፡ http://www.gzamargna.net አልኾንኽም።

9ከአንተም፡አስቀድመው፡ከነበሩት፡ዅሉ፡ይልቅ፡ክፉ፡ሠራኽ፤ታስቈጣኝም፡ዘንድ፡ኼደኽ፡ሌላዎችን፡ አማልክትና፡ቀልጠው፡የተሠሩትን፡ምስሎች፡አደረግኽ፥ወደ፡ዃላኽም፡ጣልኸኝ።

10ስለዚህ፥እንሆ፥በኢዮርብዓም፡ቤት፡ላይ፡መከራ፡አመጣለኹ፥ከኢዮርብአምም፡በእስራኤል፡ዘንድ፡ የታሰረውንና፡የተለቀቀውን፡ወንድ፡ዅሉ፡እቈርጣለኹ፤ሰውም፡ፋንድያን፡እስኪጠፋ፡ድረስ፡እንደሚጠርግ፡ እኔ፡የኢዮርብዓምን፡ቤት፡ፈጽሜ፡እጠርጋለኹ።

11ከኢዮርብዓምም፡ወገን፡በከተማዪቱ፡ውስጥ፡የሞተውን፡ውሻዎች፡ይበሉታል፤በሜዳውም፡የሞተውን፡ የሰማይ፡ወፎች፡ይበሉታል፤እግዚአብሔር፡ተናግሯልና።

12እንግዲህ፡ተነሥተሽ፡ወደ፡ቤትሽ፡ኺጂ፤እግርሽም፡ወደ፡ከተማ፡በገባ፡ጊዜ፡ልጁ፡ይሞታል።

13እስራኤልም፡ዅሉ፡ያለቅሱለታል፥ይቀብሩትማል፤በእስራኤል፡አምላክ፡በእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ በኢዮርብዓም፡ቤት፡በዚህ፡ልጅ፡መልካም፡ነገር፡ተገኝቶበታልና፥ከኢዮርብዓም፡ርሱ፡ብቻ፡ይቀበራል።

14እግዚአብሔርም፡ደግሞ፡በእስራኤል፡ላይ፡ንጉሥ፡ያስነሣል፤ርሱም፡በዚያ፡ዘመን፡የኢዮርብዓምን፡ቤት፡ ያጠፋል።

15በዚያ፡ጊዜም፡ሸምበቆ፡በውሃ፡ውስጥ፡እንደሚንቀሳቀስ፡እግዚአብሔር፡እንዲሁ፡እስራኤልን፡ ይመታል፤እግዚአብሔርንም፡ያስቈጡ፡ዘንድ፡የማምለኪያ፡ዐጸድ፡ተክለዋልና፥ለአባቶቻቸው፡ከሰጣቸው፡ ከዚች፡ከመልካሚቱ፡ምድር፡እስራኤልን፡ይነቅላል፥በወንዙም፡ማዶ፡ይበትናቸዋል።

16ስለበደለውና፡እስራኤልንም፡ስላሳተበት፡ስለ፡ኢዮርብዓም፡ኀጢአት፡እስራኤልን፡ይጥላል።

17የኢዮርብዓምም፡ሚስት፡ተነሥታ፡ኼደች፥ወደ፡ቴርሳ፡መጣች፤ወደ፡ቤቱም፡መድረክ፡በገባች፡ጊዜ፡ ልጁ፡ሞተ።

18በባሪያውም፡በነቢዩ፡በአኪያ፡እንደተነገረው፡እንደእግዚአብሔር፡ቃል፡እስራኤል፡ዅሉ፡ቀበሩት፡ አለቀሱለትም።

19የቀረውም፡የኢዮርብዓም፡ነገር፥እንዴት፡እንደ፡ተዋጋ፥እንዴትም፡እንደ፡ነገሠ፥እንሆ፥በእስራኤል፡ ነገሥታት፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡ተጽፏል።

20ኢዮርብዓምም፡የነገሠበት፡ዘመን፡ኻያ፡ኹለት፡ዓመት፡ነበረ፤ከአባቶቹም፡ጋራ፡አንቀላፋ፥ልጁም፡ ናዳብ፡በፋንታው፡ነገሠ።

21የሰሎሞንም፡ልጅ፡ሮብዓም፡በይሁዳ፡ነገሠ፤ሮብዓምም፡ንጉሥ፡በኾነ፡ጊዜ፡የአርባ፡አንድ፡ዓመት፡ ጕልማሳ፡ነበረ፤እግዚአብሔርም፡ስሙን፡ያኖርባት፡ዘንድ፡ከእስራኤል፡ነገድ፡ዅሉ፡በመረጣት፡ከተማ፡ በኢየሩሳሌም፡ዐሥራ፡ሰባት፡ዓመት፡ነገሠ፤የእናቱም፡ስም፡ናዕማ፡ነበረ፤ርሷም፡አሞናዊት፡ነበረች።

22ይሁዳም፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ክፉ፡ሠራ፤አባቶቻቸውም፡ከሠሩት፡ዅሉ፡ይልቅ፡አብዝተው፡በሠሩት፡ ኀጢአት፡አስቈጡት።

23እነርሱም፡ደግሞ፡ከፍ፡ባለው፡ኰረብታ፡ዅሉ፡ላይ፥ቅጠሉ፡ከለመለመ፡ዛፍ፡ዅሉ፡በታች፡ መስገጃዎችንና፡ሐውልቶችን፡የማምለኪያ፡ዐጸዶችንም፡ለራሳቸው፡ሠሩ።

24በምድርም፡ውስጥ፡ሰዶማውያን፡ነበሩ፤ከእስራኤልም፡ልጆች፡ፊት፡እግዚአብሔር፡ያሳደዳቸውን፡ የአሕዛብን፡ርኵሰት፡ዅሉ፡ያደርጉ፡ነበር።

25ሮብዓምም፡በነገሠ፡በዐምስተኛው፡ዓመት፡የግብጽ፡ንጉሥ፡ሺሻቅ፡በኢየሩሳሌም፡ላይ፡መጣ።

26የእግዚአብሔርም፡ቤት፡መዛግብትንና፡የንጉሥ፡ቤት፡መዛግብትን፡ወሰደ፤ዅሉንም፡ወሰደ፤ሰሎሞንም፡ የሠራውን፡የወርቁን፡ጋሻ፡ዅሉ፡ወሰደ።

27ንጉሡም፡ሮብዓም፡በፋንታው፡የናስ፡ጋሻዎችን፡ሠራ፥የንጉሥንም፡ቤት፡ደጅ፡በሚጠብቁ፡በዘበኛዎች፡ http://www.gzamargna.net አለቃዎች፡እጅ፡አኖራቸው።

28ንጉሡም፡ዘወትር፡ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡ሲገባ፡ዘበኛዎች፡ይሸከሟቸው፡ነበር፤መልሰውም፡በዘበኛዎች፡ ቤት፡ውስጥ፡ያኖሯቸው፡ነበር።

29የቀረውም፡የሮብዓም፡ነገር፥ያደረገውም፡ዅሉ፥በይሁዳ፡ነገሥታት፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡የተጻፈ፡ አይደለምን፧

30በዘመኑም፡ዅሉ፡በሮብዓምና፡በኢዮርብዓም፡መካከል፡ሰልፍ፡ነበረ።

31ሮብዓምም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡አንቀላፋ፥በዳዊትም፡ከተማ፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡ተቀበረ።ልጁም፡አብያም፡ በፋንታው፡ነገሠ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source