Skip to content
← 1 Kings

Chapter 13 · Amharic

1 Kings

1እንሆም፥አንድ፡የእግዚአብሔር፡ሰው፡በእግዚአብሔር፡ቃል፡ከይሁዳ፡ወደ፡ቤቴል፡መጣ፤ኢዮርብዓምም፡ ዕጣን፡እያጠነ፡በመሠዊያው፡አጠገብ፡ቆሞ፡ነበር።

2በመሠዊያውም፡ላይ፦መሠዊያ፡ሆይ፥መሠዊያ፡ሆይ፥እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥ስሙ፡ ኢዮስያስ፡የሚባል፡ልጅ፡ለዳዊት፡ቤት፡ይወለዳል፤ዕጣንም፡የሚያጥኑብኽን፡የኰረብታ፡መስገጃዎቹን፡ካህናት፡ ይሠዋብኻል፥የሰዎቹንም፡ዐጥንት፡ያቃጥልብኻል፡ብሎ፡በእግዚአብሔር፡ቃል፡ጮኸ።

3በዚያም፡ቀን፦እግዚአብሔር፡የተናገረው፡ምልክት፡ይህ፡ነው፤እንሆ፥መሠዊያው፡ይሰነጠቃል፥በላዩም፡ ያለው፡ዐመድ፡ይፈሳ፟ል፡ብሎ፡ምልክት፡ሰጠ። http://www.gzamargna.net

4ንጉሡም፡የእግዚአብሔር፡ሰው፡በቤቴል፡ባለው፡መሠዊያ፡ላይ፡የጮኸውን፡ነገር፡በሰማ፡ ጊዜ፥ኢዮርብዓም፡እጁን፡ከመሠዊያው፡አንሥቶ፦ያዙት፡አለ።በርሱም፡ላይ፡የዘረጋት፡እጅ፡ደረቀች፥ወደ፡ ርሱም፡ይመልሳት፡ዘንድ፡አልተቻለውም።

5የእግዚአብሔርም፡ሰው፡በእግዚአብሔር፡ቃል፡እንደ፡ሰጠው፡ምልክት፡መሠዊያው፡ተሰነጠቀ፥ዐመዱም፡ ከመሠዊያው፡ፈሰሰ።

6ንጉሡም፡የእግዚአብሔርን፡ሰው፦አኹን፡የአምላክኽን፡የእግዚአብሔርን፡ፊት፡ለምን፥እጄም፡ወደ፡እኔ፡ ትመለስ፡ዘንድ፡ስለ፡እኔ፡ጸልይ፡አለው።የእግዚአብሔርም፡ሰው፡እግዚአብሔርን፡ለመነ፥የንጉሡም፡እጅ፡ ወደ፡ርሱ፡ተመለሰች፥እንደ፡ቀድሞም፡ኾነች።

7ንጉሡም፡የእግዚአብሔርን፡ሰው፦ከእኔ፡ጋራ፡ወደ፡ቤቴ፡ና፡እንጀራም፡ብላ፥በረከትም፡እሰጥኻለኹ፡ አለው።

8የእግዚአብሔርም፡ሰው፡ንጉሡን፦የቤትኽን፡እኩሌታ፡እንኳ፡ብትሰጠኝ፡ከአንተ፡ጋራ፡ አልገባም፥በዚህም፡ስፍራ፡እንጀራ፡አልበላም፥ውሃም፡አልጠጣም፤

9እንጀራ፡አትብላ፥ውሃም፡አትጠጣ፥በመጣኽበትም፡መንገድ፡አትመለስ፡በሚል፡በእግዚአብሔር፡ቃል፡ ታዝዤያለኹና፡አለው።

10በሌላም፡መንገድ፡ኼደ፥ወደ፡ቤቴልም፡በመጣበት፡መንገድ፡አልተመለሰም።

11በቤቴልም፡አንድ፡ሽማግሌ፡ነቢይ፡ይቀመጥ፡ነበር፤ልጆቹም፡ወደ፡ርሱ፡መጥተው፡በዚያ፡ቀን፡ የእግዚአብሔር፡ሰው፡በቤቴል፡ያደረገውን፡ሥራ፡ዅሉ፡ነገሩት፡ደግሞም፡ለንጉሡ፡የተናገረውን፡ቃል፡ዅሉ፡ ለአባታቸው፡ነገሩት።

12አባታቸውም፦በማናቸው፡መንገድ፡ኼደ፧አላቸው።ልጆቹም፡ከይሁዳ፡የመጣው፡የእግዚአብሔር፡ሰው፡ የኼደበትን፡መንገድ፡አመለከቱት።

13ልጆቹንም፦አህያውን፡ጫኑልኝ፡አላቸው፤አህያውንም፡በጫኑለት፡ጊዜ፡ተቀመጠበት።

14ከእግዚአብሔርም፡ሰው፡በዃላ፡ኼደ፤በአድባርም፡ዛፍ፡በታች፡ተቀምጦ፡አገኘውና።ከይሁዳ፡የመጣኽ፡ የእግዚአብሔር፡ሰው፡አንተ፡ነኽን፧አለው።ርሱም፦እኔ፡ነኝ፡አለ።

15ርሱም፦ከእኔ፡ጋራ፡ወደ፡ቤቴ፡ና፥እንጀራም፡ብላ፡አለው።

16ርሱም፦ከአንተ፡ጋራ፡እመለስና፡እገባ፡ዘንድ፡አይቻለኝም፤በዚህም፡ስፍራ፡ከአንተ፡ጋራ፡እንጀራ፡ አልበላም፥ውሃም፡አልጠጣም፤

17በዚያ፡እንጀራ፡አትብላ፥ውሃም፡አትጠጣ፥በመጣኽበትም፡መንገድ፡አትመለስ፡በሚል፡በእግዚአብሔር፡ ቃል፡ተብሎልኛልና፥አለ።

18ርሱም፦እኔ፡ደግሞ፡እንደ፡አንተ፡ነቢይ፡ነኝ፤መልአክም፦እንጀራ፡ይበላ፡ዘንድ፡ውሃም፡ይጠጣ፡ ዘንድ፡ከአንተ፡ጋራ፡ወደ፡ቤትኽ፡መልሰው፡ብሎ፡በእግዚአብሔር፡ቃል፡ተናገረኝ፡አለው።ዋሽቶም፡ ተናገረው።

19ከርሱም፡ጋራ፡ተመለሰ፥በቤቱም፡እንጀራ፡በላ፥ውሃም፡ጠጣ።

20በማእዱም፡ተቀምጠው፡ሳሉ፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ወደመለሰው፡ነቢይ፡መጣ፤

21ከይሁዳም፡ወደመጣው፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ሰው፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በእግዚአብሔር፡አፍ፡ ላይ፡ዐምፀኻልና፥አምላክኽም፡እግዚአብሔር፡ያዘዘኽን፡ትእዛዝ፡አልጠበቅኽምና፥

22ተመልሰኽም፦እንጀራ፡አትብላ፥ውሃም፡አትጠጣ፡ባለኽ፡ስፍራ፡እንጀራ፡በልተኻልና፥ውሃም፡ ጠጥተኻልና፥ሬሳኽ፡ወዳባቶችኽ፡መቃብር፡አይደርስም፡ብሎ፡ጮኸ።

23እንጀራም፡ከበላ፥ውሃም፡ከጠጣ፡በዃላ፡አህያውን፡ጫነለት። http://www.gzamargna.net

24ተመልሶም፡በኼደ፡ጊዜ፡በመንገዱ፡ላይ፡አንበሳ፡አግኝቶ፡ገደለው፤ሬሳውም፡በመንገድ፡ላይ፡ተጋድሞ፡ ነበር፥አህያውም፡በርሱ፡አጠገብ፡ቆሞ፡ነበር፤አንበሳውም፡ደግሞ፡በሬሳው፡አጠገብ፡ቆሞ፡ነበር።

25እንሆም፥መንገድ፡ዐላፊ፡ሰዎች፡ሬሳው፡በመንገዱ፡ወድቆ፡አንበሳውም፡በሬሳው፡አጠገብ፡ቆሞ፡አዩ፡ መጥተውም፡ሽማግሌው፡ነቢይ፡ተቀምጦባት፡በነበረው፡ከተማ፡አወሩ።

26ያም፡ከመንገድ፡የመለሰው፡ነቢይ፡ያን፡በሰማ፡ጊዜ፦በእግዚአብሔር፡አፍ፡ላይ፡ያመፀ፡ያ፡ የእግዚአብሔር፡ሰው፡ነው፤እግዚአብሔር፡እንደተናገረው፡ቃል፥እግዚአብሔር፡ለአንበሳ፡አሳልፎ፡ ሰጥቶታል፤ሰብሮም፡ገድሎታል፡አለ።

27ልጆቹንም፦አህያ፡ጫኑልኝ፡አላቸው፤እነርሱም፡ጫኑለት።

28ኼደም፥ሬሳውም፡በመንገድ፡ወድቆ፥በሬሳውም፡አጠገብ፡አህያውና፡አንበሳው፡ቆመው፥አንበሳው፡ ሬሳውን፡ሳይበላው፥አህያውንም፡ሳይሰብረው፡አገኘ።

29ነቢዩም፡የእግዚአብሔርን፡ሰው፡ሬሳ፡አነሣ፥በአህያውም፡ላይ፡ጭኖ፡መለሰው፤ያለቅስለትና፡ይቀብረው፡ ዘንድ፡ወደገዛ፡ከተማው፡ይዞት፡መጣ።

30ሬሳውንም፡በገዛ፡መቃብሩ፡አኖረው፤ዋይ፡ዋይ፡ወንድሜ፡ሆይ፡እያሉ፡አለቀሱለት።

31ከቀበረውም፡በዃላ፡ልጆቹን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገራቸው፦በሞትኹ፡ጊዜ፡የእግዚአብሔር፡ሰው፡ በተቀበረበት፡መቃብር፡ቅበሩኝ፤ዐጥንቶቼንም፡በዐጥንቶቹ፡አጠገብ፡አኑሩ፤

32በቤቴል፡ባለው፡መሠዊያ፡ላይ፥በሰማርያም፡ከተማዎች፡ውስጥ፡ባሉ፡በኰረብታዎቹ፡መስገጃዎች፡ላይ፡ በእግዚአብሔር፡ቃል፡የጮኸው፡ነገር፡በእውነት፡ይደርሳልና።

33ከዚህም፡በዃላ፡ኢዮርብዓም፡ከክፉ፡መንገድ፡አልተመለሰም፥ነገር፡ግን፥ለኰረብታዎቹ፡መስገጃዎች፡ አብልጦ፡ከሕዝብ፡ዅሉ፡ካህናትን፡አደረገ፤የሚወደ፟ውንም፡ዅሉ፡ይቀድስ፡ነበር፥ርሱም፡ለኰረብታዎቹ፡ መስገጃዎች፡ካህን፡ይኾን፡ነበር።

34እስኪፈርስም፡ከምድርም፡እስኪጠፋ፡ድረስ፡ይህ፡ነገር፡ለኢዮርብዓም፡ቤት፡ኀጢአት፡ኾነ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source