Skip to content
← 1 Kings

Chapter 12 · Amharic

1 Kings

1እስራኤል፡ዅሉ፡ያነግሡት፡ዘንድ፡ወደ፡ሴኬም፡መጥተው፡ነበርና፥ሮብዓም፡ወደ፡ሴኬም፡ኼደ።

2እንዲህም፡ኾነ፤የናባጥ፡ልጅ፡ኢዮርብዓም፡ይህን፡በሰማ፡ጊዜ፥ርሱም፡ከንጉሡ፡ከሰሎሞን፡ፊት፡ኰብሎ፟፡ በግብጽ፡ተቀምጦ፡ነበርና፥በግብጽም፡ሳለ፡ልከው፡ጠርተውት፡ነበርና፥

3ኢዮርብዓምና፡የእስራኤል፡ጉባኤ፡ዅሉ፡መጥተው፡ለሮብዓም።

4አባትኽ፡ቀንበር፡አክብዶብን፡ነበር፤አኹንም፡አንተ፡ጽኑውን፡የአባትኽን፡አገዛዝ፥በላያችንም፡የጫነውን፡ የከበደውን፡ቀንበር፡አቃል፟ልን፤እኛም፡እንገዛልኻለን፡ብለው፡ተናገሩት።

5ርሱም፦ኺዱ፥በሦስተኛውም፡ቀን፡ወደ፡እኔ፡ተመለሱ፡አላቸው።ሕዝቡም፡ኼዱ።

6ንጉሡም፡ሮብዓም፦ለዚህ፡ሕዝብ፡እመልስለት፡ዘንድ፡የምትመክሩኝ፡ምንድር፡ነው፧ብሎ፡አባቱ፡ ሰሎሞን፡በሕይወቱ፡ሳለ፡በፊቱ፡ይቆሙ፡ከነበሩት፡ሽማግሌዎች፡ጋራ፡ተማከረ።

7እነርሱም፦ለዚህ፡ሕዝብ፡አኹን፡ባሪያ፡ብትኾን፡ብትገዛላቸውም፥መልሰኽም፡በገርነት፡ ብትናገራቸው፥በዘመኑ፡ዅሉ፡ባሪያዎች፡ይኾኑልኻል፡ብለው፡ተናገሩት።

8ርሱ፡ግን፡ሽማግሌዎች፡የመከሩትን፡ምክር፡ትቶ፡ከርሱ፡ጋራ፡ካደጉትና፡በፊቱ፡ይቆሙ፡ከነበሩት፡ ብላቴናዎች፡ጋራ፡ተማከረ።

9ርሱም፦አባትኽ፡የጫኑብንን፡ቀንበር፡አቃል፟ልን፡ለሚሉኝ፡ሕዝብ፡እመልስላቸው፡ዘንድ፡የምትመክሩኝ፡ ምንድር፡ነው፧አላቸው።

10ከርሱም፡ጋራ፡ያደጉት፡ብላቴናዎች፦አባትኽ፡ቀንበር፡አክብዶብናል፥አንተ፡ግን፡አቃል፟ልን፡ለሚሉኽ፡ ሕዝብ።ታናሺቱ፡ጣቴ፡ከአባቴ፡ወገብ፡ትወፍራለች።

11አኹንም፡አባቴ፡ከባድ፡ቀንበር፡ጭኖባችዃል፥እኔ፡ግን፡በቀንበራችኹ፡ላይ፡እጨምራለኹ፤አባቴ፡ በዐለንጋ፡ገርፏችዃል፥እኔ፡ግን፡በጊንጥ፡እገርፋችዃለኹ፡በላቸው፡ብለው፡ተናገሩት።

12ንጉሡም፦በሦስተኛው፡ቀን፡ወደ፡እኔ፡ተመለሱ፡ብሎ፡እንደ፡ተናገረ፡ኢዮርብዓምና፡ሕዝቡ፡ዅሉ፡ በሦስተኛው፡ቀን፡ወደ፡ሮብዓም፡መጡ።

13ንጉሡም፡ሽማግሌዎች፡የመከሩትን፡ምክር፡ትቶ፡ለሕዝቡ፡ጽኑ፡ምላሽ፡መለሰላቸው።

14እንደ፡ብላቴናዎችም፡ምክር።አባቴ፡ቀንበር፡አክብዶባችኹ፡ነበር፥እኔ፡ግን፡በቀንበራችኹ፡ላይ፡ እጨምራለኹ፤አባቴ፡በዐለንጋ፡ገርፏችኹ፡ነበር፥እኔ፡ግን፡በጊንጥ፡እገርፋችዃለኹ፡ብሎ፡ተናገራቸው።

15እግዚአብሔርም፡በሴሎናዊው፡በአኪያ፡አድርጎ፡ለናባጥ፡ልጅ፡ለኢዮርብዓም፡የተናገረውን፡ነገር፡ እንዲያጸና፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ተመድቦ፡ነበርና፥ንጉሡ፡ሕዝቡን፡አልሰማም።

16እስራኤልም፡ዅሉ፡ንጉሡ፡እንዳልሰማቸው፡ባዩ፡ጊዜ፡ሕዝቡ፡ለንጉሡ።በዳዊት፡ዘንድ፡ምን፡ክፍል፡ አለን፧በእሴይም፡ልጅ፡ዘንድ፡ርስት፡የለንም።እስራኤል፡ሆይ፥ወደ፡ድንኳኖቻችኹ፡ተመለሱ፤ዳዊት፡ ሆይ፥አኹን፡ቤትኽን፡ተመልከት፡ብለው፡መለሱለት።እስራኤልም፡ወደ፡ድንኳኖቻቸው፡ኼዱ።

17በይሁዳ፡ከተማዎች፡በተቀመጡት፡በእስራኤል፡ልጆች፡ላይ፡ግን፡ሮብዓም፡ነገሠባቸው።

18ንጉሡም፡ሮብዓም፡አስገባሪውን፡አዶኒራምን፡ሰደደ፤እስራኤልም፡ዅሉ፡በድንጋይ፡ http://www.gzamargna.net ደበደቡት፥ሞተም።ንጉሡም፡ሮብዓም፡ፈጥኖ፡ወደ፡ሠረገላው፡ወጣ፡ወደ፡ኢየሩሳሌምም፡ሸሸ።

19እስራኤልም፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡ከዳዊት፡ቤት፡ሸፈተ።

20እስራኤልም፡ዅሉ፡ኢዮርብዓም፡እንደ፡ተመለሰ፡በሰሙ፡ጊዜ፡ልከው፡ወደ፡ሸንጓቸው፡ ጠሩት፥በእስራኤልም፡ዅሉ፡ላይ፡አነገሡት።ከብቻው፡ከይሁዳ፡ነገድ፡በቀረ፡የዳዊትን፡ቤት፡የተከተለ፡አንድ፡ ሰው፡አልነበረም።

21ሮብዓምም፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡መጣ፥የእስራኤልንም፡ቤት፡ወግተው፡መንግሥቱን፡ወደሰሎሞን፡ልጅ፡ ወደ፡ሮብዓም፡ይመልሱ፡ዘንድ፡ከይሁዳ፡ቤት፡ዅሉና፡ከብንያም፡ነገድ፡የተመረጡትን፡አንድ፡መቶ፡ሰማንያ፡ ሺሕ፡ሰልፈኛዎች፡ሰዎች፡ሰበሰበ።

22የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደእግዚአብሔር፡ሰው፡ወደ፡ሳማያ።

23ለይሁዳ፡ንጉሥ፡ለሰሎሞን፡ልጅ፡ለሮብዓምና፡ለይሁዳ፡ለብንያምም፡ቤት፡ዅሉ፡ለቀረውም፡ሕዝብ፡ ዅሉ፦

24እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ይህ፡ነገር፡ከእኔ፡ዘንድ፡ነውና፥አትውጡ፥የእስራኤልንም፡ልጆች፡ ወንድሞቻችኹን፡አትውጉ፤እያንዳንዱም፡ወደ፡ቤቱ፡ይመለስ፡ብለኽ፡ንገራቸው፡ሲል፡ መጣ።የእግዚአብሔርንም፡ቃል፡ሰሙ፥እንደእግዚአብሔርም፡ቃል፡ተመልሰው፡ኼዱ።

25ኢዮርብዓምም፡በተራራማው፡በኤፍሬም፡አገር፡ሴኬምን፡ሠርቶ፡በዚያ፡ተቀመጠ፤ደግሞም፡ከዚያ፡ ወጥቶ፡ጵኒኤልን፡ሠራ።

26ኢዮርብዓምም፡በልቡ፦አኹን፡መንግሥቱ፡ወደዳዊት፡ቤት፡ይመለሳል።

27ይህ፡ሕዝብ፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡መሥዋዕትን፡ያቀርብ፡ዘንድ፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ቢወጣ፥የዚህ፡ ሕዝብ፡ልብ፡ወደ፡ጌታቸው፡ወደይሁዳ፡ንጉሥ፡ወደ፡ሮብዓም፡ይመለሳል፥እኔንም፡ይገድሉኛል፡አለ።

28ንጉሡም፡ተማከረ፥ኹለትም፡የወርቅ፡ጥጃዎች፡አድርጎ፦እስራኤል፡ሆይ፥ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ትወጡ፡ ዘንድ፡ይበዛባችዃል፤ከግብጽ፡ምድር፡ያወጡኽን፡አማልክትኽን፡እይ፡አላቸው።

29አንዱን፡በቤቴል፥ኹለተኛውንም፡በዳን፡አኖረ።

30ለአንዱ፡ጥጃ፡ይሰግድ፡ዘንድ፡ሕዝቡ፡እስከ፡ዳን፡ድረስ፡ይኼድ፡ነበርና፥ይህ፡ኀጢአት፡ኾነ።

31በኰረብታዎቹም፡ላይ፡መስገጃዎች፡ሠራ፥ከሌዊ፡ልጆች፡ካይደሉ፡ከሕዝብ፡ዅሉ፡ካህናትን፡አደረገ።

32በስምንተኛው፡ወር፡በዐሥራ፡ዐምስተኛውም፡ቀን፡በይሁዳ፡እንደሚደረግ፡በዓል፡ያለ፡በዓል፡ አደረገ፥በመሠዊያውም፡ላይ፡ሠዋ፤ለሠራቸውም፡ጥጃዎች፡ይሠዋ፡ዘንድ፡እንዲሁ፡በቤቴል፡ አደረገ፤ለኰረብታ፡መስገጃዎችም፡የመረጣቸውን፡ካህናት፡በቤቴል፡አኖራቸው።

33በስምንተኛውም፡ወር፡በዐሥራ፡ዐምስተኛው፡ቀን፡በልቡ፡ባሰበው፡ቀን፡በቤቴል፡በሠራው፡መሠዊያ፡ላይ፡ ሠዋ፤ለእስራኤልም፡ልጆች፡በዓል፡አደረገላቸው፤በመሠዊያውም፡ሠዋ፥ዕጣንም፡ዐጠነ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source