Skip to content
← 1 Kings

Chapter 11 · Amharic

1 Kings

1ንጉሡም፡ሰሎሞን፡ከፈርዖን፡ልጅ፡ሌላ፥በሞዐባውያንና፡በአሞናውያን፡በኤዶማውያን፡በሲዶናውያንና፡ http://www.gzamargna.net በኬጢያውያን፡ሴቶች፥በብዙ፡እንግዳዎች፡ሴቶች፡ፍቅር፡ተነደፈ።

2እግዚአብሔር፡የእስራኤልን፡ልጆች።አምላኮቻቸውን፡ትከተሉ፡ዘንድ፡ልባችኹን፡በእውነት፡ያዘነብላሉና፡ ወደ፡እነርሱ፡አትግቡ፥እነርሱም፡ወደ፡እናንተ፡አይግቡ፡ካላቸው፡ከአሕዛብ፥ከነዚህ፡ጋራ፡ሰሎሞን፡በፍቅር፡ ተጣበቀ።

3ለርሱም፡ወይዛዝር፡የኾኑ፡ሰባት፡መቶ፡ሚስቶች፡ሦስት፡መቶም፡ቁባቶች፡ነበሩት፤ሚስቶቹም፡ልቡን፡ አዘነበሉት።

4ሰሎሞንም፡ሲሸመግል፡ሚስቶቹ፡ሌላዎችን፡አማልክት፡ይከተል፡ዘንድ፡ልቡን፡አዘነበሉት፤የአባቱ፡የዳዊት፡ ልብ፡ከአምላኩ፡ከእግዚአብሔር፡ጋራ፡ፍጹም፡እንደ፡ነበረ፡የሰሎሞን፡ልቡ፡እንዲሁ፡አልነበረም።

5ሰሎሞንም፡የሲዶናውያንን፡አምላክ፡ዐስታሮትን፥የአሞናውያንንም፡ርኵሰት፡ሚልኮምን፥ተከተለ።

6ሰሎሞንም፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ክፉ፡ነገርን፡አደረገ፥እንደ፡አባቱም፡እንደ፡ዳዊት፡እግዚአብሔርን፡ በመከተል፡ፍጹም፡አልኾነም።

7በዚያን፡ጊዜም፡ሰሎሞን፡ለሞዐብ፡ርኵሰት፡ለካሞሽ፥ለዐሞንም፡ልጆች፡ርኵሰት፡ለሞሎክ፡በኢየሩሳሌም፡ ፊት፡ለፊት፡ባለው፡ተራራ፡ላይ፡መስገጃ፡ሠራ።

8ለአማልክታቸው፡ዕጣን፡ለሚያጥኑ፡መሥዋዕትም፡ለሚሠዉ፡ለእንግዳዎች፡ሚስቶቹ፡ዅሉ፡እንዲሁ፡ አደረገ።

10ኹለት፡ጊዜም፡ከተገለጠለት፥ሌላዎችንም፡አማልክት፡እንዳይከተል፡ካዘዘው፡ከእስራኤል፡አምላክ፡ ከእግዚአብሔር፡ልቡን፡አርቋልና፥እግዚአብሔርም፡ያዘዘውን፡ነገር፡አልጠበቀምና፡እግዚአብሔር፡ሰሎሞንን፡ ተቈጣ።

11እግዚአብሔርም፡ሰሎሞንን፡አለው፦ይህን፡ሠርተኻልና፥ያዘዝኹኽንም፡ቃል፡ኪዳኔንና፡ሥርዐቴን፡ አልጠበቅኽምና፡መንግሥትኽን፡ከአንተ፡ቀዳድጄ፡ለባሪያኽ፡እሰጠዋለኹ።

12ነገር፡ግን፥ከልጅኽ፡እጅ፡እቀደ፟ዋለኹ፡እንጂ፡ስለ፡አባትኽ፡ስለ፡ዳዊት፡ይህን፡በዘመንኽ፡አላደርግም።

13ነገር፡ግን፥ስለ፡ባሪያዬ፡ስለ፡ዳዊትና፡ስለመረጥዃት፡ስለ፡ኢየሩሳሌም፡ለልጅኽ፡አንድ፡ነገድ፡ እሰጣለኹ፡እንጂ፡መንግሥቱን፡ዅሉ፡አልቀድ፟ም።

14እግዚአብሔርም፡ከኤዶምያስ፡ነገሥታት፡ዘር፡የኤዶምያስን፡ሰው፡ሃዳድን፡ጠላት፡አድርጎ፡በሰሎሞን፡ላይ፡ አስነሣው።

16ኢዮአብና፡እስራኤልም፡ዅሉ፡የኤዶምያስን፡ወንድ፡ዅሉ፡እስኪገድሉ፡ድረስ፡ስድስት፡ወር፡በዚያ፡ ተቀምጠው፡ነበርና፥ዳዊት፡በኤዶምያስ፡በነበረ፡ጊዜ፥የሰራዊቱም፡አለቃ፡ኢዮአብ፡ተወግተው፡የሞቱትን፡ ሊቀብር፡በወጣ፡ጊዜ፥የኤዶምያስንም፡ወንድ፡ዅሉ፡በገደለ፡ጊዜ፥

17ሃዳድ፡ገና፡ብላቴና፡ሳለ፡ሃዳድና፡ከርሱ፡ጋራ፡ጥቂቶቹ፡ከኤዶምያስ፡ሰዎች፡የኾኑ፡የአባቱ፡ባሪያዎች፡ ወደ፡ግብጽ፡ኰብልለው፡ነበር።

18ከምድያምም፡ተነሥተው፡ወደ፡ፋራን፡መጡ፤ከነርሱም፡ጋራ፡ከፋራን፡ሰዎች፡ወሰዱ፥ወደ፡ግብጽም፡ መጡ፥ወደ፡ግብጽም፡ንጉሥ፡ወደ፡ፈርዖን፡ዘንድ፡ገቡ፤ርሱም፡ቤት፡ሰጥቶ፡ቀለብ፡ዳረገው፥ምድርም፡ ሰጠው።

19የሚስቱንም፡የእቴጌዪቱን፡የቴቄምናስን፡እኅት፡እስኪያጋባው፡ድረስ፡ሃዳድ፡በፈርዖን፡ፊት፡እጅግ፡ ባለሟል፡ኾነ።

20የቴቄምናስ፡እኅት፡ጌንባትን፡ወለደችለት፥ቴቄምናስም፡በፈርዖን፡ቤት፡አሳደገችው፤ጌንባትም፡በፈርዖን፡ ቤት፡በፈርዖን፡ልጆች፡መካከል፡ነበረ።

21ሃዳድም፡በግብጽ፡ሳለ፡ዳዊት፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡እንዳንቀላፋ፥የሰራዊቱም፡አለቃ፡ኢዮአብ፡እንደ፡ሞተ፡ http://www.gzamargna.net በሰማ፡ጊዜ፥ሃዳድ፡ፈርዖንን፦ወደ፡አገሬ፡እኼድ፡ዘንድ፡አሰናብተኝ፡አለው።

22ፈርዖንም፦እንሆ፥ከእኔ፡ዘንድ፡ወደ፡አገርኽ፡መኼድ፡የፈለግኽ፡ምን፡ዐጥተኽ፡ ነው፧አለው።ርሱም፦አንዳች፡አላጣኹም፤ነገር፡ግን፥ልኺድ፡ብሎ፡መለሰ።ሃዳድም፡ወደ፡አገሩ፡ ተመለሰ፥ሃዳድም፡ያደረገው፡ክፉ፡ነገር፡ይህ፡ነው፤እስራኤልን፡አስጨነቀ፥በኤዶምያስም፡ላይ፡ነገሠ።

23እግዚአብሔርም፡ደግሞ፡ከጌታው፡ከሱባ፡ንጉሥ፡ከአድርዐዛር፡የኰበለለውን፡የኤልያዳን፡ልጅ፡ሬዞንን፡ ጠላት፡አድርጎ፡አስነሣበት።

24ዳዊትም፡የሱባን፡ሰዎች፡በገደለ፡ጊዜ፡ሬዞን፡ሰዎችን፡ሰብስቦ፡የጭፍራ፡አለቃ፡ኾነ፤ወደ፡ደማስቆም፡ ኼዱ፥በዚያም፡ተቀመጡ፤በደማስቆም፡ላይ፡አነገሡት።

25ሃዳድም፡ካደረገው፡ክፋት፡ሌላ፡በሰሎሞን፡ዘመን፡ዅሉ፡የእስራኤል፡ጠላት፡ነበረ።

26ከሳሪራ፡አገር፡የኾነ፡የሰሎሞን፡ባሪያ፡የኤፍሬማዊው፡የናባጥ፡ልጅ፡ኢዮርብዓም፡በንጉሡ፡ላይ፡ ዐመፀ፤እናቱም፡ጽሩዓ፡የተባለች፡ባልቴት፡ሴት፡ነበረች።

27በንጉሡም፡ያመፀበት፡ምክንያት፡ይህ፡ነው፤ሰሎሞን፡ሚሎን፡ሠራ፥የአባቱንም፡የዳዊትን፡ከተማ፡ ሰባራውን፡ጠገነ።

28ኢዮርብዓምም፡ጽኑዕ፡ኀያል፡ሰው፡ነበረ፤ሰሎሞንም፡ጕልማሳው፡በሥራ፡የተመሰገነ፡መኾኑን፡ባየ፡ጊዜ፡ በዮሴፍ፡ነገድ፡ሥራ፡ዅሉ፡ላይ፡ሾመው።

29በዚያን፡ጊዜም፡ኢዮርብዓም፡ከኢየሩሳሌም፡በወጣ፡ጊዜ፡ሴሎናዊው፡ነቢዩ፡አኪያ፡በመንገድ፡ላይ፡ ተገናኘው፤አኪያም፡ዐዲስ፡ልብስ፡ለብሶ፡ነበር፡ኹለቱም፡በሜዳው፡ለብቻቸው፡ነበሩ።

30አኪያም፡የለበሰውን፡ዐዲስ፡ልብስ፡ይዞ፡ከዐሥራ፡ኹለት፡ቈራረጠው።

31ኢዮርብዓምንም፡አለው፦ዐሥር፡ቍራጭ፡ውሰድ፤የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ ይላልና፦እንሆ፥ከሰሎሞን፡እጅ፡መንግሥቱን፡እቀዳ፟ለኹ፥ዐሥሩንም፡ነገዶች፡እሰጥኻለኹ፤

32ስለ፡ባሪያዬ፡ስለ፡ዳዊት፡ከእስራኤልም፡ነገድ፡ስለመረጥዃት፡ከተማ፡ስለ፡ኢየሩሳሌም፡ግን፡አንድ፡ ነገድ፡ይቀርለታል፤

33ጥለውኛልና፥ለሲዶናውያንም፡አምላክ፡ለዐስታሮት፥ለሞዐብም፡አምላክ፡ለካሞሽ፥ለዐሞንም፡ልጆች፡ አምላክ፡ለሚልኮም፡ሰግደዋልና፥አባቱም፡ዳዊት፡እንዳደረገ፡በፊቴ፡ቅን፡ነገር፡ያደርጉ፡ዘንድ፥ሥርዐቴንና፡ ፍርዴንም፡ይጠብቁ፡ዘንድ፡በመንገዴ፡አልኼዱምና።

34መንግሥቱንም፡ዅሉ፡ከእጁ፡አልወስድም፤ትእዛዜንና፡ሥርዐቴን፡ስለጠበቀው፡ስለመረጥኹት፡ስለ፡ ባሪያዬ፡ስለ፡ዳዊት፡ግን፡በዕድሜው፡ዅሉ፡አለቃ፡አደርገዋለኹ።

35መንግሥቱንም፡ከልጁ፡እጅ፡እወስዳለኹ፥ለአንተም፡ዐሥሩን፡ነገድ፡እሰጥኻለኹ።

36ስሜንም፡ባኖርኹባት፡በዚያች፡በመረጥዃት፡ከተማ፡በኢየሩሳሌም፡ለባሪያዬ፡ለዳዊት፡በፊቴ፡ዅልጊዜ፡ መብራት፡ይኾንለት፡ዘንድ፡ለልጁ፡አንድ፡ነገድ፡እሰጠዋለኹ።

37አንተንም፡እወስድኻለኹ፥ነፍስኽም፡በወደደችው፡ዅሉ፡ላይ፡ትነግሣለች፥በእስራኤልም፡ላይ፡ንጉሥ፡ ትኾናለኽ።

38ባሪያዬም፡ዳዊት፡እንዳደረገ፥ያዘዝኹኽን፡ዅሉ፡ብትሰማ፥በመንገዴም፡ብትኼድ፥በፊቴም፡የቀናውን፡ ብታደርግ፥ሥርዐቴንና፡ትእዛዜን፡ብትጠብቅ፥ከአንተ፡ጋራ፡እኾናለኹ፥ለዳዊትም፡እንደ፡ሠራኹለት፡ጽኑ፡ ቤት፡እሠራልኻለኹ፥እስራኤልንም፡ለአንተ፡እሰጥኻለኹ።

39ስለዚህም፡የዳዊትን፡ዘር፡አስጨንቃለኹ፤ነገር፡ግን፥በዘመን፡ዅሉ፡አይደለም።

40ሰሎሞንም፡ኢዮርብዓምን፡ሊገድለው፡ወደደ፤ኢዮርብዓምም፡ተነሥቶ፡ወደ፡ግብጽ፡ ኰበለለ፥ወደግብጽም፡ንጉሥ፡ወደ፡ሺሻቅ፡መጣ፥ሰሎሞንም፡እስኪሞት፡ድረስ፡በግብጽ፡ተቀመጠ። http://www.gzamargna.net

41የቀረውም፡የሰሎሞን፡ነገር፥ያደረገውም፡ዅሉ፥ጥበቡም፥እንሆ፥በሰሎሞን፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡ተጽፏል።

42ሰሎሞንም፡በኢየሩሳሌም፡በእስራኤል፡ዅሉ፡ላይ፡የነገሠበት፡ዘመን፡አርባ፡ዓመት፡ነበረ።

43ሰሎሞንም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡አንቀላፋ፥በአባቱም፡በዳዊት፡ከተማ፡ተቀበረ፤ልጁም፡ሮብዓም፡በፋንታው፡ ነገሠ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source