Skip to content
← 1 Kings

Chapter 10 · Amharic

1 Kings

1የሳባም፡ንግሥት፡በእግዚአብሔር፡ስም፡የወጣለትን፡የሰሎሞንን፡ዝና፡በሰማች፡ጊዜ፡በእንቆቅልሽ፡ ትፈትነው፡ዘንድ፡መጣች።

2በግመሎችም፡ላይ፡ሽቱና፡እጅግ፡ብዙ፡ወርቅ፡የከበረም፡ዕንቍ፡አስጭና፡ከታላቅ፡ጓዝ፡ጋራ፡ወደ፡ ኢየሩሳሌም፡ገባች፤ወደ፡ሰሎሞንም፡በመጣች፡ጊዜ፡በልቧ፡ያለውን፡ዅሉ፡አጫወተችው።

3ሰሎሞንም፡የጠየቀችውን፡ዅሉ፡ፈታላት፤ሊፈታላት፡ያልቻለውና፡ከንጉሡ፡የተሰወረ፡ነገር፡አልነበረም።

4የሳባም፡ንግሥት፡የሰሎሞንን፡ጥበብ፡ዅሉ፥ሠርቶትም፡የነበረውን፡ቤት፥

5የማእዱንም፡መብል፥የብላቴናዎቹንም፡አቀማመጥ፥የሎሌዎቹንም፡አሠራር፡አለባበሳቸውንም፥ጠጅ፡ አሳላፊዎቹንም፥በእግዚአብሔርም፡ቤት፡የሚያሳርገውን፡መሥዋዕት፡ባየች፡ጊዜ፡ነፍስ፡አልቀረላትም።

6ንጉሡንም፡አለችው፦ስለ፡ነገርኽና፡ስለ፡ጥበብኽ፡በአገሬ፡ሳለኹ፡የሰማኹት፡ዝና፡እውነት፡ነው።

7እኔም፡መጥቼ፡በዐይኔ፡እስካይ፡ድረስ፡የነገሩኝን፡አላመንኹም፡ነበር፤እንሆም፥እኩሌታውን፡አልነገሩኝም፡ ነበር፤ጥበብኽና፡ሥራኽ፡ከሰማኹት፡ዝና፡ይበልጣል።

8በፊትኽ፡ዅልጊዜ፡የሚቆሙ፡ጥበብኽንም፡የሚሰሙ፡ሰዎችኽና፡እነዚህ፡ባሪያዎችኽ፡ምስጉኖች፡ናቸው።

9አንተን፡የወደደ፥በእስራኤልም፡ዙፋን፡ያስቀመጠኽ፡አምላክኽ፡እግዚአብሔር፡የተባረከ፡ ይኹን፤እግዚአብሔር፡እስራኤልን፡ለዘለዓለም፡ወዶ፟ታልና፥ስለዚህ፡ጽድቅና፡ፍርድ፡ታደርግ፡ዘንድ፡ንጉሥ፡ አድርጎ፡አስነሣኽ።

10ለንጉሡም፡መቶ፡ኻያ፡መክሊት፡ወርቅ፥እጅግም፡ብዙ፡ሽቱ፥የከበረም፡ዕንቍ፡ሰጠችው፤የሳባ፡ ንግሥት፡ለንጉሡ፡ለሰሎሞን፡እንደ፡ሰጠችው፡ያለ፡የሽቱ፡ብዛት፡ከዚያ፡ወዲያ፡አልመጣም፡ነበር።

11ከኦፊርም፡ወርቅ፡ያመጡ፡የኪራም፡መርከቦች፡እጅግ፡ብዙ፡የሰንደል፡ዕንጨትና፡የከበረ፡ዕንቍ፡ከኦፊር፡ አመጡ። http://www.gzamargna.net

12ንጉሡም፡ከሰንደሉ፡ዕንጨት፡ለእግዚአብሔር፡ቤትና፡ለንጉሡ፡ቤት፡መከታ፥ለመዘምራኑም፡መሰንቆና፡ በገና፡አደረገ፤እስከ፡ዛሬም፡ድረስ፡እንደዚያ፡ያለ፡የሰንደል፡ዕንጨት፡ከቶ፡አልመጣም፡አልታየምም።

13ንጉሡም፡ሰሎሞን፥በገዛ፡እጁ፡ከሰጣት፡ሌላ፥የወደደችውን፡ዅሉ፡ከርሱም፡የለመነችውን፡ዅሉ፡ለሳባ፡ ንግሥት፡ሰጣት፤ርሷም፡ተመልሳ፡ከባሪያዎቿ፡ጋራ፡ወደ፡ምድሯ፡ኼደች።

15ግብርም፡የሚያስገብሩ፡ሰዎች፡ነጋዴዎችም፡የዐረብም፡ነገሥታት፡ዅሉ፡የምድርም፡ሹማምት፡ ከሚያወጡት፡ሌላ፥በየዓመቱ፡ለሰሎሞን፡የሚመጣለት፡የወርቅ፡ሚዛን፡ስድስት፡መቶ፡ስድሳ፡ስድስት፡ መክሊት፡ወርቅ፡ነበረ።

16ንጉሡም፡ሰሎሞን፡ከጥፍጥፍ፡ወርቅ፡ኹለት፡መቶ፡አላበሽ፡አግሬ፡ጋሻ፡አሠራ፤በአንዱም፡አላባሽ፡ አግሬ፡ጋሻ፡ውስጥ፡የገባው፡ወርቅ፡ስድስት፡መቶ፡ሰቅል፡ነበረ።

17ከጥፍጥፍም፡ወርቅ፡ሦስት፡መቶ፡ጋሻ፡አሠራ፤በአንዱም፡ጋሻ፡የገባው፡ወርቅ፡ሦስት፡ምናን፡ ነበረ፤ንጉሡም፡የሊባኖስ፡ዱር፡በተባለው፡ቤት፡ውስጥ፡አኖራቸው።

18ንጉሡም፡ደግሞ፡ከዝኆን፡ጥርስ፡ታላቅ፡ዙፋን፡አሠራ፥በጥሩም፡ወርቅ፡ለበጠው።

19ወደ፡ዙፋንም፡የሚያስኼዱ፡ስድስት፡ዕርከኖች፡ነበሩ፤በስተዃላውም፡ያለው፡የዙፋኑ፡ራስ፡ክብ፡ ነበረ፤በዚህና፡በዚያ፡በመቀመጫው፡አጠገብ፡ኹለት፡የክንድ፡መደገፊያዎች፡ነበሩበት፥በመደገፊያዎቹም፡ አጠገብ፡ኹለት፡አንበሳዎች፡ቆመው፡ነበር።

20በስድስቱም፡ዕርከኖች፡ላይ፡በዚህና፡በዚያ፡ዐሥራ፡ኹለት፡አንበሳዎች፡ቆመው፡ነበር፤በመንግሥታት፡ ዅሉ፡እንዲህ፡ያለ፡ሥራ፡አልተሠራም።

21ንጉሡም፡ሰሎሞን፡የሚጠጣበት፡ዕቃ፡ዅሉ፡ወርቅ፡ነበረ፥የሊባኖስ፡ዱር፡የተባለውም፡ቤት፡ዕቃ፡ዅሉ፡ ጥሩ፡ወርቅ፡እንጂ፡ብር፡አልነበረም።በሰሎሞን፡ዘመን፡ብር፡ከቶ፡አይቈጠርም፡ነበር።

22ለንጉሡም፡ከኪራም፡መርከቦች፡ጋራ፡የተርሴስ፡መርከቦች፡ነበሩት፤በሦስት፡በሦስት፡ዓመትም፡አንድ፡ ጊዜ፡የተርሴስ፡መርከቦች፡ወርቅና፡ብር፥የዝኆንም፡ጥርስ፥ዝንጀሮና፡ዝንጕርጕር፡ወፍ፡ይዘው፡ይመጡ፡ ነበር።

23ንጉሡም፡ሰሎሞን፡በባለጠግነትና፡በጥበብ፡ከምድር፡ነገሥታት፡ዅሉ፡በልጦ፡ነበር።

24ምድርም፡ዅሉ፡እግዚአብሔር፡በልቡ፡ያኖረለትን፡ጥበቡን፡ይሰማ፡ዘንድ፡የሰሎሞንን፡ፊት፡ይመኝ፡ ነበር።

25ከነርሱም፡እያንዳንዱ፡በዓመቱ፡በዓመቱ፡ገጸ፡በረከቱን፥የብርና፡የወርቅ፡ዕቃ፥ልብስና፡የጦር፡ መሣሪያ፥ሽቱም፥ፈረሶችና፡በቅሎዎች፡እየያዘ፡ይመጣ፡ነበር።

26ሰሎሞንም፡ሠረገላዎችንና፡ፈረሰኛዎችን፡ሰበሰበ፤አንድ፡ሺሕ፡አራት፡መቶ፡ሠረገላዎች፥ዐሥራ፡ኹለት፡ ሺሕም፡ፈረሰኛዎች፡ነበሩት፥በሠረገላዎችም፡ከተማዎች፡ከንጉሡም፡ጋራ፡በኢየሩሳሌም፡አኖራቸው።

27ንጉሡም፡ብሩን፡በኢየሩሳሌም፡እንደ፡ድንጋይ፡እንዲበዛ፡አደረገው፤የዝግባም፡ዕንጨት፡ብዛት፡በቈላ፡ እንደሚበቅል፡ሾላ፡ኾነ።

28ሰሎሞንም፡ፈረሶችን፡ከግብጽና፡ከቀዌ፡አገር፡አስመጣ፤የንጉሡም፡ነጋዴዎች፡በገንዘብ፡እየገዙ፡ከቀዌ፡ ያመጧቸው፡ነበር።

29አንዱም፡ሠረገላ፡በስድስት፡መቶ፥አንዱም፡ፈረስ፡በመቶ፡ዐምሳ፡ብር፡ከግብጽ፡ይወጣ፡ ነበር።እንዲሁም፡ለኬጢያውያንና፡ለሶርያ፡ነገሥታት፡ዅሉ፡በእጃቸው፡ያወጡላቸው፡ነበር።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source