1ሰሎሞንም፡የእግዚአብሔርን፡ቤት፥የንጉሡን፡ቤትና፡ሰሎሞን፡የወደደውን፡የልቡን፡ዐሳብ፡ዅሉ፡ሠርቶ፡ በፈጸመ፡ጊዜ፥
2እግዚአብሔር፡በገባዖን፡ለሰሎሞን፡እንደ፡ተገለጠለት፡ዳግመኛ፡ተገለጠለት።
3እግዚአብሔርም፡አለው፦በፊቴ፡የጸለይኸውን፡ጸሎትኽንና፡ልመናኽን፡ሰምቻለኹ፤ለዘለዓለምም፡ስሜ፡ በዚያ፡ያድር፡ዘንድ፡ይህን፡የሠራኸውን፡ቤት፡ቀድሻለኹ፤ዐይኖቼና፡ልቤም፡በዘመኑ፡ዅሉ፡በዚያ፡ይኾናሉ።
4ዳዊትም፡አባትኽ፡በየዋህ፡ልብና፡በቅንነት፡እንደ፡ኼደ፡አንተ፡ደግሞ፡በፊቴ፡ብትኼድ፥ያዘዝኹኽንም፡ ዅሉ፡ብታደርግ፥ሥርዐቴንም፡ፍርዴንም፡ብትጠብቅ፥
5እኔ፦ከእስራኤል፡ዙፋን፡ከዘርኽ፡ሰው፡አታጣም፡ብዬ፡ለአባትኽ፡ለዳዊት፡እንደ፡ ተናገርኹ፥የመንግሥትኽን፡ዙፋን፡በእስራኤል፡ላይ፡ለዘለዓለም፡አጸናለኹ።
6እናንተና፡ልጆቻችኹ፡ግን፡እኔን፡ከመከትል፡ብትመለሱ፥የሰጠዃችኹንም፡ትእዛዜንና፡ሥርዐቴን፡ ባትጠብቁ፥ኼዳችኹም፡ሌላዎችን፡አማልክት፡ብታመልኩ፥ብትሰግዱላቸውም፥
7እስራኤልን፡ከሰጠዃቸው፡ምድር፡አጠፋቸዋለኹ፤ለስሜም፡የቀደስኹትን፡ይህን፡ቤት፡ከፊቴ፡ እጥለዋለኹ፤እስራኤልም፡በአሕዛብ፡ዅሉ፡መካከል፡ምሳሌና፡ተረት፡ይኾናሉ።
8ከፍ፡ከፍ፡ብሎ፡የነበረውም፡ይህ፡ቤት፡ባድማ፡ይኾናል፤በዚያም፡የሚያልፍ፡ዅሉ፡ እያፏጨ፦እግዚአብሔር፡በዚህ፡አገርና፡በዚህ፡ቤት፡ስለ፡ምን፡እንዲህ፡አደረገ፧ብሎ፡ይደነቃል።
9መልሰውም፦ከግብጽ፡ምድር፡አባቶቻቸውን፡ያወጣውን፡አምላካቸውን፡እግዚአብሔርን፡ትተው፡ ሌላዎችንም፡አማልክት፡ስለ፡ተከተሉ፥ስለ፡ሰገዱላቸውም፥ስለ፡አመለኳቸውም፥ስለዚህ፡እግዚአብሔር፡ይህን፡ ክፉ፡ነገር፡ዅሉ፡አመጣባቸው፡ይላሉ።
10ሰሎሞንም፡የእግዚአብሔርን፡ቤትና፡የንጉሡን፡ቤት፡ኹለቱን፡ቤቶች፡የሠራበት፡ኻያ፡ዓመት፡በተፈጸመ፡ ጊዜ፥
11ንጉሡ፡ሰሎሞን፡በገሊላ፡ምድር፡ያሉትን፡ኻያ፡ከተማዎች፡ለኪራም፡ሰጠው።የጢሮስም፡ንጉሥ፡ኪራም፡ የሚሻውን፡ያኽል፡የዝግባና፡የጥድ፡ዕንጨት፡የሚሻውንም፡ያኽል፡ወርቅ፡ዅሉ፡ለሰሎሞን፡ሰጥቶት፡ነበር።
12ኪራምም፡ሰሎሞን፡የሰጠውን፡ከተማዎች፡ያይ፡ዘንድ፡ከጢሮስ፡ወጣ፤ደስም፡አላሠኙትም።
13ርሱም፦ወንድሜ፡ሆይ፥የሰጠኸኝ፡እነዚህ፡ከተማዎች፡ምንድር፡ናቸው፧አለ።እስከ፡ዛሬም፡ድረስ፡ የከቡል፡አገር፡ተብለው፡ተጠሩ።
14ኪራምም፡መቶ፡ኻያ፡መክሊት፡ወርቅ፡ለንጉሡ፡ላከ።
15ንጉሡም፡ሰሎሞን፡የእግዚአብሔርን፡ቤትና፡የራሱን፡ቤት፥ሚሎንም፥የኢየሩሳሌምንም፡ ቅጥር፥ሐጾርንም፥መጊዶንም፥ጌዝርንም፡ይሠራ፡ዘንድ፡ገባሮችን፡መልምሎ፡ነበር።
16የግብጽም፡ንጉሥ፡ፈርዖን፡ወጥቶ፡ጌዝርን፡ይዞ፡ነበር፥በእሳትም፡አቃጥሎ፡ነበር፥በከተማም፡የኖሩትን፡ ከነዓናውያን፡ገድሎ፡ነበር፤ለልጁም፡ለሰሎሞን፡ሚስት፡ትሎት፡አድርጎ፡ሰጥቷት፡ነበር።
17ሰሎሞንም፡ጌዝርን፥የታችኛውንም፡ቤት፡
18ሖሮን፥ባዕላትንም፥በምድረ፡በዳም፡አገር፡ያለችውን፡ተድሞርን፥
19ለሰሎሞንም፡የነበሩትን፡የዕቃ፡ቤት፡ከተማዎች፡ዅሉ፥የሠረገላውንም፡ከተማዎች፥የፈረሰኛዎችንም፡ ከተማዎች፥በኢየሩሳሌምም፡በሊባኖስም፡በመንግሥቱም፡ምድር፡ዅሉ፡ሰሎሞን፡ይሠራ፡ዘንድ፡የወደደውን፡ ዅሉ፡ሠራ።
20ከእስራኤልም፡ልጆች፡ዘንድ፡ያልነበሩትን፡ከአሞራውያንና፡ከኬጢያውያን፥ከፌርዛውያን፥ከዔዊያውያንና፡ ከኢያቡሳውያን፡የቀሩትን፥
21የእስራኤልም፡ልጆች፡ያጠፏቸው፡ዘንድ፡ያልቻሉትን፥በዃላቸው፡የቀሩትን፡ልጆቻቸውን፥ሰሎሞን፡እስከ፡ http://www.gzamargna.net ዛሬ፡ድረስ፡ገባሮች፡አድርጎ፡መለመላቸው።
22ሰሎሞንም፡ከእስራኤል፡ልጆች፡ማንንም፡ባሪያ፡አላደረገም፤እነርሱ፡ግን፡ ሰልፈኛዎች፥ሎሌዎችም፥መሳፍንትም፥አለቃዎችም፥የሠረገላዎችና፡የፈረሶች፡ባልደራሶች፡ነበሩ።
23ሰሎሞንም፡በሚሠራው፡ሥራ፡ላይ፡ሠራተኛውን፡ሕዝብ፡የሚያዙ፟፡አለቃዎች፡ዐምስት፡መቶ፡ዐምሳ፡ ነበሩ።
24የፈርዖንም፡ልጅ፡ከዳዊት፡ከተማ፡ሰሎሞን፡ወደሠራላት፡ወደ፡ቤቷ፡ወጣች፡በዚያን፡ጊዜም፡ሚሎን፡ ሠራ።
25ሰሎሞንም፡በየዓመቱ፡ሦስት፡ጊዜ፡የሚቃጠለውንና፡የደኅንነቱን፡መሥዋዕት፡ለእግዚአብሔር፡በሠራው፡ መሠዊያ፡ላይ፡ያሳርግ፡ነበር፤በእግዚአብሔር፡ፊት፡ባለው፡መሠዊያ፡ላይ፡ዕጣን፡ያሳርግ፡ነበር፤ቤቱንም፡ ጨረሰ።
26ንጉሡም፡ሰሎሞን፡በኤዶምያስ፡ምድር፡በቀይ፡ባሕር፡ዳር፡በኤሎት፡አጠገብ፡ባለችው፡በዔጽዮንጋብር፡ መርከቦችን፡ሠራ።
27ኪራምም፡በእነዚያ፡መርከቦች፡ከሰሎሞን፡ባሪያዎች፡ጋራ፡የባሕሩን፡ነገር፡የሚያውቁ፡መርከበኛዎች፡ ባሪያዎቹን፡ሰደደ።
28ወደ፡ኦፊርም፡መጡ፥ከዚያም፡አራት፡መቶ፡ኻያ፡መክሊት፡ወርቅ፡ወሰዱ፥ወደ፡ንጉሡም፡ወደ፡ ሰሎሞን፡ይዘው፡መጡ።