1ሰሎሞንም፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ኪዳን፡ታቦት፡ከዳዊት፡ከተማ፡ከጽዮን፡ያወጡ፡ዘንድ፡የእስራኤልን፡ ሽማግሌዎችና፡የነገድ፡አለቃዎችን፡ዅሉ፥የእስራኤልን፡ልጆች፡የአባቶቻቸውን፡ቤቶች፡መሳፍንት፥ንጉሡ፡ ሰሎሞን፡ወዳለበት፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ሰበሰባቸው።
2የእስራኤልም፡ሰዎች፡ኤታኒም፡በሚባል፡በሰባተኛው፡ወር፡በበዓሉ፡ጊዜ፡ወደ፡ንጉሡ፡ወደ፡ሰሎሞን፡ ተከማቹ።
3የእስራኤልም፡ሽማግሌዎች፡ዅሉ፡መጡ፤ካህናቱም፡ታቦቱን፡አነሡ።
4የእግዚአብሔርንም፡ታቦት፥የመገናኛውንም፡ድንኳን፥በድንኳኑም፡ውስጥ፡የነበረውን፡የተቀደሰውን፡ዕቃ፡ ዅሉ፡አመጡ፤እነዚህንም፡ዅሉ፡ካህናቱና፡ሌዋውያኑ፡አመጡ።
5ንጉሡም፡ሰሎሞን፡ከርሱም፡ጋራ፡የተሰበሰቡ፡የእስራኤል፡ማኅበር፡ዅሉ፡ከርሱ፡ጋራ፡በታቦቱ፡ፊት፡ ኾነው፥ከብዛታቸው፡የተነሣ፡የማይቈጠሩትንና፡የማይመጠኑትን፡በጎችና፡በሬዎች፡ይሠዉ፡ነበር።
6ካህናቱም፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ኪዳን፡ታቦት፡በቤቱ፡በቅድስተ፡ቅዱሳን፡ውስጥ፡ከኪሩቤል፡ክንፍ፡ በታች፡ወደ፡ነበረው፡ወደ፡ስፍራው፡አመጡት።
7ኪሩቤልም፡በታቦቱ፡ስፍራ፡ላይ፡ክንፎቻቸውን፡ዘርግተው፡ነበር፤ኪሩቤልም፡ታቦቱንና፡መሎጊያዎቹን፡ በስተላይ፡በኩል፡ሸፍነው፡ነበር። http://www.gzamargna.net
8መሎጊያዎቹም፡ረዣዥሞች፡ነበሩ፤በቅድስተ፡ቅዱሳን፡ፊት፡ከመቅደሱ፡ውስጥ፡ጫፎቻቸው፡ይታዩ፡ ነበር፤በውጭ፡ያለ፡ግን፡አያያቸውም፡ነበር፤እስከ፡ዛሬም፡ድረስ፡በዚያ፡አሉ።
9በታቦቱም፡ውስጥ፡የእስራኤል፡ልጆች፡ከግብጽ፡ምድር፡በወጡ፡ጊዜ፥እግዚአብሔርም፡ከነርሱ፡ጋራ፡ቃል፡ ኪዳን፡ባደረገ፡ጊዜ፥ሙሴ፡በኰሬብ፡ካስቀመጣቸው፡ከኹለቱ፡የድንጋይ፡ጽላቶች፡በቀር፡ምንም፡ አልነበረበትም።
10ካህናቱም፡ከመቅደሱ፡በመጡ፡ጊዜ፡ደመናው፡የእግዚአብሔርን፡ቤት፡ሞላው።
11የእግዚአብሔርም፡ክብር፡የእግዚአብሔርን፡ቤት፡ሞልቶ፡ነበርና፥ካህናቱ፡ከደመናው፡የተነሣ፡ለማገልገል፡ ይቆሙ፡ዘንድ፡አልቻሉም።
12ሰሎሞንም፦እግዚአብሔር፦በጨለማው፡ውስጥ፡እኖራለኹ፡ብሏል፤
13እኔም፡ለዘለዓለም፡የምትኖርበት፡ማደሪያ፡ቤት፡በእውነት፡ሠራኹልኽ፡አለ።
14ንጉሡም፡ፊቱን፡ዘወር፡አድርጎ፡የእስራኤልን፡ጉባኤ፡ዅሉ፡መረቀ፤የእስራኤልም፡ጉባኤ፡ዅሉ፡ቆመው፡ ነበር።
16ርሱም፡አለ፦ሕዝቤን፡እስራኤልን፡ከግብጽ፡ካወጣኹበት፡ቀን፡ዠምሮ፡ስሜ፡በዚያ፡ይኾን፡ ዘንድ፥በርሷም፡ቤት፡ይሠራልኝ፡ዘንድ፡ከእስራኤል፡ነገድ፡ዅሉ፡ከተማ፡አልመረጥኹም፤አኹን፡ግን፡ስሜ፡ በዚያ፡ይኾን፡ዘንድ፡ኢየሩሳሌምን፡መርጫለኹ፥በሕዝቤም፡በእስራኤል፡ላይ፡ይኾን፡ዘንድ፡ዳዊትን፡ መርጫለኹ፡ብሎ፡ለአባቴ፡ለዳዊት፡በአፉ፡የተናገረ፥በእጁም፡የፈጸመ፡የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡ ይመስገን።
17አባቴም፡ዳዊት፡ለእስራኤል፡አምላክ፡ለእግዚአብሔር፡ስም፡ቤት፡ይሠራ፡ዘንድ፡በልቡ፡ዐሰበ።
18እግዚአብሔርም፡አባቴን፡ዳዊትን፦ለስሜ፡ቤት፡ትሠራ፡ዘንድ፡በልብኽ፡ዐስበኻልና፥ይህን፡በልብኽ፡ ማሰብኽ፡መልካም፡አደረግኽ።
19ነገር፡ግን፥ከወገብኽ፡የሚወጣው፡ልጅኽ፡ርሱ፡ለስሜ፡ቤት፡ይሠራል፡እንጂ፡ቤት፡የምትሠራልኝ፡ አንተ፡አይደለኽም፡አለው።
20እግዚአብሔርም፡የተናገረውን፡ቃል፡አጸና፤እግዚአብሔርም፡ተስፋ፡እንደ፡ሰጠ፡በአባቴ፡በዳዊት፡ፋንታ፡ ተነሣኹ፥በእስራኤልም፡ዙፋን፡ላይ፡ተቀመጥኹ፥ለእስራኤልም፡አምላክ፡ለእግዚአብሔር፡ስም፡ቤት፡ሠራኹ።
21ከግብጽም፡ምድር፡ባወጣቸው፡ጊዜ፡ከአባቶቻችን፡ጋራ፡ያደረገው፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ኪዳን፡ላለበት፡ ታቦት፡ስፍራ፡በዚያ፡አደረግኹለት።
22የእስራኤልም፡ጉባኤ፡ዅሉ፡እያዩ፡ሰሎሞን፡በእግዚአብሔር፡መሠዊያ፡ፊት፡ቆሞ፡እጆቹን፡ወደ፡ሰማይ፡ ዘረጋ።
23እንዲህም፡አለ፦የእስራኤል፡አምላክ፡አቤቱ፥በላይ፡በሰማይ፡በታችም፡በምድር፡አንተን፡የሚመስል፡ አምላክ፡የለም፤በፍጹም፡ልባቸው፡በፊትኽ፡ለሚኼዱ፡ባሪያዎችኽ፡ቃል፡ኪዳንንና፡ምሕረትን፡የምትጠብቅ፥
24ለባሪያኽ፡ለአባቴ፡ለዳዊት፡የሰጠኸውን፡ተስፋ፡የጠበቅኽ፤በአፍኽ፡ተናገርኽ፥እንደ፡ዛሬው፡ቀንም፡ በእጅኽ፡ፈጸምኸው።
25አኹንም፡የእስራኤል፡አምላክ፡አቤቱ።አንተ፡በፊቴ፡እንደ፡ኼድኽ፡ልጆችኽ፡መንገዳቸውን፡ ቢጠብቁ፥በእስራኤል፡ዙፋን፡የሚቀመጥ፡ሰው፡በፊቴ፡አታጣም፡ብለኽ፡ተስፋ፡የሰጠኸውን፡ለአባቴ፡ለዳዊት፡ ጠብቅ።
26አኹንም፥የእስራኤል፡አምላክ፡ሆይ፥ለባሪያኽ፡ለአባቴ፡ለዳዊት፡የተናገርኸው፡ቃል፥እባክኽ፥ይጽና።
27በእውኑ፡እግዚአብሔር፡ከሰው፡ጋራ፡በምድር፡ላይ፡ይኖራልን፧እንሆ፥ሰማይ፡ከሰማያትም፡በላይ፡ያለው፡ ሰማይ፡ይይዝኽ፡ዘንድ፡አይችልም፤ይልቁንስ፡እኔ፡የሠራኹት፡ቤት፡እንዴት፡ያንስ! http://www.gzamargna.net
28ነገር፡ግን፥አቤቱ፡አምላኬ፡ሆይ፥ወደባሪያኽ፡ጸሎትና፡ልመና፡ተመልከት፥ዛሬም፡ባሪያኽ፡በፊትኽ፡ የሚጸልየውን፡ጸሎትና፡ጥሪውን፡ስማ፤
29ባሪያኽ፡ወደዚህ፡ስፍራ፡የሚጸልየውን፡ጸሎት፡ትሰማ፡ዘንድ፦በዚያ፡ስሜ፡ይኾናል፡ወዳልኸው፡ስፍራ፡ ወደዚህ፡ቤት፡ዐይኖችኽ፡ሌሊትና፡ቀን፡የተገለጡ፡ይኹኑ።
30ባሪያኽና፡ሕዝብኽ፡እስራኤል፡ወደዚህ፡ስፍራ፡የሚጸልዩትን፡ልመና፡ስማ፤በማደሪያኽ፡በሰማይ፡ ስማ፤ሰምተኽም፡ይቅር፡በል።
31ሰው፡ባልንጀራውን፡ቢበድል፥በላዩም፡መሐላ፡ቢጫን፥ርሱም፡መጥቶ፡በዚህ፡ቤት፡በመሠዊያኽ፡ፊት፡ ቢምል፥
32በሰማይ፡ስማ፡አድርግም፤በባሪያዎችኽም፡ላይ፡ዳኛ፡ኹን፤በበደለኛውም፡ላይ፡ፍረድ፥መንገዱንም፡ በራሱ፡ላይ፡መልስበት፤ንጹሑን፡አጽድቀው፥እንደ፡ጽድቁም፡ክፈለው።
33ሕዝብኽ፡እስራኤል፡አንተን፡ስለ፡በደሉ፡በጠላቶቻቸው፡ፊት፡ድል፡በተመቱ፡ጊዜ፥ወዳንተ፡ ቢመለሱ፥ስምኽንም፡ቢያከብሩ፥በዚህም፡ቤት፡ቢጸልዩና፡ቢለምኑኽ፥
34አንተ፡በሰማይ፡ስማ፤የሕዝብኽንም፡የእስራኤልን፡ኀጢአት፡ይቅር፡በል፥ለአባቶቻቸውም፡ወደሰጠኻት፡ ምድር፡መልሳቸው።
35አንተን፡ስለ፡በደሉ፡ሰማይ፡በተዘጋ፡ጊዜ፡ዝናብም፡ባልዘነበ፡ጊዜ፥ወደዚህ፡ስፍራ፡ቢጸልዩ፥ስምኽንም፡ ቢያከብሩ፥ባስጨነቅኻቸውም፡ጊዜ፡ከኀጢአታቸው፡ቢመለሱ፥አንተ፡በሰማይ፡ስማ፤
36የሚኼዱበትንም፡መልካም፡መንገድ፡በማሳየት፡የባሪያዎችኽንና፡የሕዝብኽን፡የእስራኤልን፡ኀጢአት፡ ይቅር፡በል፤ለሕዝብኽም፡ርስት፡አድርገኽ፡ለሰጠኻት፡ምድር፡ዝናብ፡ስጥ።
37በምድር፡ላይ፡ራብ፥ወይም፡ቸነፈር፥ወይም፡ዋግ፥ወይም፡ዐረማሞ፥ወይም፡አንበጣ፥ወይም፡ኵብኵባ፡ ቢኾን፥የሕዝብኽም፡ጠላት፡የአገሩን፡ቀበሌዎች፡ከቦ፟፡ቢያስጨንቃቸው፥መቅሠፍትና፡ደዌ፡ዅሉ፡ቢኾን፥
38ማናቸውም፡ሰው፡የልቡን፡ሕመም፡ዐውቆ፡ጸሎትና፡ልመና፡ቢጸልይ፥እጆቹንም፡ወደዚህ፡ቤት፡ቢዘረጋ፥
40ለአባቶቻችን፡በሰጠኻት፡ምድር፡ላይ፡በሚኖሩበት፡ዘመን፡ዅሉ፡ይፈሩኽ፡ዘንድ፡በማደሪያኽ፡ በሰማይ፡ስማ፥ይቅርም፡በል፤አንተ፡ብቻ፡የሰውን፡ልጆች፡ዅሉ፡ልብ፡ታውቃለኽና፡ልቡን፡ለምታውቀው፡ ሰው፡ዅሉ፡እንደ፡መንገዱ፡ዅሉ፡መጠን፡ክፈለውና፡ስጠው።
42ከሕዝብኽም፡ከእስራኤል፡ወገን፡ያልኾነ፡እንግዳ፡ታላቁን፡ስምኽን፥ብርቱዪቱንም፡ እጅኽን፥የተዘረጋውንም፡ክንድኽን፡ሰምቶ፡ስለ፡ስምኽ፡ከሩቅ፡አገር፡በመጣ፡ጊዜ፥መጥቶም፡ወደዚህ፡ቤት፡ በጸለየ፡ጊዜ፥
43አንተ፡በማደሪያኽ፡በሰማይ፡ስማ፤የምድርም፡አሕዛብ፡ዅሉ፡ስምኽን፡ያውቁ፡ዘንድ፡እንደ፡ሕዝብኽም፡ እንደ፡እስራኤል፡ይፈሩኽ፡ዘንድ፥በዚህም፡በሠራኹት፡ቤት፡ስምኽ፡አንደ፡ተጠራ፡ያውቁ፡ዘንድ፥እንግዳው፡ የሚለምንኽን፡ዅሉ፡አድርግ።
44ሕዝብኽም፡ጠላቶቻቸውን፡ለመውጋት፡አንተ፡በምትልካቸው፡መንገድ፡ቢወጡ፥አንተም፡ወደመረጥኻት፡ ከተማ፡እኔም፡ለስምኽ፡ወደሠራኹት፡ቤት፡ለእግዚአብሔር፡ቢጸልዩ፥
45ጸሎታቸውንና፡ልመናቸውን፡በሰማይ፡ስማ፥ፍርድንም፡አድርግላቸው።
46የማይበድልም፡ሰው፡የለምና፡አንተን፡ቢበድሉ፥ተቈጥተኽም፡ለጠላቶቻቸው፡አሳልፈኽ፡ብትሰጣቸው፡ ሩቅ፡ወይም፡ቅርብ፡ወደ፡ኾነ፡ወደጠላቶች፡አገር፡ቢማረኩም፥
47በተማረኩበትም፡አገር፡ኾነው፡በልባቸው፡ንስሓ፡ቢገቡ፥በማራኪዎቹም፡አገር፡ሳሉ፡ ተመልሰው፦ኀጢአት፡ሠርተናል፥በድለንማል፥ክፉንም፡አድርገናል፡ብለው፡ቢለምኑኽ፥
48በማረኳቸው፡በጠላቶቻቸው፡አገር፡ሳሉ፡በፍጹም፡ልባቸውና፡በፍጹም፡ነፍሳቸው፡ወዳንተ፡ http://www.gzamargna.net ቢመለሱ፥ለአባቶቻቸው፡ወደሰጠኻት፡ወደ፡ምድራቸው፡ወደመረጥኻትም፡ከተማ፡ለስምኽም፡ወደሠራኹት፡ ቤት፡ቢጸልዩ፥
49ጸሎታቸውንና፡ልመናቸውን፡በማደሪያኽ፡በሰማይ፡ስማ፥
50ፍርድንም፡አድርግላቸው፥አንተንም፡የበደሉኽን፡ሕዝብኽን፥ባንተም፡ላይ፡ያደረጉትን፡በደላቸውን፡ዅሉ፡ ይቅር፡በል፤ይራሩላቸውም፡ዘንድ፡በማረኳቸው፡ፊት፡ምሕረት፡ስጣቸው፤
51ከግብጽ፡ምድር፡ከብረት፡እቶን፡ውስጥ፡ያወጣኻቸው፡ሕዝብኽና፡ርስትኽ፡ናቸውና።
52በጠሩኽ፡ጊዜ፡ዅሉ፡ትሰማቸው፡ዘንድ፡ለባሪያኽና፡ለሕዝብኽ፡ለእስራኤል፡ልመና፡ዐይኖችኽ፡የተገለጡ፡ ይኹኑ።
53ጌታዬ፡እግዚአብሔር፡ሆይ፥አባቶቻችንን፡ከግብጽ፡ባወጣኽ፡ጊዜ፡በባሪያኽ፡በሙሴ፡እጅ፡እንደ፡ ተናገርኽ፡ርስት፡ይኾኑኽ፡ዘንድ፡ከምድር፡አሕዛብ፡ዅሉ፡ለይተኻቸዋልና።
54ሰሎሞንም፡ይህችን፡ጸሎትና፡ልመና፡ዅሉ፡ለእግዚአብሔር፡ጸልዮ፡በፈጸመ፡ጊዜ፥በጕልበቱ፡ተንበርክኮ፡ እጁንም፡ወደ፡ሰማይ፡ዘርግቶ፡ነበርና፥ከእግዚአብሔር፡መሠዊያ፡ፊት፡ተነሣ።
55ቆሞም፡የእስራኤልን፡ጉባኤ፡ዅሉ፡በታላቅ፡ድምፅ፡ሲመርቅ፡እንዲህ፡አለ።
56እንደተናገረው፡ተስፋ፡ዅሉ፡ለሕዝቡ፡ለእስራኤል፡ዕረፍትን፡የሰጠ፡እግዚአብሔር፡ይመስገን፤በባሪያው፡ በሙሴ፡ከሰጠው፡ከመልካም፡ተስፋ፡ዅሉ፡አንድ፡ቃል፡አልወደቀም።
57አምላካችን፡እግዚአብሔር፡ከአባቶቻችን፡ጋራ፡እንደ፡ነበረ፡ከእኛ፡ጋራ፡ይኹን፤አይተወን፥አይጣለንም፤
58በመንገዱም፡ዅሉ፡እንኼድ፡ዘንድ፥ለአባቶቻችንም፡ያዘዛትን፡ሥርዐትና፡ፍርድ፡ትእዛዙንም፡እንጠብቅ፡ ዘንድ፥ልባችንን፡ወደ፡ርሱ፡ያዘነብል፡ዘንድ።
59ለባሪያውና፡ለሕዝቡ፡ለእስራኤል፡በየዕለቱ፡ፍርድን፡ያደርግ፡ዘንድ፡ይህች፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ የለመንዃት፡ቃል፡በቀንና፡በሌሊት፡ወደ፡አምላካችን፡ወደ፡እግዚአብሔር፡የቀረበች፡ትኹን፤
60የምድር፡አሕዛብ፡ዅሉ፡እግዚአብሔር፡ርሱ፡አምላክ፡እንደ፡ኾነ፥ከርሱም፡በቀር፡ሌላ፡እንደሌለ፡ያውቅ፡ ዘንድ።
61እንደ፡ዛሬው፡ቀን፡በሥርዐቱ፡ትኼዱ፡ዘንድ፥ትእዛዙንም፡ትጠብቁ፡ዘንድ፥ከአምላካችን፡ከእግዚአብሔር፡ ጋራ፡ልባችኹ፡ፍጹም፡ይኹን።
62ንጉሡም፡ከርሱም፡ጋራ፡እስራኤል፡ዅሉ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡መሥዋዕት፡ሠዉ።
63ሰሎሞንም፡ለእግዚአብሔር፡ይሠዋ፡ዘንድ፡ለደኅንነት፡መሥዋዕት፡ኻያ፡ኹለት፡ሺሕ፡በሬዎችና፡መቶ፡ ኻያ፡ሺሕ፡በጎች፡አቀረበ።ንጉሡና፡የእስራኤልም፡ልጆች፡ዅሉ፡እንዲህ፡የእግዚአብሔርን፡ቤት፡ቀደሱ።
64በእግዚአብሔር፡ፊት፡ያለው፡የናሱ፡መሠዊያ፡የሚቃጠለውን፡መሥዋዕትና፡የእኽሉን፡ቍርባን፡ የደኅንነቱንም፡መሥዋዕት፡ስብ፡ይይዝ፡ዘንድ፡ታናሽ፡ስለ፡ነበረ፥በዚያ፡የሚቃጠለውን፡መሥዋዕትና፡ የእኽሉን፡ቍርባን፡የደኅንነቱንም፡መሥዋዕት፡ስብ፡አሳርጓልና፥በእግዚአብሔር፡ቤት፡ፊት፡የነበረውን፡ የአደባባዩ፡መካከል፡ንጉሡ፡በዚያ፡ቀን፡ቀደሰ።
65በዚያም፡ዘመን፡ሰሎሞን፡ከርሱም፡ጋራ፡እስራኤል፡ዅሉ፥ከሐማት፡መግቢያ፡ዠምሮ፡እስከግብጽ፡ ወንዝ፡ድረስ፡ያለው፡ታላቅ፡ጉባኤ፥በአምላካችን፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ሰባት፡ቀን፡በዓሉን፡አደረጉ።
66በስምንተኛውም፡ቀን፡ሕዝቡን፡አሰናበተ፤እነርሱም፡ንጉሡን፡መረቁ፥እግዚአብሔርም፡ለባሪያው፡ ለዳዊትና፡ለሕዝቡ፡ለእስራኤል፡ስላደረገው፡ቸርነት፡ዅሉ፡በልባቸው፡ተደስተው፡ሐሤትም፡አድርገው፡ወደ፡ ስፍራቸው፡ኼዱ።