Skip to content
← 1 Kings

Chapter 7 · Amharic

1 Kings

1ሰሎሞንም፡የራሱን፡ቤት፡በዐሥራ፡ሦስት፡ዓመት፡ሠራ፥የቤቱንም፡ሥራ፡ዅሉ፡ጨረሰ። http://www.gzamargna.net

2የሊባኖስ፡ዱር፡ቤት፡የሚባል፡ቤትን፡ሠራ፤ርዝመቱንም፡መቶ፡ክንድ፥ስፋቱንም፡ዐምሳ፡ ክንድ፥ቁመቱንም፡ሠላሳ፡ክንድ፡አደረገ፤የዝግባም፡ዕንጨት፡በሦስት፡ተራ፡በተሠሩ፡አዕማድ፡ላይ፡ቆሞ፡ ነበር፤በአዕማዱም፡ላይ፡የዝግባ፡ዕንጨት፡አግዳሚ፡ሠረገላዎች፡ነበሩ።

3በአዕማዱም፡ላይ፡በነበሩ፡አግዳሚዎች፡ቤቱ፡በዝግባ፡ሳንቃ፡ተሸፍኖ፡ነበር፤አዕማዱም፡በአንዱ፡ተራ፡ ዐሥራ፡ዐምስት፥በአንዱ፡ተራ፡ዐሥራ፡ዐምስት፡እየኾኑ፡አርባ፡ዐምስት፡ነበሩ።

4መስኮቶቹም፡በሦስት፡ተራ፡ነበሩ፥መስኮቶቹም፡ፊት፡ለፊት፡ይተያዩ፡ነበር።

5ደጆቹና፡መስኮቶቹም፡ዅሉ፡አራት፡ማእዘን፡ነበሩ፤መስኮቶቹም፡በሦስት፡ተራ፡ኾነው፡ፊት፡ለፊት፡ ይተያዩ፡ነበር።

6አዕማዱም፡ያሉበቱን፡ቤት፡ሠራ፤ርዝመቱም፡ዐምሳ፡ክንድ፥ስፋቱም፡ሠላሳ፡ክንድ፡ነበረ፤በርሱም፡ፊት፡ ደግሞ፡አዕማድና፡መድረክ፡ያሉበት፡ወለል፡ነበረ።

7ደግሞም፡የሚፈርድበት፡ዙፋን፡ያለበትን፡የፍርድ፡ቤት፡አደረገ።ከወለሉም፡አንሥቶ፡እስከ፡ጣራው፡ ድረስ፡በዝግባ፡ዕንጨት፡ተሸፍኖ፡ነበር።

8ከፍርድ፡ሰቀላ፡ወደ፡ውስጥ፥በሌላውም፡አደባባይ፡ውስጥ፡የነበረውን፡መኖሪያ፡ቤት፡እንዲሁ፡ ሠራ።እንደዚሁም፡ያለ፡ቤት፡ሰሎሞን፡ላገባት፡ለፈርዖን፡ልጅ፡ቤት፡ሠራ።

9እነዚህም፡ዅሉ፡ከመሠረቱ፡ዠምሮ፡እስከ፡ጕልላቱ፡ድረስ፡በጥሩ፡በተጠረበና፡በውስጥና፡በውጭ፡በልክ፡ በተከረከመ፡ድንጋይ፡ተሠርተው፡ነበር፤በውጭውም፡እስከ፡ታላቁ፡አደባባይ፡ድረስ፡እንዲሁ፡ነበረ።

10መሠረቱም፡ዐሥር፡ወይም፡ስምንት፡ክንድ፡በኾነ፡በጥሩና፡በታላቅ፡ድንጋይ፡ተሠርቶ፡ነበር።

11በላዩም፡ልክ፡ኾኖ፡የተከረከመ፡ጥሩ፡ድንጋይና፡የዝግባ፡ሳንቃ፡ነበረ።

12በታላቁም፡አደባባይ፡ዙሪያ፡የነበረው፡ቅጥር፡እንደእግዚአብሔር፡ቤት፡እንደ፡ውስጠኛው፡አደባባይ፡ ቅጥርና፡እንደ፡ቤቱ፡ወለል፡ሦስቱ፡ተራ፡በተጠረበ፡ድንጋይ፡አንዱም፡ተራ፡በዝግባ፡ሳንቃ፡ተሠርቶ፡ነበር።

13ንጉሡም፡ሰሎሞን፡ልኮ፡ኪራምን፡ከጢሮስ፡አስመጣ።

14ርሱም፡ከንፍታሌም፡ወገን፡የነበረች፡የባል፡አልባ፡ሴት፡ልጅ፡ነበረ፥አባቱም፡የጢሮስ፡ሰው፡ናስ፡ ሠራተኛ፡ነበረ፤የናስንም፡ሥራ፡ዅሉ፡ይሠራ፡ዘንድ፡በጥበብና፡በማስተዋል፡በብልኀትም፡ተሞልቶ፡ ነበር።ወደ፡ንጉሡም፡ወደ፡ሰሎሞን፡መጥቶ፡ሥራውን፡ዅሉ፡ሠራ።

15ኹለቱን፡የናስ፡አዕማድ፡አደረገ፤የአንዱም፡ዐምድ፡ቁመት፡ዐሥራ፡ስምንት፡ክንድ፡ነበረ፥የዙሪያውም፡ መጠን፡ዐሥራ፡ኹለት፡ክንድ፡ነበረ፤የዐምዱም፡ውፍረት፡አንድ፡ጋት፡ነበረ፥ውስጠ፡ክፍትም፡ ነበረ።ኹለተኛውም፡ዐምድ፡እንዲሁ፡ነበረ።

16በኹለቱም፡አዕማድ፡ራስ፡ላይ፡እንዲቀመጡ፡ከፈሰሰ፡ናስ፡ኹለት፡ጕልላት፡ሠራ፤የአንዱም፡ጕልላት፡ ቁመት፡ዐምስት፡ክንድ፥የኹለተኛውም፡ጕልላት፡ቁመት፡ዐምስት፡ክንድ፡ነበረ።

17በአዕማዱም፡ራስ፡ላይ፡የነበሩትን፡ጕልላቶች፡ይሸፍኑ፡ዘንድ፡ኹለት፡እንደ፡መርበብ፡ሥራ፡ አደረገ፤አንዱም፡መርበብ፡ለአንዱ፡ጕልላት፡ኹለተኛውም፡መርበብ፡ለኹለተኛው፡ጕልላት፡ነበረ።

18ሮማኖችንም፡ሠራ፤ባንድ፡ጕልላት፡ዙሪያ፡በተራ፡ኹለት፡መቶ፡ሮማኖች፡ነበሩ፥በአንድም፡መርበብ፡ ላይ፡ኹለት፡ተራ፡ነበረ፤እንዲሁም፡ለኹለተኛው፡ጕልላት፡አደረገ።

19በወለሉም፡አዕማድ፡በነበሩት፡ጕልላቶች፡ላይ፡የሱፍ፡አበባ፡የሚመስል፡ሥራ፡አራት፡ክንድ፡አድርጎ፡ ቀረጸ።

20በኹለቱም፡አዕማድ፡በነበሩት፡ጕልላቶች፡ላይ፡በመርበቡ፡ሥራ፡አጠገብ፡ሮማኖቹን፡አደረገ።

21አዕማዱንም፡በመቅደሱ፡ወለል፡አጠገብ፡አቆማቸው፤የቀኙንም፡ዐምድ፡አቁሞ፡ያቁም፡ብሎ፡ ጠራው፤የግራውንም፡ዐምድ፡አቁሞ፡በለዝ፡ብሎ፡ጠራው። http://www.gzamargna.net

22በአዕማዱም፡ራስ፡ላይ፡የሱፍ፡አበባ፡የሚመስል፡ሥራ፡ነበረ፤እንዲሁም፡የአዕማዱ፡ሥራ፡ተጨረሰ።

23ከፈሰሰም፡ናስ፡ከዳር፡እስከ፡ዳር፡ዐሥር፡ክንድ፥ቁመቱም፡ዐምስት፡ክንድ፥በዙሪያውም፡ሠላሳ፡ክንድ፡ የኾነ፡ክብ፡ኵሬ፡ሠራ።

24ከከንፈሩም፡በታች፡ላንድ፡ክንድ፡ዐሥር፡ላንድ፡ክንድም፡ዐሥር፡ጕብጕቦች፡አዞረበት፤ርሱም፡በቀለጠ፡ ጊዜ፡ጕብጕቦቹ፡በኹለት፡ተራ፡ከርሱ፡ጋራ፡ዐብረው፡ቀልጠው፡ነበር።

25ኵሬውም፡በዐሥራ፡ኹለት፡በሬዎች፡ምስል፡ላይ፡ተቀምጦ፡ነበር፤ከነርሱም፡ሦስቱ፡ወደ፡ ሰሜን፥ሦስቱም፡ወደ፡ምዕራብ፥ሦስቱም፡ወደ፡ደቡብ፥ሦስቱም፡ወደ፡ምሥራቅ፡ይመለከቱ፡ነበር።ኵሬውም፡ በላያቸው፡ነበረ፥የዅሉም፡ዠርባቸው፡በስተውስጥ፡ነበረ።

26ውፍረቱም፡አንድ፡ጋት፡ነበረ፤ከንፈሩም፡እንደ፡ጽዋ፡ከንፈር፡ተሠርቶ፡ነበር፤እንደ፡ሱፍ፡አበባዎች፡ ኾኖ፡ተከርክሞ፡ነበር።ኹለት፡ሺሕም፡የባዶስ፡መስፈሪያ፡ይይዝ፡ነበር።

27ዐሥርም፡የናስ፡መቀመጫዎች፡ሠራ፤የአንዱም፡መቀመጫ፡ርዝመት፡አራት፡ክንድ፥ወርዱም፡አራት፡ ክንድ፥ቁመቱም፡ሦስት፡ክንድ፡ነበረ።

28የመቀመጫውም፡ሥራ፡እንዲህ፡ነበረ፤በክፈፎችም፡መካከል፡ያለው፡ሰንበር፡ይመስል፡ነበር።

29በክፈፎቹም፡መካከል፡በነበሩ፡ሰንበሮች፡ላይ፡አንበሳዎችና፡በሬዎች፡ኪሩቤልም፡ነበሩ፤እንዲሁም፡ በክፈፎቹ፡ላይ፡ነበረ፤ከአንበሳዎቹና፡ከበሬዎቹ፡በታች፡ሻኵራ፡የሚመስል፡ተንጠልጥሎ፡ነበር።

30በየመቀመጫዎቹም፡ዅሉ፡አራት፡የናስ፡መንኰራኵሮች፡ነበሩባቸው፤መንኰራኵሮቹም፡የሚዞሩበትን፡ የናስ፡ወስከምት፡ሠራ፤ከመታጠቢያውም፡ሰን፡በታች፡በአራቱ፡ማእዘን፡በኩል፡አራት፡በምስል፡የፈሰሱ፡ እግሮች፡ነበሩ።

31በክፈፉም፡ውስጥ፡የነበረ፡ዐንገት፡አንድ፡ክንድ፡ነበረ፤ዐንገቱም፡ድቡልቡል፡ነበረ፥ቁመቱም፡ክንድ፡ ተኩል፡ነበረ።በዐንገቱም፡ላይ፡ቅርጽ፡ነበረበት፤ክፈፉ፡ግን፡አራት፡ማእዘን፡ነበረ፡እንጂ፡ድቡልቡል፡ አልነበረም።

32አራቱም፡መንኰራኵሮች፡ከሰንበሮቹ፡በታች፡ነበሩ፤የመንኰራኵሮቹም፡ወስከምት፡በመቀመጫው፡ውስጥ፡ ነበረ፤የመንኰራኵሩም፡ቁመት፡ክንድ፡ተኩል፡ነበረ።

33የመንኰራኵሮቹም፡ሥራ፡እንደ፡ሠረገላ፡መንኰራኵር፡ነበረ፥ወስከምቶቹና፡የመንኰራኵሮቹ፡ክፈፍ፡ ቅትርቶቹም፡ወስከምቱም፡የሚገባበት፡ቧምቧ፡ዅሉ፡በምስል፡የፈሰሰ፡ነበር።

34በያንዳንዱም፡መቀመጫ፡በአራቱ፡ማእዘን፡በኩል፡አራት፡ደገፋዎች፡ነበሩ፤ደገፋዎቹም፡ከመቀመጫው፡ ጋራ፡ተገጥመው፡ነበር።

35በመቀመጫውም፡ላይ፡ስንዝር፡የሚኾን፡ድቡልቡል፡ነገር፡ነበረ፤በመቀመጫውም፡ላይ፡የነበሩ፡ መያዣዎችና፡ሰንበሮች፡ከርሱ፡ጋራ፡ይጋጠሙ፡ነበር።

36በመያዣውና፡በሰንበሮቹ፡ላይ፡ኪሩቤልንና፡አንበሳዎችን፡የዘንባባውንም፡ዛፍ፡እንደ፡መጠናችው፡ ቀረጸ፥በዙሪያውም፡ሻኵራ፡አደረገ።

37እንዲሁ፡ዐሥሩን፡መቀመጫዎች፡ሠራ፤ዅሉም፡በምስልና፡በመጠን፡በንድፍም፡ትክክሎች፡ነበሩ።

38ዐሥሩንም፡የናስ፡መታጠቢያ፡ሰን፡ሠራ፤አንዱ፡መታጠቢያ፡ሰን፡አርባ፡የባዶስ፡መስፈሪያ፡ያነሣ፡ ነበር፤እያንዳንዱም፡መታጠቢያ፡ሰን፡አራት፡ክንድ፡ነበረ፤በዐሥሩም፡መቀመጫዎች፡ላይ፡በያንዳንዱ፡አንድ፡ አንድ፡መታጠቢያ፡ሰን፡ይቀመጥ፡ነበር።

39ዐምስቱንም፡መቀመጫዎች፡በቤቱ፡ቀኝ፥ዐምስቱንም፡በቤቱ፡ግራ፡አኖራቸው፤ኵሬውንም፡በቤቱ፡ቀኝ፡ በአዜብ፡በኩል፡አኖረው።

40ኪራምም፡ምንችቶችንና፡መጫሪያዎችን፡ድስቶችንም፡ሠራ፤ኪራምም፡ለንጉሡ፡ለሰሎሞን፡ http://www.gzamargna.net በእግዚአብሔር፡ቤት፡የሠራውን፡ሥራ፡ዅሉ፡ጨረሰ።

41ኹለቱም፡አዕማድ፥በአዕማዱም፡ላይ፡የነበሩትን፡ኩብ፡የሚመስሉትን፡ጕልላቶች፥በአዕማዱም፡ላይ፡ የነበሩትን፡ኹለቱን፡ጕልላቶች፡የሚሸፍኑትን፡ኹለቱን፡መርበቦች፥

42በአዕማዱም፡ላይ፡የነበሩትን፡ኹለቱን፡ጕልላቶች፡ይሸፍኑ፡ዘንድ፡ለያንዳንዱ፡መርበብ፡በኹለት፡ በኹለት፡ተራ፡አድርጎ፡ለኹለቱ፡መርበቦች፡አራት፡መቶ፡ሮማኖች፡አደረገ።

43ዐሥሩንም፡መቀመጫዎች፥በመቀመጫዎችም፡ላይ፡የሚቀመጡትን፡ዐሥሩን፡መታጠቢያ፡ሰን፥

44አንዱንም፡ኵሬ፥ከኵሬውም፡በታች፡የሚኾኑትን፡ዐሥራ፡ኹለቱን፡በሬዎች፥

45ምንቸቶቹንም፥መጫሪያዎቹንም፥ድስቶቹንም፡አደረገ።ኪራምም፡ለንጉሡ፡ለሰሎሞን፡በእግዚአብሔር፡ ቤት፡የሠራው፡ይህ፡ዕቃ፡ዅሉ፡የጋለ፡ናስ፡ነበረ።

46በዮርዳኖስ፡ሜዳ፡በሱኮትና፡በጸርታን፡መካከል፡ባለው፡በወፍራሙ፡መሬት፡ውስጥ፡አስፈሰሰው።

47ሰሎሞንም፡ዕቃውን፡ዅሉ፡ሳያስመዝን፡አኖረ፤የናሱም፡ሚዛን፡ከብዛቱ፡የተነሣ፡አይቈጠርም፡ነበር።

48ሰሎሞንም፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡የነበረውን፡ዕቃ፡ዅሉ፡አሠራ፤የወርቁን፡መሠዊያ፥የገጹም፡ኅብስት፡ የነበረበትን፡የወርቅ፡ገበታ፥

49በቅድስተ፡ቅዱሳኑ፡ፊት፡ዐምስቱ፡በቀኝ፡ዐምስቱም፡በግራ፡የሚቀመጡትን፡ከጥሩ፡ወርቅ፡የተሠሩትንም፡ መቅረዞች፥የወርቁንም፡አበባዎችና፡ቀንዲሎች፡መኰስተሪያዎችም፥

50ከጥሩ፡ወርቅም፡የተሠሩትን፡ጽዋዎችና፡ጕጠቶች፥ድስቶቹንና፡ ጭልፋዎቹንም፥ማንደጃዎቹንም፥ለውስጠኛውም፡ቤት፡ለቅድስተ፡ቅዱሳን፡ደጆች፡ለቤተ፡መቅደሱም፡ደጆች፡ የሚኾኑትን፡የወርቅ፡ማጠፊያዎች፡አሠራ።

51እንዲሁ፡ንጉሡ፡ሰሎሞን፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡ውስጥ፡ያሠራው፡ሥራ፡ዅሉ፡ተፈጸመ።አባቱም፡ ዳዊት፡የቀደሰውን፥ብርና፡ወርቅ፡ዕቃም፥ሰሎሞን፡አገባ፥በእግዚአብሔርም፡ቤት፡ውስጥ፡በነበሩ፡ግምጃ፡ ቤቶች፡አኖረው።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source