Skip to content
← 1 Samuel

Chapter 1 · Amharic

1 Samuel

1በተራራማው፡በኤፍሬም፡አገር፡ከአርማቴም፡መሴፋ ፡የኾነ፡ስሙ፡ሕልቃና፡የተባለ፡ኤፍሬማዊ፡ሰው፡ ነበረ፤ርሱም፡የኢያሬምኤል ፡ልጅ፡የኢሊዮ ፡ልጅ፡የቶሑ፡ልጅ፡የናሲብ ፡ልጅ፡ነበረ።

2ኹለትም፡ሚስቶች፡ነበሩት፤የአንዲቱ፡ስም፡ሐና፡የኹለተኛዪቱም፡ስም፡ፍናና፡ነበረ፤ለፍናናም፡ልጆች፡ ነበሯት፥ለሐና፡ግን፡ልጅ፡አልነበራትም።

3ያም፡ሰው፡በሴሎ ፡ይሰግድ፡ዘንድ፡ለሰራዊት፡ጌታም፡ለእግዚአብሔር፡ይሠዋ፡ዘንድ፡ከከተማው፡ በየዓመቱ፡ይወጣ፡ነበር።የእግዚአብሔርም፡ካህናት፡ኹለቱ፡የዔሊ፡ልጆች፡አፍኒንና፡ፊንሐስ፡በዚያ፡ነበሩ።

4ሕልቃና፡የሚሠዋበት፡ቀን፡በደረሰ፡ጊዜም፡ለሚስቱ፡ለፍናና፡ለወንዶችና፡ለሴቶች፡ልጆቿ፡ዅሉ፡ዕድል፡ ፈንታቸውን፡ሰጣቸው።

5ሐናንም፡ይወድ፟፡ነበርና፥ለሐና፡ኹለት፡ዕጥፍ፡ዕድል፡ፈንታ፡ሰጣት።እግዚአብሔር፡ግን፡ማሕፀኗን፡ ዘግቶ፡ነበር።

6እግዚአብሔርም፡ማሕፀኗን፡ዘግቶ፡ነበርና፥ጣውንቷ፡ታስቈጣት፡ታበሳጫትም፡ነበር።

7በየዓመቱም፡እንዲህ፡ባደረገ፡ጊዜ፡ርሷም፡ወደ፡እግዚአብሔር፡በምትወጣበት፡ጊዜ፡ታበሳጫት፡ ነበር፤ሐናም፡ታለቅስ፡ነበር፥አንዳችም፡አትቀምስም፡ነበር።

8ባሏም፡ሕልቃና፦ሐና፡ሆይ፥ለምን፡ታለቅሻለሽ፧ለምንስ፡አትቀምሺም፧ለምንስ፡ልብሽ፡ ያዝንብሻል፧እኔስ፡ከዐሥር፡ልጆች፡አልሻልልሽምን፧አላት።

9በሴሎ፡ከበሉና፡ከጠጡ፡በዃላ፡ሐና፡ተነሣች።ካህኑም፡ዔሊ፡በእግዚአብሔር፡መቅደስ፡መቃን፡አጠገብ፡ በመንበሩ፡ላይ፡ተቀምጦ፡ነበር።

10ርሷም፡በልቧ፡ትመረር፡ነበር፥በእግዚአብሔር፡ፊት፡ጸለየች፥ጽኑ፡ልቅሶም፡አለቀሰች።

11ርሷም፦አቤቱ፥የሰራዊት፡ጌታ፡ሆይ፥የባሪያኽን፡መዋረድ፡ተመልክተኽ፡ብታስበኝ፥እኔንም፡ ባትረሳ፥ለባሪያኽም፡ወንድ፡ልጅ፡ብትሰጥ፥ዕድሜውን፡ዅሉ፡ለእግዚአብሔር፡እሰጠዋለኹ፥ምላጭም፡በራሱ፡ ላይ፡አይደርስም፡ብላ፡ስእለት፡ተሳለች።

12ጸሎቷንም፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ባበዛች፡ጊዜ፡ዔሊ፡አፏን፡ይመለከት፡ነበር።

13ሐናም፡በልቧ፡ትናገር፡ነበር፤ድምፇም፡ሳይሰማ፡ከንፈሯን፡ታንቀሳቅስ፡ነበር፤ዔሊም፡እንደ፡ሰከረች፡ ቈጠራት።

14ዔሊም፦ስካርሽ፡እስከ፡መቼ፡ነው፧የወይን፡ጠጅሽን፡ከአንቺ፡አርቂው፡አላት።

15ሐናም፦ጌታዬ፡ሆይ፥አይደለም፥እኔስ፡ልቧ፡ያዘነባት፡ሴት፡ነኝ፤ጠጅና፡ሌላ፡የሚያሰክር፡ነገር፡ አልጠጣኹም፥ነገር፡ግን፥በእግዚአብሔር፡ፊት፡ነፍሴን፡አፈሰስኹ፤

16ሐዘኔና፡ጭንቀቴ፡ስለ፡በዛ፡እስከ፡አኹን፡ድረስ፡ተናግሬያለኹና፡ባሪያኽን፡እንደ፡ምናምንቴ፡ሴት፡ 129 ዕብ.፥ራማታይም፡ጾፊይም። 130 ዕብ.፥የሮኀም። 131 ዕብ.፡ኤሊሁ። 132 ዕብ.፡ጹፍ። 133 ዕብ.፥ሺይሎህ/ሺሎ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org አትቍጠረኝ፡ብላ፡መለሰችለት።

17ዔሊም፦በደኅና፡ኺጂ፥የእስራኤልም፡አምላክ፡የለመንሽውን፡ልመና፡ይስጥሽ፡ብሎ፡መለሰላት።

18ርሷም፦ባሪያኽ፡በዐይንኽ፡ፊት፡ሞገስ፡ላግኝ፡አለች።ሴቲቱም፡መንገዷን፡ኼደች፡በላችም፥ፊቷም፡ ከእንግዲህ፡ወዲያ፡ዐዘንተኛ፡መስሎ፡አልታየም።

19ማልደው፡ተነሥተው፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ሰገዱ፥ተመልሰውም፡ወደ፡አርማቴም፡ወደ፡ቤታቸው፡ መጡ።ሕልቃናም፡ሚስቱን፡ሐናን፡ዐወቃት፤እግዚአብሔርም፡ዐሰባት፤

20የመፅነሷም፡ወራት፡ካለፈ፡በዃላ፡ሐና፡ወንድ፡ልጅ፡ወለደች፤ርሷም፦ከእግዚአብሔር፡ለምኜዋለኹ፡ ስትል፡ስሙን፡ሳሙኤል፡ብላ፡ጠራችው።

21ሰውዮውም፡ሕልቃና፡ከቤተ፡ሰቡ፡ዅሉ፡ጋራ፡የዓመቱን፡መሥዋዕትና፡ስእለቱን፡ለእግዚአብሔር፡ያቀርብ፡ ዘንድ፡ወጣ።

22ሐና፡ግን፡አልወጣችም፥ባሏንም፦ሕፃኑ፡ጡት፡እስኪተው፡ድረስ፡እቀመጣለኹ፤ከዚያም፡በዃላ፡ በእግዚአብሔር፡ፊት፡ይታይ፡ዘንድ፥በዚያም፡ለዘለዓለም፡ይኾን፡ዘንድ፡አመጣዋለኹ፡አለችው።

23ባሏም፡ሕልቃና፦በዐይንሽ፡ደስ፡ያሠኘሽን፡አድርጊ፥ጡትም፡እስኪተው፡ድረስ፡ተቀመጪ፤ብቻ፡ እግዚአብሔር፡ቃሉን፡ያጽና፡አላት።ሴቲቱም፡ልጇን፡እያጠባች፡ጡት፡እስኪተው፡ድረስ፡በቤቷ፡ተቀመጠች።

24ጡትም፡በተወ፡ጊዜ፡ከርሷ፡ጋራ፡ርሱንና፡አንድ፡የሦስት፡ዓመት፡ወይፈን፥አንድ፡የኢፍ፡መስፈሪያ፡ ዱቄት፥አንድ፡አቍማዳ፡የወይን፡ጠጅ፡ይዛ፡ወደ፡ሴሎ፡ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡አመጣችው፤ሕፃኑም፡ገና፡ ታናሽ፡ነበረ።

25ወይፈኑንም፡ዐረዱ፥ሕፃኑንም፡ወደ፡ዔሊ፡አመጡት።

26ርሷም፡አለች፦ጌታዬ፡ሆይ፥በሕያው፡ነፍስኽ፡እምላለኹ! ጌታ፡ሆይ፥ወደ፡እግዚአብሔር፡ለመጸለይ፡ በዚህ፡ባንተ፡ዘንድ፡ቆማ፡የነበረች፡ሴት፡እኔ፡ነኝ።

27ሰለዚህ፡ሕፃን፡ጸለይኹ፤

28እግዚአብሔርም፡የለመንኹትን፡ልመናዬን፡ሰጥቶኛል፤እኔም፡ደግሞ፡ለእግዚአብሔር፡ ሰጥቼዋለኹ፤ዕድሜውን፡ዅሉ፡ለእግዚአብሔር፡የተሰጠ፡ይኾናል።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source