Skip to content
← 1 Samuel

Chapter 31 · Amharic

1 Samuel

1ፍልስጥኤማውያንም፡ከእስራኤል፡ጋራ፡ተዋጉ፤የእስራኤልም፡ሰዎች፡ከፍልስጥኤማውያን፡ፊት፡ ሸሹ፥ተወግተውም፡በጊልቦዓ፡ተራራ፡ላይ፡ወደቁ።

2ፍልስጥኤማውያንም፡ሳኦልንና፡ልጆቹን፡በእግር፡በእግራቸው፡ተከትለው፡አባረሯቸው፤ፍልስጥኤማውያንም፡ የሳኦልን፡ልጆች፡ዮናታንንና፡ዐሚናዳብን፡ሜልኪሳንም፡ገደሉ።

3ሰልፍም፡በሳኦል፡ላይ፡ጠነከረ፥ቀስተኛዎችም፡አገኙት፤ርሱም፡ከቀስተኛዎቹ፡የተነሣ፡እጅግ፡ተጨነቀ።

4ሳኦልም፡ጋሻ፡ዣግሬውን፦እነዚህ፡ቈላፋን፡መጥተው፡እንዳይወጉኝና፡እንዳይሣለቁብኝ፡ሰይፍኽን፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org መዘ፟ኽ፡ውጋኝ፡አለው።ጋሻ፡ዣግሬው፡ግን፡እጅግ፡ፈርቶ፡ነበርና፥እንቢ፡አለ።ሳኦልም፡ሰይፉን፡ወስዶ፡ በላዩ፡ወደቀ።

5ጋሻ፡ዣግሬውም፡ሳኦል፡እንደ፡ሞተ፡ባየ፡ጊዜ፡ርሱ፡ደግሞ፡በሰይፉ፡ላይ፡ወደቀ፥ከርሱም፡ጋራ፡ሞተ።

6በዚያም፡ቀን፡ሳኦል፡ሦስቱም፡ልጆቹ፡ጋሻ፡ዣግሬውም፡ሰዎቹም፡ዅሉ፡ባንድ፡ላይ፡ሞቱ።

7በሸለቆውም፡ማዶና፡በዮርዳኖስ፡ማዶ፡የነበሩ፡እስራኤላውያን፡የእስራኤል፡ሰዎች፡እንደ፡ሸሹ፥ሳኦልና፡ ልጆቹም፡እንደ፡ሞቱ፡ባዩ፡ጊዜ፡ከተማዎቹን፡ለቀ፟ው፡ሸሹ፤ፍልስጥኤማውያንም፡መጥተው፡ተቀመጡባቸው።

8በማግስቱም፡ፍልስጥኤማውያን፡የሞቱትን፡ለመግፈፍ፡በመጡ፡ጊዜ፡ሳኦልና፡ሦስቱ፡ልጆቹ፡በጊልቦዓ፡ ተራራ፡ላይ፡ወድቀው፡አገኟቸው።

9የሳኦልንም፡ራስ፡ቈረጠው፡የጦር፡ዕቃውን፡ገፈ፟ው፡ለጣዖታቱ፡መቅደስ፡ለሕዝቡም፡የምሥራች፡ይሰጥ፡ ዘንድ፡ወደፍልስጥኤማውያን፡አገር፡ዅሉ፡ሰደዱ።

10የጦር፡ዕቃውንም፡በዐስታሮት፡መቅደስ፡ውስጥ፡አኖሩት፤ሬሳውንም፡በቤትሳን፡ቅጥር፡ላይ፡አንጠለጠሉት።

11ፍልስጥኤማውያንም፡በሳኦል፡ላይ፡ያደረጉትን፡የኢያቢስ፡ገለዓድ፡ሰዎች፡በሰሙ፡ጊዜ፥

12ዠግናዎች፡ሰዎች፡ዅሉ፡ተነሥተው፡ሌሊቱን፡ዅሉ፡ኼዱ፥የሳኦልንም፡ሬሳ፡የልጆቹንም፡ሬሳ፡ከቤትሳን፡ ቅጥር፡ላይ፡አወረዱ፤ወደ፡ኢያቢስም፡መጡ፥በዚያም፡አቃጠሉት።

13ዐጥንታቸውንም፡ወሰዱ፡በኢያቢስም፡ባለው፡በዐጣጡ፡ዛፍ፡በታች፡ቀበሩት፥ሰባት፡ቀንም፡ጾሙ፨ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source