Skip to content
← 2 Chronicles

Chapter 1 · Amharic

2 Chronicles

1የዳዊት፡ልጅ፡ሰሎሞን፡በመንግሥቱ፡በረታ፤አምላኩም፡እግዚአብሔር፡ከርሱ፡ጋራ፡ነበረ፥እጅግም፡ አገነነው።

2ሰሎሞንም፡ለእስራኤል፡ዅሉ፥ለሻለቃዎች፥ለመቶ፡አለቃዎችም፥ለፈራጆችም፥በእስራኤልም፡ዅሉ፡ዘንድ፡ ለነበሩ፡መሳፍንት፡ዅሉ፥ለአባቶች፡ቤቶች፡አለቃዎች፡ተናገረ።

3ሰሎሞንም፡ከርሱም፡ጋራ፡ጉባኤው፡ዅሉ፡የእግዚአብሔር፡ባሪያ፡ሙሴ፡በምድረ፡በዳ፡የሠራው፡ የእግዚአብሔር፡መገናኛ፡ድንኳን፡በዚያ፡ነበረና፡በገባዖን፡ወዳለው፡የኰረብታ፡መስገጃ፡ኼዱ።

4ለእግዚአብሔር፡ታቦት፡ግን፡ዳዊት፡በኢየሩሳሌም፡ድንኳን፡ተክሎለት፡ነበርና፥ዳዊት፡ከቂርያትይዓሪም፡ ወዳዘጋጀለት፡ስፍራ፡አምጥቶት፡ነበር።

5የሆርም፡ልጅ፡የኡሪ፡ልጅ፡ባስልኤል፡የሠራው፡የናስ፡መሠዊያ፡በዚያ፡በእግዚአብሔር፡ማደሪያ፡ፊት፡ ነበረ፤ሰሎሞንም፡ጉባኤውም፡ይህን፡ይፈልጉት፡ነበር።

6ሰሎሞንም፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡በመገናኛው፡ድንኳን፡አጠገብ፡ወዳለው፡ወደናሱ፡መሠዊያ፡ ወጣ፥በዚያም፡አንድ፡ሺሕ፡የሚቃጠል፡መሥዋዕት፡አቀረበ።

7በዚያም፡ሌሊት፡እግዚአብሔር፦ምን፡እንድሰጥኽ፡ለምነኝ፡ሲል፡ለሰሎሞን፡ተገለጠ።

8ሰሎሞንም፡እግዚአብሔርን፡አለው፦ከአባቴ፡ከዳዊት፡ጋራ፡ታላቅ፡ምሕረት፡አድርገኻል፥በርሱም፡ፋንታ፡ አንግሠኸኛል።

9አኹንም፥አቤቱ፡አምላክ፡ሆይ፥ቍጥሩ፡እንደምድር፡ትቢያ፡በኾነው፡በብዙ፡ሕዝብ፡ላይ፡ አንግሠኸኛልና፥ለአባቴ፡ለዳዊት፡የሰጠኸው፡ተስፋ፡ይጽና።

10አኹንም፡በዚህ፡ሕዝብ፡ፊት፡እወጣና፡እገባ፡ዘንድ፡ጥበብንና፡ዕውቀትን፡ስጠኝ፤ይህን፡በሚያኽል፡ በዚህ፡በታላቅ፡ሕዝብ፡ላይ፡ይፈርድ፡ዘንድ፡የሚችል፡የለምና።

11እግዚአብሔርም፡ሰሎሞንን፦ይህ፡በልብኽ፡ነበረና፥ባለጠግነትንና፡ሀብትን፡ክብርንና፡የጠላቶችኽን፡ነፍስ፡ ረዥምም፡ዕድሜን፡አልለመንኽምና፥ነገር፡ግን፥ባነገሥኹኽ፡በሕዝቤ፡ላይ፡ለመፍረድ፡ትችል፡ዘንድ፡ ጥበብንና፡ዕውቀትን፡ለራስኽ፡ለምነኻልና፥ጥበብንና፡ዕውቀትን፡ሰጥቼኻለኹ፤

12ከአንተ፡በፊትም፡ከነበሩት፡ከአንተም፡በዃላ፡ከሚነሡት፡ነገሥታት፡አንድ፡ስንኳ፡የሚመስልኽ፡ እንዳይኖር፡ባለጠግነትንና፡ሀብትን፡ክብርንም፡እሰጥኻለኹ፡አለው።

13ሰሎሞንም፡በገባዖን፡ካለው፡ከኰረብታው፡መስገጃ፡ከመገናኛው፡ድንኳን፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ መጣ፤በእስራኤልም፡ላይ፡ነገሠ።

14ሰሎሞንም፡ሠረገላዎቹንና፡ፈረሰኛዎችን፡ሰበሰበ፥አንድ፡ሺሕም፡አራት፡መቶ፡ሠረገላዎች፥ዐሥራ፡ ኹለት፡ሺሕም፡ፈረሰኛዎች፡ነበሩት፤በሠረገላዎች፡ከተማዎችና፡ከርሱ፡ጋራ፡በኢየሩሳሌም፡አኖራቸው።

15ንጉሡም፡ብሩንና፡ወርቁን፡በኢየሩሳሌም፡እንደ፡ድንጋይ፡እንዲበዛ፡አደረገው፤የዝግባም፡ዕንጨት፡ብዛት፡ በቈላ፡እንደሚበቅል፡ሾላ፡ኾነ።

16ሰሎሞንም፡ፈረሶችን፡ከግብጽና፡ከቀዌ፡አስመጣ፤የንጉሡም፡ነጋዴዎች፡በገንዘብ፡እየገዙ፡ከቀዌ፡ ያመጧቸው፡ነበር። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

17አንዱም፡ሠረገላ፡በስድስት፡መቶ፥አንዱም፡ፈረስ፡በመቶ፡ዐምሳ፡ሰቅል፡ብር፡ከግብጽ፡ይወጣ፡ ነበር፤እንዲሁም፡ለኬጢያውያንና፡ለሶርያ፡ነገሥታት፡ዅሉ፡በእጃቸው፡ያመጡላቸው፡ነበር።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source