1ሴዴቅያስም፡በነገሠ፡በዘጠነኛው፡ዓመት፡በዐሥረኛው፡ወር፡ከወሩም፡በዐሥረኛው፡ቀን፡የባቢሎን፡ንጉሥ፡ ናቡከደነጾርና፡ሰራዊቱ፡ዅሉ፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡መጥተው፡ከበቧት፤በዙሪያዋም፡ዕርድ፡ሠሩባት።
2ከተማዪቱም፡እስከ፡ንጉሡ፡እስከ፡ሴዴቅያስ፡እስከ፡ዐሥራ፡አንደኛው፡ዓመት፡ድረስ፡ተከባ፟፡ነበር።
3በአራተኛውም፡ወር፡በዘጠነኛው፡ቀን፡በከተማዪቱ፡ራብ፡ጸንቶ፡ነበርና፥ለአገሩ፡ሰዎች፡እንጀራ፡ታጣ።
4ከተማዪቱም፡ተሰበረች፥ሰልፈኛዎችም፡ዅሉ፡በኹለት፡ቅጥር፡መካከል፡ባለው፡በር፡ወደንጉሡ፡አትክልት፡ በሚወስደው፡መንገድ፡በሌሊት፡ሸሹ፤ከለዳውያንም፡በከተማዪቱ፡ዙሪያ፡ነበሩ፤በዐረባም፡መንገድ፡ኼዱ።
5የከለዳውያንም፡ሰራዊት፡ንጉሡን፡ተከታተሉ፥በኢያሪኮም፡ሜዳ፡ያዙት፤ሰራዊቱም፡ዅሉ፡ከርሱ፡ ተለይተው፡ተበትነው፡ነበር።
6ንጉሡንም፡ይዘው፡የባቢሎን፡ንጉሥ፡ወዳለበት፡ወደ፡ሪብላ፡አመጡት፤ፍርድም፡ፈረዱበት።
7የሴዴቅያስንም፡ልጆች፡በፊቱ፡ገደሏቸው፤የሴዴቅያስንም፡ዐይኖች፡አወጡ፥በሰንሰለትም፡አሰሩት፥ወደ፡ ባቢሎንም፡ወሰዱት።
8በባቢሎንም፡ንጉሥ፡በናቡከደነጾር፡በዐሥራ፡ዘጠነኛው፡ዓመት፡በዐምስተኛው፡ወር፡ከወሩም፡በሰባተኛው፡ ቀን፡የባቢሎን፡ንጉሥ፡ባሪያ፡የዘበኛዎቹ፡አለቃ፡ናቡዘረዳን፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡መጣ።
9የእግዚአብሔርንም፡ቤትና፡የንጉሡን፡ቤት፡አቃጠለ፤የኢየሩሳሌምንም፡ቤቶች፡ዅሉ፥ታላላቆቹን፡ቤቶች፡ ዅሉ፥በእሳት፡አቃጠለ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
10ከዘበኛዎቹም፡አለቃ፡ጋራ፡የነበረው፡የከለዳውያን፡ሰራዊት፡ዅሉ፡የኢየሩሳሌምን፡ቅጥር፡ዙሪያዋን፡ አፈረሱ።
11የዘበኛዎቹም፡አለቃ፡ናቡዘረዳን፡በከተማዪቱ፡ውስጥ፡የቀረውን፡ሕዝብ፥ሸሽተውም፡ወደባቢሎን፡ንጉሥ፡ የተጠጉትን፥የቀሩትንም፡ሕዝብ፡አፈለሰ።
12የዘበኛዎቹም፡አለቃ፡ከአገሩ፡ድኻዎች፡ወይን፡ተካዮችና፡ዐራሾች፡እንዲኾኑ፡አስቀረ።
13ከለዳውያንም፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡ውስጥ፡የነበሩትን፡የናስ፡ዐምዶች፥በእግዚአብሔርም፡ቤት፡የነበሩትን፡ መቀመጫዎችና፡የናስ፡ኵሬ፡ሰባበሩ፥ናሱንም፡ወደ፡ባቢሎን፡ወሰዱ።
14ምንቸቶቹንና፡መጫሪያዎቹንም፡መኰስተሪያዎቹንና፡ጭልፋዎቹንም፡የሚያገለግሉበትንም፡የናስ፡ዕቃ፡ዅሉ፡ ወሰዱ።
15የዘበኛዎቹም፡አለቃ፡ማንደጃዎቹንና፡መቀመጨዎቹን፥የወርቁን፡ዕቃ፡ዅሉ፡በወርቅ፥የብሩንም፡በብር፡ አድርጎ፡ወሰደ።
16ሰሎሞንም፡ለእግዚአብሔር፡ቤት፡የሠራቸውን፡ኹለቱን፡ዐምዶች፡አንዱንም፡ኵሬ፡መቀመጫዎቹንም፡ ወሰደ፤ለእነዚህ፡ዕቃዎች፡ዅሉ፡ናስ፡ሚዛን፡አልነበረውም።
17የአንዱም፡ዐምድ፡ቁመት፡ዐሥራ፡ስምንት፡ክንድ፡ነበረ፥የናስም፡ጕልላት፡ነበረበት፤የጕልላቱም፡ ርዝመት፡ሦስት፡ክንድ፡ነበረ፥በጕልላቱም፡ላይ፡በዙሪያው፡የናስ፡መርበብና፡ሮማኖች፡ነበሩ፤እንዲሁም፡ ደግሞ፡በኹለተኛው፡ዐምድ፡ላይ፡መርበብ፡ነበረበት።
18የዘበኛዎቹም፡አለቃ፡ታላቁን፡ካህን፡ሰራያን፡ኹለተኛውንም፡ካህን፡ሶፎንያስን፡ሦስቱንም፡በረኛዎች፡ ወሰደ።
19ከከተማዪቱም፡በሰልፈኛዎች፡ላይ፡ተሾመው፡ከነበሩት፡አንዱን፡ጃን፡ደረባ፥በከተማዪቱም፡የተገኙትን፡ በንጉሡ፡ፊት፡የሚቆሙትን፡ዐምስቱን፡ሰዎች፥የአገሩንም፡ሕዝብ፡የሚያሰልፍ፡የሰራዊቱን፡አለቃ፡ ጸሓፊ፥በከተማዪቱም፡ከተገኙት፡ከአገሩ፡ሕዝብ፡ስድሳ፡ሰዎች፡ወሰደ።
20የዘበኛዎቹም፡አለቃ፡ናቡዘረዳን፡ወስዶ፡የባቢሎን፡ንጉሥ፡ወዳለበት፡ወደ፡ሪብላ፡አመጣቸው።
21የባቢሎንም፡ንጉሥ፡መታቸው፥በሐማትም፡ምድር፡ባለችው፡በሪብላ፡ገደላቸው።እንዲሁ፡ይሁዳ፡ከአገሩ፡ ተማረከ።
22የባቢሎንም፡ንጉሥ፡ናቡከደነጾር፡በይሁዳ፡ምድር፡በቀረው፡ሕዝብ፡ላይ፡የሳፋንን፡ልጅ፡የአኪቃምን፡ ልጅ፡ጎዶልያስን፡አለቃ፡አደረገው።
23የጭፍራዎቹም፡አለቃዎች፡ዅሉ፥የናታንያ፡ልጅ፡እስማኤል፥የቃሬያም፡ልጅ፡ዮሐናን፥የነጦፋዊውም፡ የተንሑሜት፡ልጅ፡ሰራያ፥የማዕካታዊውም፡ልጅ፡ያእዛንያ፥ሰዎቻቸውም፡የባቢሎን፡ንጉሥ፡ጎዶልያስን፡እንደ፡ ሾመ፡በሰሙ፡ጊዜ፡ወደ፡ጎዶልያስ፡ወደ፡ምጽጳ፡መጡ።
24ጎዶልያስም፦ከከለዳውያን፡ሎሌዎች፡የተነሣ፡አትፍሩ፥በአገሩ፡ተቀመጡ፥ለባቢሎንም፡ንጉሥ፡ ተገዙ፥መልካምም፡ይኾንላችዃል፡ብሎ፡ለእነርሱና፡ለሰዎቻቸው፡ማለላቸው።
25በሰባተኛው፡ወር፡ግን፡የመንግሥት፡ዘር፡የነበረ፡የኤሊሳማ፡ልጅ፡የናታንያ፡ልጅ፡እስማኤል፡ከርሱም፡ ጋራ፡ዐሥር፡ሰዎች፡መጥተው፡ጎዶልያስንና፡ከርሱ፡ጋራ፡በምጽጳ፡የነበሩትን፡አይሁድንና፡ከለዳውያንን፡ እስኪሞቱ፡ድረስ፡መቷቸው።
26ከለዳውያንንም፡ፈርተው፡ነበርና፥ከታናሹ፡ዠምሮ፡እስከ፡ታላቁ፡ድረስ፡ሕዝቡ፡ዅሉ፡የጭፍራዎቹም፡ አለቃዎች፡ተነሥተው፡ወደ፡ግብጽ፡መጡ።
27እንዲህም፡ኾነ፤የይሁዳ፡ንጉሥ፡ዮአኪን፡በተማከረ፡በሠላሳ፡ሰባተኛው፡ዓመት፡በዐሥራ፡ኹለተኛው፡ ወር፡ከወሩም፡በኻያ፡ሰባተኛው፡ቀን፡የባቢሎን፡ንጉሥ፡ዮርማሮዴክ፡በነገሠ፡በአንደኛው፡ዓመት፡የይሁዳ፡ ንጉሥ፡ዮአኪንን፡ከወህኒ፡አወጣው፤ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
28በፍቅርም፡ተናገረው፥ዙፋኑንም፡ከርሱ፡ጋራ፡በባቢሎን፡ከነበሩት፡ነገሥታት፡ዙፋን፡በላይ፡አደረገለት።
29በወህኒም፡ውስጥ፡ለብሶት፡የነበረውን፡ልብስ፡ለወጠለት፤ዮአኪንም፡በሕይወቱ፡ዘመን፡ዅሉ፡በፊቱ፡ ዅልጊዜ፡እንጀራ፡ይበላ፡ነበር።
30ንጉሡም፡በሕይወቱ፡ዘመን፡ዅሉ፡የዘወትር፡ቀለብ፡ዕለት፡ዕለት፡ይሰጠው፡ነበር፨ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org