Skip to content
← 2 Kings

Chapter 24 · Amharic

2 Kings

1በርሱም፡ዘመን፡የባቢሎን፡ንጉሥ፡ናቡከደነጾር፡ወጣ፥ኢዮአቄምም፡ሦስት፡ዓመት፡ተገዛለት፤ከዚያም፡ በዃላ፡ዘወር፡አለና፡ዐመፀበት።

2እግዚአብሔርም፡የከለዳውያንንና፡የሶርያውያንን፡የሞዐባውያንንም፡የዐሞንንም፡ልጆች፡አደጋ፡ጣዮች፡ ሰደደበት፤በባሪያዎቹ፡በነቢያት፡እንደተናገረው፡እንደእግዚአብሔር፡ቃል፡ያጠፉት፡ዘንድ፡በይሁዳ፡ላይ፡ ሰደዳቸው።

3ምናሴ፡ስላደረገው፡ኀጢአት፡ዅሉ፡ስላፈሰሰውም፡ንጹሕ፡ደም፥ኢየሩሳሌምንም፡በንጹሕ፡ደም፡ስለ፡ሞላ፡ ከፊቱ፡ያስወግዳቸው፡ዘንድ፡ይህ፡ነገር፡በእግዚአብሔር፡ትእዛዝ፡በይሁዳ፡ላይ፡ኾነ፤

4እግዚአብሔርም፡ይራራ፡ዘንድ፡አልወደደም።

5የቀረውም፡የኢዮአቄም፡ነገር፥የሠራውም፡ሥራ፡ዅሉ፥በይሁዳ፡ነገሥታት፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡የተጻፈ፡ አይደለምን፧

6ኢዮአቄምም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡አንቀላፋ፤ልጁም፡ዮአኪን ፤በርሱ፡ፋንታ፡ነገሠ።

7የባቢሎንም፡ንጉሥ፡ለግብጽ፡ንጉሥ፡የነበረውን፡ዅሉ፡ከግብጽ፡ወንዝ፡ዠምሮ፡እስከኤፍራጥስ፡ወንዝ፡ ድረስ፡ወስዶ፡ነበርና፥የግብጽ፡ንጉሥ፡ከዚያ፡ወዲያ፡ከአገሩ፡አልወጣም።

8ዮአኪን፡መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡የዐሥራ፡ስምንት፡ዓመት፡ጕልማሳ፡ነበረ፤በኢየሩሳሌምም፡ሦስት፡ወር፡ ነገሠ፤እናቱም፡ኔስታ፡ትባል፡ነበር፤ርሷም፡የኢየሩሳሌም፡ሰው፡የኤልናታን፡ልጅ፡ነበረች።

9አባቱም፡እንዳደረገ፡ዅሉ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ክፉ፡አደረገ።

10በዚያም፡ወራት፡የባቢሎን፡ንጉሥ፡የናቡከደነጾር፡ባሪያዎች፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ወጡ፥ከተማዪቱም፡ 184 ዕብ.፥የሆያቂም፡(ያቀውም፡እግዚእ•ጌታ፡ያቆማል)። 185 ዕብ.፥የሆያኪይን፡(ይከውን፡በእግዚእ•በጌታ፡ይኾናል)። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ተከበበች።

11ባሪያዎቹም፡በከበቧት፡ጊዜ፡የባቢሎን፡ንጉሥ፡ናቡከደነጾር፡ወደ፡ከተማዪቱ፡ወጣ።

12የይሁዳም፡ንጉሥ፡ዮአኮንና፡እናቱ፥ባሪያዎቹም፥አለቃዎቹም፥ጃን፡ደረባዎቹም፡ወደባቢሎን፡ንጉሥ፡ ወጡ፤የባቢሎንም፡ንጉሥ፡በነገሠ፡በስምንተኛው፡ዓመት፡ያዘው።

13የእግዚአብሔርም፡ቤት፡መዛግብትን፡ዅሉ፡የንጉሡም፡ቤት፡መዛግብትን፡ከዚያ፡አወጣ፤እግዚአብሔርም፡ እንደ፡ተናገረው፡የእስራኤል፡ንጉሥ፡ሰሎሞን፡በእግዚአብሔር፡መቅደስ፡የሠራውን፡የወርቁን፡ዕቃ፡ዅሉ፡ ሰባበረ።

14ኢየሩሳሌምንም፡ዅሉ፥አለቃዎቹንም፡ዅሉ፥ጽኑዓን፡ኀያላኑንም፡ዅሉ፥ጠራቢዎቹንም፡ዅሉ፥ብረት፡ ሠራተኛዎቹን፡ዅሉ፡ዐሥር፡ሺሕ፡ምርኮኛዎች፡አፈለሰ፤ከድኻዎች፡ከአገሩ፡ሕዝብ፡በቀር፡ማንም፡አልቀረም።

15ዮአኮንንም፡ወደ፡ባቢሎን፡አፈለሰ፤የንጉሡንም፡እናት፥የንጉሡንም፡ሚስቶች፥ጃን፡ ደረባዎቹንም፥የአገሩንም፡ታላላቆች፡ከኢየሩሳሌም፡ወደ፡ባቢሎን፡ማረከ።

16የባቢሎንም፡ንጉሥ፡ብርቱዎቹንና፡ሰልፍ፡የሚችሉትን፡ዅሉ፥ኀያላኑን፡ዅሉ፡ሰባት፡ሺሕ፡ ያኽል፥ጠራቢዎችና፡ብረት፡ሠራተኛዎችም፡አንድ፡ሺሕ፥ወደ፡ባቢሎን፡ማረከ።

17የባቢሎንም፡ንጉሥ፡የዮአኪንን፡አጎት፡ማታንያን፡በርሱ፡ፋንታ፡አነገሠ፥ስሙንም፡ሴዴቅያስ፡ብሎ፡ ለወጠው።

18ሴዴቅያስ፡መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡የኻያ፡አንድ፡ዓመት፡ጕልማሳ፡ነበረ፤በኢየሩሳሌምም፡ዐሥራ፡ አንድ፡ዓመት፡ነገሠ፤እናቱም፡ዐሚጣል፡የተባለች፡የልብና፡ሰው፡የኤርምያስ፡ልጅ፡ነበረች።

19ኢዮአቄምም፡እንዳደረገ፡ዅሉ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ክፉ፡አደረገ።

20ከፊቱ፡አውጥቶ፡እስኪጥላቸው፡ድረስ፡ይህ፡ነገር፡በእግዚአብሔር፡ቍጣ፡በኢየሩሳሌምና፡በይሁዳ፡ላይ፡ ኾኗልና፤ሴዴቅያስም፡በባቢሎን፡ንጉሥ፡ላይ፡ዐመፀ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source