1እንዲህም፡ኾነ፥ሳኦል፡ከሞተ፡በዃላ፡ዳዊት፡ዐማሌቃውያንን፡ከመግደል፡ተመልሶ፡በጺቅላግ፡ኹለት፡ቀን፡ ያኽል፡ተቀመጠ።
2በሦስተኛውም፡ቀን፥እንሆ፥ከሳኦል፡ሰፈር፡አንድ፡ሰው፡ልብሱን፡ቀዶ፟፡በራሱም፡ላይ፡ትቢያ፡ነስንሶ፡ መጣ፤ወደ፡ዳዊትም፡በመጣ፡ጊዜ፡በግንባሩ፡ተደፍቶ፡እጅ፡ነሣ።
3ዳዊትም፦ከወዴት፡መጣኽ፧አለው፡ርሱም፦ከእስራኤል፡ሰፈር፡ኰብልዬ፡መጣኹ፡አለው።
4ዳዊትም፦ነገሩ፡እንደ፡ምን፡ኾነ፧እስኪ፡ንገረኝ፡አለው።ርሱም፡መልሶ፦ሕዝቡ፡ከሰልፉ፡ ሸሽቷል፥ከሕዝቡ፡ብዙው፡ወደቁ፡ሞቱም፤ሳኦልና፡ልጁም፡ዮናታን፡ደግሞ፡ሞተዋል፡አለ።
5ዳዊትም፡ወሬኛውን፡ጕልማሳ፦ሳኦልና፡ልጁ፡ዮናታን፡እንደ፡ሞቱ፡በምን፡ታውቃለኽ፧አለው።
6ወሬኛውም፡ጕልማሳ፡አለ፦በድንገት፡ወደጊልቦዓ፡ተራራ፡መጣኹ፥እንሆም፥ሳኦል፡ጦሩን፡ተመርኵዞ፡ ቆሞ፡ነበር፤ሠረገላዎችና፡ፈረሰኛዎችም፡ተከትለው፡ደረሱበት።
7ወደ፡ዃላውም፡ዘወር፡አለና፡እኔን፡አይቶ፡ጠራኝ፤እኔም፦እንሆኝ፡አልኹ።
8ርሱም፦አንተ፡ማን፡ነኽ፧አለኝ፤እኔም፦ዐማሌቃዊ፡ነኝ፡ብዬ፡መለስኹለት።
9ርሱም፦ሰውነቴ፡ዝሏልና፥ደግሞ፡እስከ፡አኹን፡ድረስ፡ነፍሴ፡ገና፡ፈጽማ፡ሕያው፡ናትና፥በላዬ፡ ቆመኽ፡ግደለኝ፡አለኝ።
10እኔም፡ከወደቀ፡በዃላ፡አለ፡መዳኑን፡አይቼ፡በላዩ፡ቆሜ፡ገደልኹት፤በራሱም፡ላይ፡የነበረውን፡ዘውድ፡ በክንዱም፡የነበረውን፡ቢተዋ፡ወሰድኹ፥ወደዚህም፡ወደ፡ጌታዬ፡አመጣኹት።
11ዳዊትና፡ከርሱ፡ጋራ፡የነበሩ፡ሰዎች፡ዅሉ፡ልብሳቸውን፡ይዘው፡ቀደዱ።
12በሰይፍም፡ወድቀዋልና፥ለሳኦልና፡ለልጁ፡ለዮናታን፡ለእግዚአብሔርም፡ሕዝብ፡ለእስራኤልም፡ወገን፡እንባ፡ እያፈሰሱ፡አለቀሱ፥እስከ፡ማታም፡ድረስ፡ጾሙ።
13ዳዊትም፡ወሬኛውን፡ጕልማሳ።አንተ፡ከወዴት፡ነኽ፧አለው፤ርሱም፦እኔ፡የመጻተኛው፡የዐማሌቃዊው፡ ልጅ፡ነኝ፡ብሎ፡መለሰለት።
14ዳዊትም፦እግዚአብሔር፡የቀባውን፡ለመግደል፡እጅኽን፡ስትዘረጋ፡ለምን፡አልፈራኽም፧አለው።
15ዳዊትም፡ከጕልማሳዎቹ፡አንዱን፡ጠርቶ፦ወደ፡ርሱ፡ቅረብና፡ውደቅበት፡አለው።ርሱም፡ መታው፥ሞተም።
16ዳዊትም፦እግዚአብሔር፡የቀባውን፡እኔ፡ገድያለኹ፡ብሎ፡አፍኽ፡በላይኽ፡መስክሯልና፥ደምኽ፡በራስኽ፡ ላይ፡ይኹን፡አለው።
17ዳዊትም፡ስለ፡ሳኦልና፡ሰለ፡ልጁ፡ስለ፡ዮናታን፡ይህን፡የሐዘን፡ቅኔ፡ተቀኘ፥
18የይሁዳንም፡ልጆች፡ያስተምሩ፡ዘንድ፡አዘዘ።እንሆ፥ይህ፡በያሻር፡መጽሐፍ፡ተጽፏል።
19የእስራኤል፡ክብር፡በኰረብታዎች፡ላይ፡ተወግቶ፡ሞተ፤ኀያላን፡እንዴት፡ወደቁ!
20የፍልስጥኤማውያን፡ቈነዣዥት፡ደስ፡እንዳይላቸው፥የቈላፋንም፡ቈነዣዥት፡እልል፡እንዳይሉ፥በጌት፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ውስጥ፡አታውሩ፤በአስቀሎናም፡አደባባይ፡የምሥራች፡አትበሉ።
21እናንተ፡የጊልቦዓ፡ተራራዎች፡ሆይ፥የሳኦል፡ጋሻ፡በዘይት፡እንዳልተቀባ፥የኀያላን፡ጋሻ፡በዚያ፡ ወድቋልና፥ዝናብና፡ጠል፡አይውረድባችኹ፥ቍርባንንም፡የሚያበቅል፡ዕርሻ፡አይኹንባችኹ።
22ከሞቱት፡ደምና፡ከኀያላን፡ስብ፡የዮናታን፡ቀስት፡አልተመለሰችም፥የሳኦልም፡ሰይፍ፡በከንቱ፡ አልተመለሰም።
23ሳኦልና፡ዮናታን፡የተዋደዱና፡የተስማሙ፡ነበሩ፤በሕይወታቸውና፡በሞታቸው፡አልተለያዩም፤ከንስር፡ይልቅ፡ ፈጣኖች፡ነበሩ፤ከአንበሳም፡ይልቅ፡ብርቱዎች፡ነበሩ።
24የእስራኤል፡ቈነዣዥት፡ሆይ፥ቀይ፡ሐርና፡ጥሩ፡ግምጃ፡ያለብሳችኹ፡ለነበረ፥በወርቀ፡ዘቦም፡ ላስጌጣችኹ፡ለሳኦል፡አልቅሱለት።
25ኀያላንም፡በሰልፍ፡ውስጥ፡እንዴት፡ወደቁ! ዮናታንም፡በኰረብታዎችኽ፡ላይ፡ወድቋል።
26ወንድሜ፡ዮናታን፡ሆይ፥እኔ፡ስለ፡አንተ፡እጨነቃለኹ፤በእኔ፡ዘንድ፡ውድኽ፡እጅግ፡የተለየ፡ ነበረ፤ከሴት፡ፍቅር፡ይልቅ፡ፍቅርኽ፡ለእኔ፡ግሩም፡ነበረ።
27ኀያላን፡እንዴት፡ወደቁ! የሰልፍም፡ዕቃ፡እንዴት፡ጠፋ!