Skip to content
← 2 Samuel

Chapter 2 · Amharic

2 Samuel

1ከዚያም፡በዃላ፡ዳዊት፦ከይሁዳ፡ከተማዎች፡ወደ፡አንዲቱ፡ልውጣን፧ብሎ፡እግዚአብሔርን፡ ጠየቀ።እግዚአብሔርም፦ውጣ፡አለው።ዳዊትም፦ወዴት፡ልውጣ፧አለ።ርሱም፦ወደ፡ኬብሮን፡ውጣ፡ አለው።

2ዳዊትም፡ከኹለቱ፡ሚስቶቹ፡ከኢይዝራኤላዊቱ፡ከአኪናሖምና፡የቀርሜሎሳዊው፡የናባል፡ሚስት፡ከነበረችው፡ ከአቢግያ፡ጋራ፡ወደዚያ፡ወጣ።

3ዳዊትም፡ከርሱ፡ጋራ፡የነበሩትን፡ሰዎችና፡ቤተ፡ሰባቸውን፡ዅሉ፡አመጣ፤በኬብሮንም፡ከተማዎች፡ ተቀመጡ።

4የይሁዳም፡ሰዎች፡መጥተው፡በይሁዳ፡ቤት፡ይነግሥ፡ዘንድ፡ዳዊትን፡በዚያ፡ቀቡት።ሳኦልን፡የቀበሩት፡ የኢያቢስ፡ገለዓድ፡ሰዎች፡ናቸው፡ብለው፡ለዳዊት፡ነገሩት።

5ዳዊትም፡ወደኢያቢስ፡ገለዓድ፡ሰዎች፡መልእክተኛዎችን፡ልኮ፡እንዲህ፡አላቸው።እናንተ፡ለጌታችኹ፡ ለሳኦል፡ይህን፡ቸርነት፡አድርጋችዃልና፥ቀብራችኹትማልና፥በእግዚአብሔር፡የተባረካችኹ፡ኹኑ።

6አኹንም፡እግዚአብሔር፡ቸርነትንና፡እውነትን፡ያድርግላችኹ፤ይህንም፡ነገር፡አድርጋችዃልና፥እኔ፡ደግሞ፡ ይህን፡ቸርነት፡እመልስላችዃለኹ።

7አኹንም፡ጌታችኹ፡ሳኦል፡ሞቷልና፥እጃችኹ፡ትጽና፥እናንተም፡ጨክኑ፤ዳግም፡የይሁዳ፡ቤት፡በእነርሱ፡ ላይ፡ንጉሥ፡እኾን፡ዘንድ፡ቀብተውኛል።

8የሳኦልም፡ጭፍራ፡አለቃ፣የኔር፡ልጅ፡አበኔር፥የሳኦልን፡ልጅ፣ኢያቡስቴን፡ወስዶ፡ወደ፡መሃናይም፡ አሻገረው፤

9በገለዓድና፡በአሹራውያን፡በኢይዝራኤልም፡በኤፍሬምም፡በብንያምም፡በእስራኤልም፡ዅሉ፡ላይ፡አነገሠው።

10የሳኦል፡ልጅ፡ኢያቡስቴም፡በእስራኤል፡ላይ፡መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡የአርባ፡ዓመት፡ሰው፡ ነበረ፤ኹለት፡ዓመትም፡ነገሠ፤ነገር፡ግን፥የይሁዳ፡ቤት፡ዳዊትን፡ተከተለ።

11ዳዊትም፡በይሁዳ፡ቤት፡ነግሦ፡በኬብሮን፡የተቀመጠበት፡ዘመን፡ሰባት፡ዓመት፡ከስድስት፡ወር፡ነበረ።

12የኔር፡ልጅ፡አበኔርና፡የሳኦል፡ልጅ፡የኢያቡስቴ፡ባሪያዎች፡ከመሃናይም፡ወደ፡ገባዖን፡ወጡ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

13የጽሩያ፡ልጅ፡ኢዮአብና፡የዳዊት፡ባሪያዎች፡ወጥተው፡በገባዖን፡ውሃ፡መቆሚያ፡አጠገብ፡ ተገናኟቸው፤በውሃውም፡መቆሚያ፡በአንዱ፡ወገን፡እነዚህ፥በሌላውም፡ወገን፡እነዚያ፡ኾነው፡ተቀመጡ።

14አበኔርም፡ኢዮአብን፦ጕልማሳዎች፡ይነሡ፥በፊታችንም፡ይቈራቈሱ፡አለው፤ኢዮአብም፦ይነሡ፡አለ።

15ለብንያም፡ወገንና፡ለሳኦል፡ልጅ፡ለኢያቡስቴ፡አስራ፡ኹለት፥ከዳዊትም፡ባሪያዎች፡ዐሥራ፡ኹለት፡ ተቈጥረው፡ተነሡ።

16ዅሉም፡እያንዳንዱ፡የወደረኛውን፡ራስ፡ያዘ፥ሰይፉንም፡በወደረኛው፡ጐን፡ሻጠ፥ተያይዘውም፡ ወደቁ።የዚያም፡ስፍራ፡ስም፡የስለታም፡ሰይፍ፡ዕርሻ፡ተብሎ፡ተጠራ፥ርሱም፡በገባዖን፡ነው።

17በዚያም፡ቀን፡ጽኑ፡ሰልፍ፡ኾነ፤በዳዊትም፡ባሪያዎች፡ፊት፡አበኔርና፡የእስራኤል፡ሰዎች፡ተሸነፉ።

18በዚያም፡ሦስቱ፡የጽሩያ፡ልጆች፡ኢዮአብና፡አቢሳ፡ዐሳሄልም፡ነበሩ፤ዐሳሄልም፡እንደ፡ዱር፡ሚዳቋ፡ በሩጫ፡ፈጣን፡ነበረ።

19ዐሳሄልም፡የአበኔርን፡ፍለጋ፡ተከታተለ፥አበኔርንም፡ከማሳደድ፡ቀኝና፡ግራ፡አላለም።

20አበኔርም፡ዘወር፡ብሎ፡ተመለከተና፦አንተ፡ዐሳሄል፡ነኽን፧አለ።ርሱም፦እኔ፡ነኝ፡አለ።

21አበኔርም፦ወደ፡ቀኝ፡ወይም፡ወደ፡ግራ፡ፈቀቅ፡በል፤አንድ፡ጕልማሳ፡ያዝ፥መሣሪያውንም፡ውሰድ፡ አለው።ዐሳሄል፡ግን፡ርሱን፡ከማሳደድ፡ፈቀቅ፡ይል፡ዘንድ፡እንቢ፡አለ።

22አበኔርም፡ዐሳሄልን፦ከምድር፡ጋራ፡እንዳላጣብቅኽ፡እኔን፡ከማሳደድ፡ፈቀቅ፡በል፤ወደ፡ወንድምኽ፡ ወደ፡ኢዮአብ፡ፊቴን፡አቅኝቼ፡አይ፡ዘንድ፡እንዴት፡ይቻለኛል፧አለው።

23ነገር፡ግን፥ከርሱ፡ፈቀቅ፡ይል፡ዘንድ፡እንቢ፡አለ፤አበኔርም፡በጦሩ፡ጫፍ፡ሆዱን፡ወጋው፥ጦሩም፡ በዃላው፡ወጣ፥በዚያም፡ስፍራ፡ወድቆ፡ሞተ።ዐሳሄልም፡ወድቆ፡በሞተበቱ፡ስፍራ፡የሚያልፍ፡ዅሉ፡ይቆም፡ ነበር።

24ኢዮአብና፡አቢሳም፡አበኔርን፡አሳደዱ፤በገባዖንም፡ምድረ፡በዳ፡መንገድ፡በጋይ፡ፊት፡ለፊት፡እስካለው፡ እስከ፡አማ፡ኰረብታ፡ድረስ፡በወጡ፡ጊዜ፡ፀሓይ፡ጠለቀች።

25የብንያምም፡ልጆች፡ወደ፡አበኔር፡ተሰበሰቡ፥በአንድነትም፡ኾኑ፥በኰረብታም፡ራስ፡ላይ፡ቆሙ።

26አበኔርም፡ወደ፡ኢዮአብ፡ጮኸ፦ሰይፍ፡በእውኑ፡እስከ፡ዘለዓለም፡ያጠፋልን፧ፍጻሜውሳ፡መራራ፡እንደ፡ ኾነ፡አታውቅምን፧ሕዝቡ፡ወንድሞቻቸውን፡ከማሳደድ፡ይመለሱ፡ዘንድ፡ሕዝቡን፡የማትናገር፡እስከ፡መቼ፡ ነው፧አለው።

27ኢዮአብም፦ሕያው፡እግዚአብሔርን! ባትናገር፡ኖሮ፡ሕዝቡ፡በጧት፡ወጥተው፡በኼዱ፡ ነበር፥ወንድሞቻቸውንም፡ማሳደድ፡በተዉ፡ነበር፡አለ።

28ኢዮአብም፡ቀንደ፡መለከት፡ነፋ፥ሕዝቡም፡ዅሉ፡ቆመ፥ከዚያም፡በዃላ፡እስራኤልን፡ አላሳደደም፥ሰልፍም፡አላደረገም።

29አበኔርና፡ሰዎቹም፡ሌሊቱን፡ዅሉ፡ዐረባ፡እያለፉ፡ኼዱ፤ዮርዳኖስንም፡ተሻገሩ፥ቢትሮንንም፡ዅሉ፡ካለፉ፡ በዃላ፡ወደ፡መሃናይም፡መጡ።

30ኢዮአብም፡አበኔርን፡ከማሳደድ፡ተመለሰ፤ሕዝቡንም፡ዅሉ፡ሰበሰበ፥ከዳዊትም፡ባሪያዎች፡ከዐሳሄል፡ሌላ፡ ዐሥራ፡ዘጠኝ፡ሰዎች፡ጐደሉ።

31የዳዊትም፡ባሪያዎች፡ከብንያምና፡ከአበኔር፡ሰዎች፡ሦስት፡መቶ፡ስድሳ፡ያኽል፡ገደሉ።

32ዐሳሄልንም፡አንሥተው፡በቤተ፡ልሔም፡በአባቱ፡መቃብር፡ቀበሩት፤ኢዮአብና፡ሰዎቹም፡ሌሊቱን፡ዅሉ፡ ኼዱ፥በኬብሮንም፡አነጉ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source