1በሳኦል፡ቤትና፡በዳዊት፡ቤት፡መካከል፡ብዙ፡ዘመን፡ጦርነት፡ኾነ፤የዳዊት፡ቤት፡እየበረታ፥የሳኦል፡ቤት፡ ግን፡እየደከመ፡የሚኼድ፡ኾነ።
2ለዳዊትም፡ወንድ፡ልጆች፡በኬብሮን፡ተወለዱለት፤በኵሩም፡ከኢይዝራኤላዊቱ፡ከአኪናሖም፡የተወለደው፡ አምኖን ፡ነበረ።
3ኹለተኛውም፡የቀርሜሎሳዊው፡የናባል፡ሚስት፡ከነበረች፡ከአቢግያ፡የተወለደው፡ዶሎሕያ ፡ ነበረ።ሦስተኛውም፡ከጌሹር፡ንጉሥ፡ከተልማይ ፡ልጅ፡ከመዓካ፡የተወለደው፡አቤሴሎም ፡ነበረ።
4አራተኛውም፡የአጊት፡ልጅ፡አዶንያስ፥ዐምስተኛውም፡የአቢጣል፡ልጅ፡ሰፋጥያስ፡ነበረ።
5ስድስተኛውም፡የዳዊት፡ልጅ፡ሚስት፡የዔግላ፡ልጅ፡ይትረኃም፡ነበረ።እነዚህም፡ለዳዊት፡በኬብሮን፡ ተወለዱለት።
6በሳኦል፡ቤትና፡በዳዊት፡ቤት፡መካከል፡ጦርነት፡ኾኖ፡ሳለ፡አበኔር፡በሳኦል፡ቤት፡ይበረታ፡ነበር።
7ለሳኦልም፡የኢዮሄል፡ልጅ፡ሪጽፋ፡የተባለች፡ቁባት፡ነበረችው፤ኢያቡስቴም፡አበኔርን፦ወዳባቴ፡ቁባት፡ ለምን፡ገባኽ፧አለው።
8አበኔርም፡በኢያቡስቴ፡ቃል፡እጅግ፡ተቈጥቶ፡እንዲህ፡አለ፦እኔ፡ለአባትኽ፡ለሳኦል፡ቤት፡ለወንድሞቹም፡ ለዘመዶቹም፡ቸርነት፡አድርጌያለኹ፥አንተንም፡ለዳዊት፡እጅ፡አሳልፌ፡አልሰጠኹም፤አንተም፡ዛሬ፡ከዚች፡ ሴት፡ጋራ፡ስለሠራኹት፡ኀጢአት፡ትከሰ፟ኛለኽ፤በእውኑ፡እኔ፡የውሻ፡ራስ፡ነኝን፧
10መንግሥትን፡ከሳኦል፡ቤት፡ያወጣ፡ዘንድ፡የዳዊትንም፡ዙፋን፡በእስራኤልና፡በይሁዳ፡ከዳን፡ዠምሮ፡ እስከ፡ቤርሳቤሕ፡ድረስ፡ከፍ፡ያደርግ፡ዘንድ፡እግዚአብሔር፡ለዳዊት፡እንደ፡ማለለት፡እንዲሁ፡ከርሱ፡ጋራ፡ ባላደርግ፡እግዚአብሔር፡በአበኔር፡ይህን፡ያድርግበት፡ይህንም፡ይጨምርበት።
11ኢያቡስቴም፡አበኔርን፡ይፈራው፡ነበርና፥አንዳች፡ይመልስለት፡ዘንድ፡አልቻለም።
12አበኔርም፡ለዳዊት፦ምድሪቱ፡ለማን፡ናት፧ከእኔ፡ጋራ፡ቃል፡ኪዳን፡አድርግ፥እጄም፡ከአንተ፡ጋራ፡ ትኾናለች፥እስራኤልንም፡ዅሉ፡ወዳንተ፡እመልሰዋለኹ፡ብለው፡ይነግሩት፡ዘንድ፡መልእክተኛዎች፡ሰደደለት።
13ዳዊትም፦ይኹን፥ከአንተ፡ጋራ፡ቃል፡ኪዳን፡አደርጋለኹ፤ነገር፡ግን፥አንድ፡ነገር፡ከአንተ፡ እሻለኹ፤ፊቴን፡ለማየት፡በመጣኽ፡ጊዜ፥የሳኦልን፡ልጅ፡ሜልኮልን፡ካላመጣኽልኝ፡ፊቴን፡አታይም፡አለ።
14ዳዊትም፡ወደሳኦል፡ልጅ፡ወደ፡ኢያቡስቴ፦በመቶ፡ፍልስጥኤማውያን፡ሸለፈት፡ያጨዃትን፡ሚስቴን፡ ሜልኮልን፡ስጠኝ፡ብሎ፡መልእክተኛዎችን፡ሰደደ።
15ኢያቡስቴም፡ልኮ፡ከሌሳ፡ልጅ፡ከባሏ፡ከፈልጢኤል፡ወሰዳት።
16ባሏም፡እያለቀሰ፡ከርሷ፡ጋራ፡ኼደ፥እስከ፡ብራቂም፡ድረስ፡ተከተላት።አበኔርም፦ኺድ፥ተመለስ፡ አለው፤ርሱም፡ተመለሰ።
17አበኔርም፡ለእስራኤል፡ሽማግሌዎች፦አስቀድሞ፡ዳዊት፡በእናንተ፡ላይ፡ንጉሥ፡ይኾን፡ዘንድ፡ፈልጋችኹ፡ ነበር።
18እግዚአብሔርም፡ስለ፡ዳዊት፦በባሪያዬ፡በዳዊት፡እጅ፡ሕዝቤን፡እስራኤልን፡ከፍልስጥኤማውያን፡እጅና፡ ከጠላቶቻቸው፡ዅሉ፡እጅ፡አድናለኹ፡ብሎ፡ተናግሯልና፥እንግዲህ፡አኹን፡አድርጉ፡ብሎ፡ነገራቸው።
19አበኔርም፡ደግሞ፡በብንያም፡ወገን፡ዦሮ፡ተናገረ፤አበኔርም፡ደግሞ፡በእስራኤልና፡በብንያም፡ቤት፡ዅሉ፡ መልካም፡የነበረውን፡ለዳዊት፡ሊነግረው፡ወደ፡ኬብሮን፡ኼደ። 145 አማኝ። 146 ዕብ.፥ኪልአብ፡(ከለአ፡አበ፥ከላ፡ከለከለ፡አባት)። 147 ዕብ.፥ታልማይ፡(ተላሚ፥ዐራሽ)። 148 ዕብ.፥አቢሻሎም፡(አበ፡ሰላም፥የሰላም፡አባት)። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
20አበኔርም፡ከኻያ፡ሰዎች፡ጋራ፡ወደ፡ዳዊት፡ወደ፡ኬብሮን፡መጣ።ዳዊትም፡ለአበኔርና፡ከርሱ፡ጋራ፡ ለነበሩት፡ሰዎች፡ግብዣ፡አደረገላቸው።
21አበኔርም፡ዳዊትን፦ተነሥቼ፡ልኺድ፥ከአንተ፡ጋራም፡ቃል፡ኪዳን፡እንዲያደርጉ፥ነፍስኽም፡እንደ፡ ወደደች፡ዅሉን፡እንድትገዛ፡እስራኤልን፡ዅሉ፡ለጌታዬ፡ለንጉሥ፡ልሰብስብ፡አለው።ዳዊትም፡አበኔርን፡ አሰናበተው፥በደኅናም፡ኼደ።
22በዚያን፡ጊዜም፡የዳዊት፡ባሪያዎችና፡ኢዮአብ፡ከዘመቻ፡ታላቅ፡ምርኮ፡ይዘው፡መጡ።አበኔር፡ግን፡ ዳዊት፡አሰናብቶት፡በደኅና፡ኼዶ፡ነበር፡እንጂ፡በኬብሮን፡አልነበረም።
23ኢዮአብና፡ከርሱም፡ጋራ፡የነበረ፡ጭፍራ፡ዅሉ፡በመጡ፡ጊዜ፦የኔር፡ልጅ፡አበኔር፡ወደ፡ንጉሥ፡ መጣ፥አሰናበተውም፡በደኅናውም፡ኼደ፡ብለው፡ሰዎች፡ለኢዮአብ፡ነገሩት።
24ኢዮአብም፡ወደ፡ንጉሥ፡ገብቶ፦ምን፡አደረግኽ፧እንሆ፥አበኔር፡መጥቶልኽ፡ነበር፤በደኅና፡እንዲኼድ፡ ስለ፡ምን፡አሰናበትኸው፧
25የኔር፡ልጅ፡አበኔር፡ያታልልኽ፡ዘንድ፥መውጫኽንና፡መግቢያኽንም፡ያውቅ፡ዘንድ፥የምታደርገውንም፡ ነገር፡ዅሉ፡ያስተውል፡ዘንድ፡እንደ፡መጣ፡አታውቅምን፧አለው።
26ኢዮአብም፡ከዳዊት፡በወጣ፡ጊዜ፡መልእክተኛዎችን፡ከአበኔር፡በዃላ፡ላከ፥ከሴይርም፡ጕድጓድም፡ መለሱት።ዳዊት፡ግን፡ይህን፡አላወቀም።
27አበኔርም፡ወደ፡ኬብሮን፡በተመለሰ፡ጊዜ፡ኢዮአብ፡በበር፡ውስጥ፡በቈይታ፡ይናገረው፡ዘንድ፡ወደ፡ አጠገቡ፡ወሰደው፤በዚያም፡ለወንድሙ፡ለዐሳሄል፡ደም፡ተበቅሎ፡ሆዱን፡መታው፥ሞተም።
28በዃላም፡ዳዊት፡ይህ፡ነገር፡እንደ፡ተደረገ፡በሰማ፡ጊዜ፦ከኔር፡ልጅ፡ከአበኔር፡ደም፡በእግዚአብሔር፡ ዘንድ፡ለዘለዓለም፡እኔ፡ንጹሕ፡ነኝ፥መንግሥቴም፡ንጹሕ፡ነው፤
29በኢዮአብ፡ራስ፡ላይና፡በአባቱ፡ቤት፡ዅሉ፡ላይ፡ይምጣበት፤በኢዮአብም፡ቤት፡ፈሳሽ፡ነገር፡ያለበት፡ ወይም፡ለምጻም፡ወይም፡ዐንካሳ፡ወይም፡በሰይፍ፡የሚወድቅ፡ወይም፡እንጀራ፡የሌለው፡ሰው፡አይታጣ፡አለ።
30ኢዮአብና፡ወንድሙ፡አቢሳም፡በሰልፍ፡በገባዖን፡ወንድማቸው፡ዐሳሄልን፡ገድሎ፡ነበርና፥አበኔርን፡ ገደሉት።
31ዳዊትም፡ኢዮአብንና፡ከርሱ፡ጋራ፡የነበሩትን፡ሕዝብ፡ዅሉ፦ልብሳችኹን፡ቅደዱ፥ማቅም፡ ልበሱ፥በአበኔርም፡ፊት፡አልቅሱ፡አላቸው።ንጉሡም፡ዳዊት፡ከቃሬዛው፡በዃላ፡ኼደ።
32አበኔርንም፡በኬብሮን፡ቀበሩት፤ንጉሡም፡ድምፁን፡ከፍ፡አድርጎ፡በአበኔር፡መቃብር፡አጠገብ፡ አለቀሰ፤ሕዝቡም፡ዅሉ፡አለቀሱ።ንጉሡም፡ለአበኔር፦
33አበኔር፡ሰነፍ፡እንደሚሞት፡ይምታልን፧
34እጅኽ፡አልታሰረም፥እግርኽም፡በሰንሰለት፡አልተያዘም፤ሰው፡በዐመፀኛዎች፡ፊት፡እንደሚወድቅ፡አንተ፡ እንዲሁ፡ወደቅኽ፡ብሎ፡የልቅሶ፡ቅኔ፡ተቀኘለት።ሕዝቡም፡ዅሉ፡ዋይታ፡አብዝተው፡አለቀሱ።
35ሕዝቡም፡ዅሉ፡ገና፡ሳይመሽ፡ዳዊትን፡እንጀራ፡ይበላ፡ዘንድ፡ሊጋብዙት፡መጡ፤ዳዊት፡ግን፦ፀሓይ፡ ሳትጠልቅ፡እንጀራ፡ወይም፡ሌላ፡ነገር፡ብቀምስ፡እግዚአብሔር፡ይህን፡ያድርግብኝ፥ይህንም፡ይጨምርብኝ፡ ብሎ፤ማለ።
36ሕዝቡም፡ዅሉ፡ይህን፡ተመለከቱ፥ደስ፡አሠኛቸውም፤በሕዝቡም፡ዅሉ፡ፊት፡ንጉሥ፡ያደረገው፡ዅሉ፡ ደስ፡አሠኛቸው።
37በዚያም፡ቀን፡ሕዝቡ፡ዅሉ፡እስራኤልም፡ዅሉ፡የኔር፡ልጅ፡የአበኔር፡ሞት፡ከንጉሡ፡ዘንድ፡እንዳልኾነ፡ ዐወቁ።
38ንጉሡም፡ባሪያዎቹን፦ዛሬ፡በእስራኤል፡ዘንድ፡መኰንንና፡ታላቅ፡ሰው፡እንደ፡ወደቀ፡አታውቁምን፧ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
39እኔም፡ዛሬ፡ምንም፡ለመንገሥ፡የተቀባኹ፡ብኾን፡ደካማ፡ነኝ፤እነዚህም፡ሰዎች፡የጽሩያ፡ልጆች፡ በርትተውብኛል፤እግዚአብሔር፡ክፋት፡በሠራ፡ላይ፡እንደ፡ክፋቱ፡ይመልስበት፡አላቸው።