Skip to content
← 2 Samuel

Chapter 24 · Amharic

2 Samuel

1ደግሞም፡የእግዚአብሔር፡ቍጣ፡በእስራኤል፡ላይ፡ነደደ፥ዳዊትንም፦ኺድ፥እስራኤልንና፡ይሁዳን፡ቍጠር፡ ብሎ፡በላያቸው፡አስነሣው።

2ንጉሡም፡ኢዮአብንና፡ከርሱ፡ጋራ፡የነበሩትን፡የሰራዊት፡አለቃዎች።የሕዝቡን፡ድምር፡ዐውቅ፡ዘንድ፡ ከዳን፡ዠምሮ፡እስከ፡ቤርሳቤሕ፡ድረስ፡ተመላለሱ፥ሕዝቡንም፡ቍጠሯቸው፡አላቸው።

3ኢዮአብም፡ንጉሡን፦የጌታዬ፡የንጉሡ፡ዐይን፡እያየ፡አምላክኽ፡እግዚአብሔር፡ዛሬ፡ካለው፡ሕዝብ፡ መጠን፡በላይ፡መቶ፡ዕጥፍ፡ይጨምርበት፤ጌታዬ፡ንጉሡ፡ግን፡ይህን፡ነገር፡ለምን፡ይወዳ፟ል፧አለው።

4ነገር፡ግን፥የንጉሡ፡ቃል፡በኢዮአብና፡በሰራዊቱ፡አለቃዎች፡ላይ፡አሸነፈ።ኢዮአብና፡የሰራዊቱ፡ አለቃዎችም፡የእስራኤልን፡ሕዝብ፡ይቈጥሩ፡ዘንድ፡ከንጉሥ፡ዘንድ፡ወጡ።

5ዮርዳኖስንም፡ተሻገሩ፤በጋድ፡ሸለቆ፡መካከል፡ባለችው፡በኢያዜር፡ከተማ፡ቀኝ፡በኩል፡በዐሮዔር፡ላይ፡ ሰፈሩ።

6ወደ፡ገለዓድም፡ወደተባሶን፡አዳሰይ፡አገር፡መጡ፤ወደ፡ዳንየዓንም፡ደረሱ፥ወደ፡ሲዶናም፡ዞሩ፥

7ወደጢሮስም፡ምሽግ፡ወደዔዊያውያንና፡ወደከነዓናውያንም፡ከተማዎች፡ዅሉ፡መጡ፤በይሁዳም፡ደቡብ፡ በኩል፡በቤርሳቤሕ፡ወጡ።

8በአገሪቱም፡ዅሉ፡ላይ፡ተመላልሰው፡ከዘጠኝ፡ወርና፡ከኻያ፡ቀን፡በዃላ፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡መጡ።

9ኢዮአብም፡የሕዝቡን፡ቍጥር፡ድምር፡ለንጉሡ፡ሰጠ፤በእስራኤልም፡ሰይፍ፡የሚመዙ፟፡ስምንት፡መቶ፡ ሺሕ፡ጽኑዓን፡ሰዎች፡ነበሩ፤የይሁዳም፡ሰዎች፡ዐምስት፡መቶ፡ሺሕ፡ነበሩ።

10ሕዝቡንም፡ከቈጠረ፡በዃላ፡ዳዊትን፡ልቡ፡መታው፤ዳዊትም፡እግዚአብሔርን፦ባደረግኹት፡ነገር፡እጅግ፡ በድያለኹ፤አኹን፡ግን፥አቤቱ፥ታላቅ፡ስንፍና፡አድርጌያለኹና፡የባሪያኽን፡ኀጢአት፡ታርቅ፡ዘንድ፡ እለምንኻለኹ፡አለው።

11ዳዊትም፡ማልዶ፡በተነሣ፡ጊዜ፥የእግዚአብሔር፡ቃል፡ወደዳዊት፡ባለራእይ፡ወደ፡ነቢዩ፡ወደ፡ጋድ፡ እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦

12ኺድ፡ለዳዊት፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ሦስት፡ነገሮች፡በፊትኽ፡አኖራለኹ፤አደርግብኽ፡ዘንድ፡ ከነርሱ፡አንዱን፡ምረጥ፡ብለኽ፡ንገረው፡አለው።

13ጋድም፡ወደ፡ዳዊት፡መጥቶ፦የሦስት፡ዓመት፡ራብ፡በአገርኽ፡ላይ፡ይምጣብኽን፧ወይስ፡ጠላቶችኽ፡ 156 ዕብ.፥አሒያም፡(የእናት፡ወንድም) 157 ዕብ.፥ከርመሊይ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org እያሳደዱኽ፡ሦስት፡ወር፡ከነርሱ፡ትሸሽን፧ወይስ፡የሦስት፡ቀን፡ቸነፈር፡በአገርኽ፡ላይ፡ይኹን፧አኹንም፡ ለላከኝ፡ምን፡መልስ፡እንደምሰጥ፡ዐስብና፡መርምር፡ብሎ፡ነገረው።

14ዳዊትም፡ጋድን፦እጅግ፡ተጨንቄያለኹ፤ምሕረቱ፡ብዙ፡ነውና፥በእግዚአብሔር፡እጅ፡እንውደቅ፤በሰው፡ እጅ፡ግን፡አልውደቅ፡አለው።

15ዳዊትም፡ቸነፈሩን፡መረጠ፤የስንዴም፡መከር፡ወራት፡በኾነ፡ጊዜ፡ቸነፈሩ፡በሕዝቡ፡መካከል፡ ዠመረ፤ከሕዝቡም፡ሰባ፡ሺሕ፡ሰው፡ሞተ።

16የእግዚአብሔርም፡መልአክ፡ኢየሩሳሌምን፡ያጠፋት፡ዘንድ፡እጁን፡በዘረጋ፡ጊዜ፡እግዚአብሔር፡ስለ፡ ክፉው፡ነገር፡ዐዘነ፥ሕዝቡንም፡የሚያጠፋውን፡መልአክ፦እንግዲህ፡በቃኽ፤እጅኽን፡መልስ፡ አለው።የእግዚአብሔርም፡መልአክ፡በኢያቡሳዊው፡በኦርና፡ዐውድማ፡አጠገብ፡ነበረ።

17ዳዊትም፡ሕዝቡን፡የሚመታውን፡መልአክ፡ባየ፡ጊዜ፡እግዚአብሔርን፦እንሆ፥እኔ፡በድያለኹ፡ጠማማም፡ ሥራ፡እኔ፡አድርጌያለኹ፤እነዚህ፡በጎች፡ግን፡እነርሱ፡ምን፡አደረጉ፧እጅኽ፡በእኔና፡በአባቴ፡ቤት፡ላይ፡ እንድትኾን፡እለምንኻለኹ፡ብሎ፡ተናገረው።

18በዚያም፡ቀን፡ጋድ፡ወደ፡ዳዊት፡መጥቶ፦ውጣ፥በኢያቡሳዊው፡በኦርና፡ዐውድማ፡ለእግዚአብሔር፡ መሠዊያ፡ሥራ፡አለው።

19ዳዊትም፡እግዚአብሔር፡እንዳዘዘው፡እንደ፡ጋድ፡ነገር፡ወጣ።

20ኦርናም፡ሲመለከት፡ንጉሡና፡ባሪያዎቹ፡ወደ፡ርሱ፡ሲመጡ፡አየ፤ኦርናም፡ወጥቶ፡በንጉሡ፡ፊት፡ በምድር፡ላይ፡በግንባሩ፡ተደፋ።

21ኦርናም፦ጌታዬን፡ንጉሡን፡ወደ፡ባሪያው፡ያመጣው፡ምክንያት፡ምንድር፡ ነው፧አለ።ዳዊትም፦መቅሠፍቱ፡ከሕዝቡ፡ላይ፡ይከለከል፡ዘንድ፡ዐውድማውን፡ከአንተ፡ገዝቼ፡ ለእግዚአብሔር፡መሠዊያ፡ልሠራ፡ነው፡አለው።

22ኦርናም፡ዳዊትን፦ጌታዬ፡ንጉሡ፡እንደ፡ወደደ፡ወስዶ፡ያቅርብ፤እንሆ፥ለሚቃጠል፡መሥዋዕት፡ በሬዎች፥ለሚቃጠልም፡ዕንጨት፡የዐውድማ፡ዕቃና፡የበሬ፡ቀንበር፡አለ።

23ንጉሥ፡ሆይ፥ይህን፡ዅሉ፡ኦርና፡ለንጉሡ፡ይሰጣል፡አለው፤ኦርናም፡ንጉሡን፦አምላክኽ፡ እግዚአብሔር፡ይቀበልኽ፡አለው።

24ንጉሡም፡ኦርናን፦እንዲህ፡አይደለም፥ነገር፡ግን፥በዋጋ፡ከአንተ፡እገዛለኹ፤ለአምላኬም፡ ለእግዚአብሔር፡የሚቃጠል፡መሥዋዕት፡ያለዋጋ፡አላቀርብም፡አለው።ዳዊትም፡ዐውድማውንና፡በሬዎቹን፡ በዐምሳ፡ሰቅል፡ብር፡ገዛ።

25በዚያም፡ዳዊት፡ለእግዚአብሔር፡መሠዊያ፡ሠራ፥የሚቃጠልና፡የደኅንነትንም፡መሥዋዕት፡ አቀረበ።እግዚአብሔርም፡ስለ፡አገሪቱ፡የተለመነውን፡ሰማ፥መቅሠፍቱም፡ከእስራኤል፡ተከለከለ፨ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source