1የዳዊትም፡የመጨረሻ፡ቃሉ፡ይህ፡ነው።ከፍ፡ከፍ፡የተደረገው፥በያዕቆብም፡አምላክ፡ የተቀባው፥በእስራኤል፡ዘንድ፡መልካም፡ባለቅኔ፡የኾነ፥የእሴይ፡ልጅ፡የዳዊት፡ንግግር፤
2የእግዚአብሔር፡መንፈስ፡በእኔ፡ተናገረ፤ቃሉም፡በአንደበቴ፡ላይ፡ነበረ።
3የእስራኤል፡አምላክ፡ተናገረኝ፤የእስራኤል፡ጠባቂ፡እንዲህ፡አለ፦በሰው፡ላይ፡በጽድቅ፡ የሚሠለጥን፥በእግዚአብሔርም፡ፍርሀት፡የሚነግሥ፥
4ርሱ፡እንደ፡ማለዳ፡ብርሃን፡እንደ፡ፀሓይ፡አወጣጥ፥በጧትም፡ያለ፡ደመና፡እንደሚደምቅ፥ከዝናብ፡ በዃላ፡ከምድር፡እንደሚበቅል፡ልምላሜ፡ይኾናል።
5በእውኑ፡ቤቴ፡በእግዚአብሔር፡ዘንድ፡እንዲሁ፡አይደለምን፧ከእኔም፡ጋራ፡በዅሉ፡ነገር፡ቅንና፡ጽኑ፡ የኾነውን፡የዘለዓለም፡ቃል፡ኪዳን፡አድርጓል፤መድኀኒቴንና፡ፈቃዴን፡ዅሉ፡ያበቅላል።
6ዐመፀኛዎች፡ዅሉ፡ግን፡ሰው፡በእጁ፡እንደማይዘው፥እንደተጣለ፡ሾኽ፡ናቸው።
7ማናቸውም፡ሰው፡ይነካው፡ዘንድ፡ቢወደድ፥በእጁ፡ብረትና፡የጦሩን፡የቦ፡ይይዛል፤በሥራቸውም፡በእሳት፡ ፈጽሞ፡ይቃጠላሉ።
8የዳዊት፡ኀያላን፡ስም፡ይህ፡ነው።የአለቃዎች፡አለቃ፡የኾነ፡ከነዓናዊው፡ኢያቡስቴ፡ነበረ፤ርሱም፡ጦሩን፡ አንሥቶ፡ስምንት፡መቶ፡ያኽል፡ባንድ፡ጊዜ፡ገደለ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
9ከርሱም፡በዃላ፡የአሖሓዊው፡የዱዲ፡ልጅ፡ኤልያናን፡ነበረ፤ለሰልፍ፡የተሰበሰቡትን፡ፍልስጥኤማውያንን፡ በተገዳደሩ፡ጊዜ፡ከዳዊት፡ጋራ፡ከሦስቱ፡ኀያላን፡አንዱ፡ርሱ፡ነበረ፤የእስራኤልም፡ሰዎች፡ተመለሱ።
10ርሱ፡ግን፡ተነሥቶ፡እጁ፡እስኪደክምና፡ከሰይፉ፡ጋራ፡እስኪጣበቅ፡ድረስ፡ፍልስጥኤማውያንን፡ መታ፤በዚያም፡ቀን፡እግዚአብሔር፡ታላቅ፡መድኀኒት፡አደረገ፤ሕዝቡም፡ከርሱ፡በዃላ፡ምርኮ፡ለመግፈፍ፡ ብቻ፡ተመለሰ።
11ከርሱም፡በዃላ፡የአሮዳዊው፡የአጌ፡ልጅ፡ሳማ፡ነበረ።ፍልስጥኤማውያንም፡ምስር፡በሞላበት፡ዕርሻ፡ በአንድነት፡ኾነው፡ተከማችተው፡ነበር፤ሕዝቡም፡ከፍልስጥኤማውያን፡ፊት፡ሸሹ።
12ርሱ፡ግን፡በዕርሻው፡መካከል፡ቆሞ፡ጠበቀ፥ፍልስጥኤማውያንንም፡ገደለ፤እግዚአብሔርም፡ታላቅ፡ መድኀኒት፡አደረገ።
13ከሠላሳውም፡አለቃዎች፡ሦስቱ፡ወርደው፡በመከር፡ጊዜ፡ወደ፡ዳዊት፡ወደዓዶላም፡ዋሻ፡ መጡ፤የፍልስጥኤማውያንም፡ጭፍራ፡በራፋይም፡ሸለቆ፡ሰፍሮ፡ነበር።
14በዚያ፡ጊዜም፡ዳዊት፡በምሽጉ፡ውስጥ፡ነበረ፥የፍልስጥኤማውያንም፡ጭፍራ፡በዚያ፡ጊዜ፡በቤተ፡ልሔም፡ ነበረ።
15ዳዊትም፦በበሩ፡አጠገብ፡ካለችው፡ከቤተ፡ልሔም፡ምንጭ፡ውሃ፡ማን፡ባጠጣኝ፧ብሎ፡ተመኘ።
16ሦስቱም፡ኀያላን፡የፍልስጥኤማውያንን፡ሰራዊት፡ቀደ፟ው፡ኼዱ፥በበሩም፡አጠገብ፡ካለችው፡ከቤተ፡ልሔም፡ ምንጭ፡ውሃ፡ቀዱ፥ይዘውም፡ለዳዊት፡አመጡለት፤ርሱ፡ግን፡ሊጠጣ፡አልወደደም፥ነገር፡ ግን፥ለእግዚአብሔር፡አፍሶ፟፦
17አቤቱ፥ይህን፡ኣደርግ፡ዘንድ፡ከእኔ፡ይራቅ፤በነፍሳቸው፡ደፍረው፡የኼዱ፡ሰዎች፡ደም፡ አይደለምን፧ብሎ፡ይጠጣ፡ዘንድ፡አልወደደም።ሦስቱ፡ኀያላን፡ያደረጉት፡ይህ፡ነው።
18የጽሩያም፡ልጅ፡የኢዮአብ፡ወንድም፡አቢሳ፡የሠላሳው፡አለቃ፡ነበረ።ርሱም፡ጦሩን፡በሦስቱ፡መቶ፡ላይ፡ አንሥቶ፡ገደላቸው፤ስሙም፡እንደ፡ሦስቱ፡ተጠርቶ፡ነበር።
19ርሱ፡በሠላሳው፡መካከል፡የከበረ፡አልነበረምን፧ስለዚህ፡አለቃቸው፡ኾኖ፡ነበር፤ነገር፡ግን፥ወደ፡ሦስቱ፡ አልደረሰም።
20በቀብጽኤል፡የነበረው፡ታላቅ፡ሥራ፡ያደረገው፡የጽኑዕ፡ሰው፡የዮዳዔ፡ልጅ፡በናያስ፡የሞዐባዊውን፡ የቀብስኤልን፡ኹለት፡ልጆች፡ገደለ፤በዐመዳዩም፡ወራት፡ወርዶ፡በጕድጓድ፡ውስጥ፡አንበሳ፡ገደለ።
21ረዥሙንም፡ግብጻዊ፡ሰው፡ገደለ፤ግብጻዊው፡በእጁ፡ጦር፡ነበረው፤በናያስ፡ግን፡በትር፡ይዞ፡ወደ፡ ርሱ፡ወረደ፥ከግብጻዊውም፡እጅ፡ጦሩን፡ነቅሎ፡በገዛ፡ጦሩ፡ገደለው።
22የዮዳዔ፡ልጅ፡በናያስ፡ያደረገው፡ይህ፡ነው፤ስሙም፡እንደ፡ሦስቱ፡ኀያላን፡ተጠርቶ፡ነበር።
23ከሠላሳውም፡ይልቅ፡የከበረ፡ነበረ፥ነገር፡ግን፥ወደ፡ሦስቱ፡አልደረሰም።ዳዊትም፡በክብር፡ዘበኛዎቹ፡ ላይ፡ሾመው።
24የኢዮአብም፡ወንድም፡ዐሳሄል፡በሠላሳው፡መካከል፡ነበረ፥የቤተ፡ልሔም፡ሰው፡የዱዲ፡
25ልጅ፡ኤልያናን፥አሮዳዊው፡ሳማ፥ሒሮዳዊው፡ኤሊቃ፥
26ፈልጣዊው፡ሴሌስ፥የቴቁሐዊው፡የዒስካ፡ልጅ፡ዒራስ፥
27ዓናቶታዊው፡አቢዔዜር፥ኩሳታዊው፡ምቡናይ፥
28አሖሓዊው፡ጸልሞን፥ነጦፋዊው፡ኖኤሬ፥
29የነጦፋዊው፡የበዓና፡ልጅ፡ሔሌብ፥ከብንያም፡ወገን፡
30ከጊብዓ፡የሪባይ፡ልጅ፡ኢታይ፥ጲርዓቶናዊው፡በናያስ፥የገዓስ፡ወንዝ፡ሰው፡ሂዳይ፥ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
31ዐረባዊው፡አቢዓልቦን፥በርሑማዊው፡ዓዝሞት፥
32ሸዓልቦናዊው፡ኤሊያሕባ፥የአሳን፡ልጆች፥ዮናታን፥
33አሮዳዊው፡ሳማ፡የአሮዳዊው፡የአራር፡ልጅ፡አምናን ፥
34የማዕካታዊው፡ልጅ፡የአሐስባይ፡ልጅ፡ኤሌፋላት፥የጊሎናዊው፡የአኪጦፌል፡ልጅ፡ኤልያብ፥
35ቀርሜሎሳዊው ፡ሐጽሮ፥አርባዊው፡ፈዓራይ፥
36የሱባ፡ሰው፡የናታን፡ልጅ፡ይግአል፥ጋዳዊው፡
37ባኒ፥የጽሩያ፡ልጅ፣የኢዮአብ፡ጋሻ፡ዣግሬዎች፥አሞናዊው፡ጼሌቅ፥ብኤሮታዊው፡
38ነሃራይ፥ይትራዊው፡ዒራስ፥ይትራዊው፡ጋሬብ፥
39ኬጢያዊው፡ኦርዮ፤ዅሉ፡በዅሉ፡ሠላሳ፡ሰባት፡ናቸው።