Skip to content
← 2 Samuel

Chapter 22 · Amharic

2 Samuel

1ዳዊትም፡እግዚአብሔር፡ከሳኦል፡እጅና፡ከጠላቶቹ፡እጅ፡ዅሉ፡ባዳነው፡ቀን፡የዚህን፡ቅኔ፡ቃል፡ ለእግዚአብሔር፡ተናገረ።

2እንዲህም፡አለ፦እግዚአብሔር፡አለቴ፣ዐምባዬ፣መድኀኒቴ፡ነው፤

3እግዚአብሔር፡ጠባቂዬ፡ነው፥በርሱም፡እታመናለኹ፤ጋሻዬና፡የረድኤቴ፡ቀንድ፥መጠጊያዬና፡ መሸሸጊያዬ፥መድኀኒቴ፡ሆይ፥ከግፍ፡ሥራ፡ታድነኛለኽ።

4ምስጋና፡የሚገ፟ባ፟ውን፡እግዚአብሔርን፡እጠራለኹ፤ከጠላቶቼም፡እድናለኹ።

5የሞት፡ጣር፡ያዘኝ፤የዐመፅ፡ፈሳሽም፡አስፈራኝ፤ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

6የሲኦል፡ጣር፡ከበበኝ፤የሞት፡ወጥመድ፡ደረሰብኝ።

7በጨነቀኝ፡ጊዜ፡እግዚአብሔርን፡ጠራኹት፥ወደ፡አምላኬም፡ጮኽኹ፤ከመቅደሱም፡ቃሌን፡ ሰማኝ፥ጩኸቴም፡በፊቱ፡ወደ፡ዦሮው፡ገባ።

8ምድርም፡ተንቀጠቀጠች፥ተናወጠችም፥የሰማዮችም፡መሠረቶች፡ተነቃነቁ፤እግዚአብሔርም፡ ተቈጥቷልና፥ተንቀጠቀጡ።

9ከቍጣው፡ጢስ፡ወጣ፥ከአፉም፡የሚበላ፡እሳት፡ነደደ፤ፍምም፡ከርሱ፡በራ።

10ሰማዮችን፡ዝቅ፡ዝቅ፡አደረገ፥ወረደም፤ጨለማም፡ከእግሩ፡በታች፡ነበረ።

11በኪሩብም፡ላይ፡ተቀምጦ፡በረረ፤በነፋስም፡ክንፍ፡ኾኖ፡ታየ፤

12መሰወሪያውን፡ጨለማ፥በዙሪያውም፡የነበረውን፡ድንኳን፥በደመና፡ውስጥ፡የነበረ፡የጨለማ፡ውሃ፡ አደረገ።

13በፊቱም፡ካለው፡ብርሃን፡የተነሣ፡ፍም፡ተቃጠለ።

14እግዚአብሔርም፡ከሰማያት፡አንጐደጐደ፥ልዑልም፡ቃሉን፡ሰጠ፤

15ፍላጻውን፡ላከ፥በተናቸውም፡መብረቆችን፡ላከ፥አወካቸውም።

16ከእግዚአብሔር፡ዘለፋ፥ከመዓቱም፡መንፈስ፡እስትንፋስ፡የተነሣ፥የባሕር፡ፈሳሾች፡ታዩ፥የዓለም፡ መሠረቶችም፡ተገለጡ።

17ከላይ፡ሰደደ፥ወሰደኝም፤ከብዙ፡ውሃዎችም፡አወጣኝ።

18ከብርቱዎች፡ጠላቶቼ፥ከሚጠሉኝም፡አዳነኝ፤በርትተውብኝ፡ነበርና።

19በመከራዬ፡ቀን፡ደረሱብኝ፤እግዚአብሔር፡ግን፡ደገፋዬ፡ኾነ።

20ወደ፡ሰፊ፡ስፍራም፡አወጣኝ፤ወዶ፟ኛልና፥አዳነኝ።

21እግዚአብሔር፡እንደ፡ጽድቄ፡ይከፍለኛል፤እንደ፡እጄ፡ንጽሕና፡ይመልስልኛል፤

22የእግዚአብሔርን፡መንገድ፡ጠብቄያለኹና፥በአምላኬም፡አላመፅኹምና።

23ፍርዱ፡ዅሉ፡በፊቴ፡ነበረና፤ከሥርዐቱም፡አልራቅኹምና።

24በርሱ፡ዘንድ፡ቅን፡ነበርኹ፥ከኀጢአቴም፡ተጠበቅኹ።

25እግዚአብሔርም፡እንደ፡ጽድቄ፥እንደ፡እጄም፡ንጽሕና፡በዐይኖቹ፡ፊት፡መለሰልኝ።

26ከቸር፡ሰው፡ጋራ፡ቸር፡ኾነኽ፡ትገኛለኽ፤ከቅን፡ሰው፡ጋራ፡ቅን፡ኾነኽ፡ትገኛለኽ፤

27ከንጹሕ፡ጋራ፡ንጹሕ፡ኾነኽ፡ትገኛለኽ፤ከጠማማም፡ጋራ፡ጠማማ፡ኾነኽ፡ትገኛለኽ።

28አንተ፡የተጠቃውን፡ሕዝብ፡ታድናለኽና፤የትዕቢተኛዎችን፡ዐይን፡ግን፡ታዋርዳለኽ።

29አቤቱ፥አንተ፡መብራቴ፡ነኽና፤እግዚአብሔርም፡ጨለማዬን፡ያበራል።

30ባንተ፡ኀይል፡በጭፍራ፡ላይ፡እሮጣለኹና፤በአምላኬም፡ቅጥሩን፡እዘላ፟ለኹና።

31የአምላክ፡መንገድ፡ፍጹም፡ነው፤የእግዚአብሔር፡ቃል፡የነጠረ፡ነው፤በርሱ፡ለሚታመኑት፡ዅሉ፡ጋሻ፡ ነው።

32ከእግዚአብሔር፡በቀር፡አምላክ፡ማን፡ነው፧ከአምላካችንስ፡በቀር፡ዐምባ፡ማን፡ነው፧

33ኀይልን፡የሚያስታጥቀኝ፥መንገዴንም፡የሚያቃና፥

34እግሮቼን፡እንደ፡ብሖር፡እግሮች፡የሚያበረታ፥በኰረብታዎችም፡የሚያቆመኝ፡እግዚአብሔር፡ነው። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

35እጆቼን፡ሰልፍ፡ያስተምራል፤በክንዴም፡የናስ፡ቀስት፡እገትራለኹ።

36የማዳንኽንም፡ጋሻ፡ሰጠኸኝ፤ተግሣጽኽም፡አሳደገኝ።

37አረማመዴን፡በበታቼ፡አሰፋኽ፥እግሮቼም፡አልተንሸራተቱም።

38ጠላቶቼን፡አሳድዳቸዋለኹ፥አጠፋቸውማለኹ፤እስካጠፋቸውም፡ድረስ፡አልመለስም።

39አስጨንቃቸዋለኹ፡መቆምም፡አይችሉም፥ከእግሬም፡በታች፡ይወድቃሉ።

40ለሰልፍም፡ኀይልን፡ታስታጥቀኛለኽ፤በላዬ፡የቆሙትን፡በበታቼ፡ታስገዛቸዋለኽ።

41የጠላቶቼን፡ዠርባ፡ሰጠኸኝ፥የሚጠሉኝንም፡አጠፋኻቸው።

42ጮኹ፥የሚረዳቸውም፡አልነበረም፤ወደ፡እግዚአብሔር፡ጮኹ፥አልሰማቸውምም።

43እንደምድር፡ትቢያ፡ፈጨዃቸው፤እንደ፡አደባባይም፡ጭቃ፡ረገጥዃቸው፥ደቀደቅዃቸውም።

44ከሕዝብ፡ክርክር፡ታድነኛለኽ፤የአሕዛብም፡ራስ፡አድርገኽ፡ትሾመኛለኽ፤የማላውቀው፡ሕዝብም፡ ይገዛልኛል።

45የባዕድ፡ልጆች፡ደለሉኝ፤በዦሮ፡ሰምተው፡ተገዙልኝ።

46የባዕድ፡ልጆች፡እየጠፉ፡ይኼዳሉ፤ከተዘጉ፡ስፍሮች፡እየተንቀጠቀጡ፡ይወጣሉ።

47እግዚአብሔር፡ሕያው፡ነው፥ጠባቂዬም፡ቡሩክ፡ነው፤የመድኀኒቴ፡ጠባቂ፡አምላኬ፡ከፍ፡ከፍ፡ይበል፤

48በቀሌን፡የሚመልስልኝ፡አምላክ፥አሕዛብን፡በበታቼ፡የሚያስገዛ፥

49ከጠላቶቼ፡የሚያወጣኝ፡ርሱ፡ነው፤በእኔም፡ላይ፡ከቆሙ፡ከፍ፡ከፍ፡ታደርገኛለኽ፤ከግፈኛ፡ሰው፡ ታድነኛለኽ።

50አቤቱ፥ስለዚህ፡በአሕዛብ፡ዘንድ፡አመሰግንኻለኹ፥ለስምኽም፡እዘምራለኹ።

51የንጉሡን፡መድኀኒት፡ታላቅ፡ያደርጋል፤ቸርነቱንም፡ለቀባው፥ለዳዊትና፡ለዘሩ፥ለዘለዓለም፡ይሰጣል።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source