Skip to content
← 2 Samuel

Chapter 21 · Amharic

2 Samuel

1በዳዊትም፡ዘመን፡ሦስት፡ዓመት፡ያኽል፡ቀጥሎ፡ራብ፡ኾነ፤ዳዊትም፡የእግዚአብሔርን፡ፊት፡ ጠየቀ።እግዚአብሔርም፦የገባዖንን፡ሰዎች፡ስለ፡ገደለ፡በሳኦልና፡በቤቱ፡ላይ፡ደም፡አለበት፡አለ።

2ንጉሡም፡የገባዖንን፡ሰዎች፡ጠራ፤የገባዖን፡ሰዎችም፡ከአሞራውያን፡የተረፉ፡ነበሩ፡እንጂ፡ከእስራኤል፡ ልጆች፡ወገን፡አልነበሩም፤የእስራኤልም፡ልጆች፡ምለውላቸው፡ነበር፤ሳኦል፡ግን፡ለእስራኤል፡ልጆችና፡ ለይሁዳ፡ስለ፡ቀና፡ሊገድላቸው፡ወዶ፟፡ነበር።

3ዳዊትም፡የገባዖንን፡ሰዎች፦የእግዚአብሔርን፡ርስት፡ትባርኩ፡ዘንድ፡ምን፡ላድርግላችኹ፧ማስተስረያውስ፡ ምንድር፡ነው፧አላቸው።

4የገባዖን፡ሰዎችም፦በእኛና፡በሳኦል፡ወይም፡በእኛና፡በቤቱ፡መካከል፡ያለው፡የብርና፡የወርቅ፡ነገር፡ አይደለም፤ከእስራኤልም፡ወገን፡እኛ፡የምንገድለው፡የለም፡አሉት።ርሱም፦የምትናገሩትን፡አደርግላችዃለኹ፡ አለ።

5ንጉሡንም፦እኛን፡ካጠፋ፥በእስራኤልም፡ዳርቻ፡ዅሉ፡እንዳንቀመጥ፡መፍረሳችንን፡

6ካሰበው፡ሰው፡ልጆች፡ሰባት፡ሰዎች፡አሳልፈኽ፡ስጠንና፡ከእግዚአብሔር፡በተመረጠው፡በሳኦል፡አገር፡ በጊብዓ፡ለእግዚአብሔር፡እንሰቅላቸዋለን፡አሉት።ንጉሡም፦እሰጣችዃለኹ፡አለ።

7ንጉሡም፡በሳኦል፡ልጅ፡በዮናታንና፡በዳዊት፡መካከል፡ስለነበረው፡ስለእግዚአብሔር፡መሐላ፡የሳኦልን፡ልጅ፡ የዮናታንን፡ልጅ፡ሜምፊቦስቴን፡አዳነ። 155 ዕብ.፥ዒይራ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

8ንጉሡም፡ለሳኦል፡የወለደቻቸውን፡የኢዮሄል፡ልጅ፡የሪጽፋን፡ኹለቱን፡ልጆች፡ሄርሞንንና፡ሜምፊቦስቴን፡ ለመሐላታዊውም፡ለቤርዜሊ፡ልጅ፡ለኤስድሪኤል፡የወለደቻቸውን፡የሳኦልን፡ልጅ፡የሜሮብን፡ዐምስቱን፡ልጆች፡ ወሰደ፥

9ለገባዖንም፡ሰዎች፡እጅ፡አሳልፎ፡ሰጣቸው፤በእግዚአብሔርም፡ፊት፡በተራራው፡ላይ፡ሰቀሏቸው፥ሰባቱም፡ በአንድነት፡ወደቁ፤እኽል፡በሚታጨድበት፡ወራት፡በገብሱ፡መከር፡መዠመሪያ፡ተገደሉ።

10የኢዮሄልም፡ልጅ፡ሪጽፋ፡ማቅ፡ወስዳ፡ከመከር፡ወራት፡ዠምሮ፡ዝናብ፡ከሰማይ፡እስኪዘንብ፡ድረስ፡ በድንጋይ፡ላይ፡ዘረጋችው፤በቀንም፡ወፎች፡በሌሊትም፡አራዊት፡ያርፉባቸው፡ዘንድ፡አልተወችም።

11የሳኦልም፡ቁባት፡የኢዮሄል፡ልጅ፡ሪጽፋ፡ያደረገችውን፡ለዳዊት፡ነገሩት።

12ዳዊትም፡ኼደ፥ሳኦልንም፡በጊልቦዓ፡በገደሉ፡ጊዜ፡ፍልስጥኤማውያን፡ከሰቀሏቸው፡ስፍራ፡ከቤትሳን፡ አደባባይ፡ከሰረቁት፡ከኢያቢስ፡ገለዓድ፡ሰዎች፡የሳኦልንና፡የልጁን፡የዮናታንን፡ዐጥንት፡ወሰደ፤

13ከዚያም፡የሳኦልንና፡የልጁን፡የዮናታንን፡ዐጥንት፡ይዞ፡መጣ፤የተሰቀሉትንም፡ሰዎች፡ዐጥንት፡ሰበሰቡ።

14የሳኦልንና፡የልጁን፡የዮናታንን፡ዐጥንት፡በብንያም፡አገር፡በጼላ፡በአባቱ፡በቂስ፡መቃብር፡ ቀበሩት፤ንጉሡም፡ያዘዘውን፡ዅሉ፡አደረጉ።ከዚያም፡በዃላ፡እግዚአብሔር፡ስለ፡አገሩ፡የተለመነውን፡ሰማ።

15በፍልስጥኤማውያንና፡በእስራኤልም፡መካከል፡ደግሞ፡ሰልፍ፡ነበረ፤ዳዊትም፡ከርሱም፡ጋራ፡ባሪያዎቹ፡ ወረዱ፥ከፍልስጥኤማውያንም፡ጋራ፡ተዋጉ፤ዳዊትም፡ደከመ።

16ከራፋይም፡ወገን፡የነበረው፡ይሽቢብኖብ፡ዳዊትን፡ይገድል፡ዘንድ፡ዐሰበ፤የጦሩም፡ሚዛን፡ክብደት፡ሦስት፡ መቶ፡ሰቅል፡ናስ፡ነበረ፥ዐዲስም፡የጦር፡መሣሪያ፡ታጥቆ፡ነበር።

17የጽሩያም፡ልጅ፡አቢሳ፡አዳነው፥ፍልስጥኤማዊውንም፡መቶ፟፡ገደለው።ያን፡ጊዜም፡የዳዊት፡ ሰዎች፦አንተ፡የእስራኤልን፡መብራት፡እንዳታጠፋ፡ከእንግዲህ፡ወዲህ፡ከእኛ፡ጋራ፡ለሰልፍ፡አትወጣም፡ ብለው፡ማሉለት።

18ከዚህም፡በዃላ፡እንደ፡ገና፡በጎብ፡ላይ፡ከፍልስጥኤማውያን፡ጋራ፡ሰልፍ፡ኾነ፥ኩሳታዊውም፡ሴቦካይ፡ ከራፋይም፡ወገን፡የነበረውን፡ሳፍን፡ገደለ።

19ደግሞም፡በጎብ፡ላይ፡ከፍልስጥኤማውያን፡ጋራ፡ሰልፍ፡ነበረ፤የቤተ፡ልሔማዊውም፡የየዓሬኦርጊም፡ልጅ፡ ኤልያናን፡የጦሩ፡የቦ፡እንደ፡ሸማኔ፡መጠቅለያ፡የነበረውን፡የጌት፡ሰው፡ጎልያድን፡ገደለ።

20ደግሞም፡በጌት፡ላይ፡ሰልፍ፡ኾነ፤በዚያም፡በእጁና፡በእግሩ፡ስድስት፡ስድስት፡ዅላዅሉ፡ኻያ፡አራት፡ ጣቶች፡የነበሩት፡አንድ፡ረዥም፡ሰው፡ነበረ፤ርሱ፡ደግሞ፡ከራፋይም፡የተወለደ፡ነበረ።

21እስራኤልንም፡በተገዳደረ፡ጊዜ፥የዳዊት፡ወንድም፣የሳማ፡ልጅ፣ዮናታን፡ገደለው።

22እነዚያም፡አራቱ፡በጌት፡ውስጥ፡ከራፋይም፡የተወለዱ፡ነበሩ፤በዳዊትም፡እጅ፣በባሪያዎቹም፡እጅ፡ወደቁ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source