Skip to content
← Amos

Chapter 1 · Amharic

Amos

1በቴቁሔ፡ከላም፡ጠባቂዎች፡መካከል፡የነበረ፡ዓሞጽ፡በይሁዳ፡ንጉሥ፡በዖዝያን፡ዘመን፥በእስራኤልም፡ ንጉሥ፡በዮአስ፡ልጅ፡በኢዮርብዓም፡ዘመን፥የምድር፡መናወጥ፡ከኾነበቱ፡ከኹለት፡ዓመት፡በፊት፡ስለ፡ እስራኤል፡ያየው፡ቃል፡ይህ፡ነው፦

2እንዲህም፡አለ፦እግዚአብሔር፡በጽዮን፡ኾኖ፡ድምፁን፡ከፍ፡አድርጎ፡ይጮኻል፥በኢየሩሳሌምም፡ኾኖ፡ ቃሉን፡ይሰጣል፤የእረኛዎችም፡ማሰማሪያዎች፡ያለቅሳሉ፥የቀርሜሎስም፡ራስ፡ይደርቃል።

3እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ገለዓድን፡በብረት፡መንኰራኵር፡አኺዷልና፥ስለ፡ሦስት፡ወይም፡ስለ፡ አራት፡የደማስቆ፡ኀጢአት፡መቅሠፍቴን፡ከማድረግ፡አልመለስም።

4በአዛሄል፡ቤት፡እሳትን፡እሰዳ፟ለኹ፥የወልደ፡አዴርንም፡አዳራሾች፡ትበላለች።

5የደማስቆንም፡መወርወሪያ፡እሰብራለኹ፥ተቀማጮችንም፡ከአዌን፡ሸለቆ፡አጠፋለኹ፥በትር፡የያዘውንም፡ ከዔዴን፡ቤት፡አጠፋለኹ፤የሶርያም፡ሕዝብ፡ወደ፡ቂር፡ይማረካል፥ይላል፡እግዚአብሔር።

6እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ለኤዶምያስ፡አሳልፈው፡ይሰጧቸው፡ዘንድ፡ምርኮኛዎችን፡ዅሉ፡ ማርከዋልና፥ስለ፡ሦስት፡ወይም፡ስለ፡አራት፡የጋዛ፡ኀጢአት፡መቅሠፍቴን፡ከማድረግ፡አልመለስም።

7በጋዛ፡ቅጥር፡ላይ፡እሳትን፡እሰዳ፟ለኹ፥አዳራሾቿንም፡ትበላለች።

8ተቀማጮችን፡ከአዛጦን፡አጠፋለኹ፥በትር፡የያዘውንም፡ከአስቀሎና፡አጠፋለኹ፤እጄንም፡በዐቃሮን፡ላይ፡ እመልሳለኹ፥ከፍልስጥኤማውያንም፡የቀሩት፡ይጠፋሉ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።

9እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ምርኮኛዎችን፡ዅሉ፡ለኤዶምያስ፡አሳልፈው፡ሰጥተዋልና፥የወንድሞችንም፡ ቃል፡ኪዳን፡አላሰቡምና፡ስለ፡ሦስት፡ወይም፡ስለ፡አራት፡የጢሮስ፡ኀጢአት፡መቅሠፍቴን፡ከማድረግ፡ አልመለስም።

10በጢሮስ፡ቅጥር፡ላይ፡እሳትን፡እሰዳ፟ለኹ፥አዳራሾቿንም፡ትበላለች።

11እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ወንድሙን፡በሰይፍ፡አሳዶ፟ታልና፥ርኅራኄንም፡ዅሉ፡ጥሏልና፥ቍጣውም፡ ዅልጊዜ፡ቀዷ፟ልና፥መዓቱንም፡ለዘለዓለም፡ጠብቋልና፥ስለ፡ሦስት፡ወይም፡ስለ፡አራት፡የኤዶምያስ፡ኀጢአት፡ መቅሠፍቴን፡ከማድረግ፡አልመለስም።

12በቴማን፡ላይ፡እሳትን፡እሰዳ፟ለኹ፥የባሶራንም፡አዳራሾች፡ትበላለች።

13እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ዳርቻቸውን፡ያሰፉ፡ዘንድ፡የገለዓድን፡እርጕዞች፡ቀደ፟ዋልና፥ስለ፡ሦስት፡ ወይም፡ስለ፡አራት፡የዐሞን፡ልጆች፡ኀጢአት፡መቅሠፍቴን፡ከማድረግ፡አልመለስም።

14በረባት፡ቅጥር፡ላይ፡እሳትን፡አነዳ፟ለኹ፤በሰልፍም፡ቀን፡በጩኸት፡በዐውሎ፡ነፋስም፡ቀን፡በሁከት፡ አዳራሾቿን፡ትበላለች፤

15ንጉሣቸውም፡ከአለቃዎቹ፡ጋራ፡በአንድነት፡ይማረካል፥ይላል፡እግዚአብሔር።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source