1የይሁዳ፡ንጉሥ፡ኢዮአቄም፡በነገሠ፡በሦስተኛው፡ዓመት፡የባቢሎን፡ንጉሥ፡ናቡከደነጾር፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ መጥቶ፡ከበባት።
2ጌታም፡የይሁዳን፡ንጉሥ፡ኢዮአቄምን፡ከእግዚአብሔርም፡ቤት፡ዕቃ፡ከፍሎ፡በእጁ፡አሳልፎ፡ ሰጠው፤ርሱም፡ወደሰናዖር፡ምድር፡ወደአምላኩ፡ቤት፡ወሰደው፥ዕቃውንም፡ወደአምላኩ፡ግምጃ፡ቤት፡ አገባው።
4ንጉሡም፡ነውር፡የሌለባቸውንና፡መልከ፡መልካሞቹን፥በጥበብ፡ዅሉ፡የሚያስተውሉትን፡ዕውቀትም፡ የሞላባቸውን፡ብልኀተኛዎችና፡አስተዋዮች፡የኾኑትን፥በንጉሡም፡ቤት፡መቆም፡የሚችሉትን፡ብላቴናዎች፡ ከእስራኤል፡ልጆች፡ከነገሥታቱና፡ከመሳፍንቱ፡ዘር፡ያመጣ፡ዘንድ፥የከለዳውያንንም፡ትምህርትና፡ቋንቋ፡ ያስተምሯቸው፡ዘንድ፥ለጃን፡ደረባዎች፡አለቃ፡ለአስፋኔዝ፡ነገረ።
5ንጉሡም፡ሦስት፡ዓመት፡ያሳድጓቸው፡ዘንድ፥ከዚያም፡በዃላ፡በንጉሡ፡ፊት፡ይቆሙ፡ዘንድ፥ከንጉሡ፡ መብል፡ከሚጠጣውም፡ጠጅ፡በየዕለቱ፡ድርጓቸውን፡አዘዘላቸው።
6በእነዚህም፡መካከል፡ከይሁዳ፡ልጆች፡ዳንኤልና፡ዐናንያ ፡ሚሳኤልና ፡ዐዛርያ ፡ነበሩ።
7የጃን፡ደረባዎቹም፡አለቃ፡ስም፡አወጣላቸው፤ዳንኤልን፡ብልጣሶር ፥ዐናንያንም፡ሲድራቅ ፥ሚሳኤልንም፡ ሚሳቅ፥ዐዛርያንም፡ዐብደናጎ፡ብሎ፡ጠራቸው።
8ዳንኤልም፡በንጉሡ፡መብልና፡በሚጠጣው፡ጠጅ፡እንዳይረክስ፡በልቡ፡ዐሰበ፤እንዳይረክስም፡የጃን፡ ደረባዎቹን፡አለቃ፡ለመነ።
9እግዚአብሔርም፡በጃን፡ደረባዎቹ፡አለቃ፡ፊት፡ለዳንኤል፡ሞገስንና፡ምሕረትን፡ሰጠው።
10የጃን፡ደረባዎቹም፡አለቃ፡ዳንኤልን፦መብሉንና፡መጠጡን፡ያዘዘላችኹን፡ጌታዬን፡ንጉሡን፡ እፈራለኹ፤በዕድሜ፡እንደናንተ፡ካሉ፡ብላቴናዎች፡ይልቅ፡ፊታችኹ፡ከስቶ፡ያየ፡እንደ፡ኾነ፥ከንጉሡ፡ዘንድ፡ በራሴ፡ታስፈርዱብኛላችኹ፡አለው።
11ዳንኤልም፡የጃንደርባዎቹ፡አለቃ፡በዳንኤልና፡በዐናንያ፡በሚሳኤልና፡በዐዛርያ፡ላይ፡የሾመውን፡ሜልዳርን።
12እኛን፡ባሪያዎችኽን፡ዐሥር፡ቀን፡ያኽል፡ትፈትነን፡ዘንድ፥እለምንኻለኹ፤የምንበላውንም፡ጥራጥሬ፡ የምንጠጣውንም፡ውሃ፡ይስጡን፤
13ከዚያም፡በዃላ፡የእኛን፡ፊትና፡ከንጉሡ፡መብል፡የሚበሉትን፡የብላቴናዎችን፡ፊት፡ ተመልከት፤እንዳየኸውም፡ዅሉ፡ከባሪያዎችኽ፡ጋራ፡የወደድኸውን፡አድርግ፡አለው።
14ይህንም፡ነገራቸውን፡ሰምቶ፡ዐሥር፡ቀን፡ፈተናቸው።
15ከዐሥር፡ቀንም፡በዃላ፡ከንጉሡ፡መብል፡ከበሉ፡ብላቴናዎች፡ዅሉ፡ይልቅ፡ፊታቸው፡አምሮ፡ሥጋቸውም፡ ወፍሮ፡ታየ። 262ዕብ.፥ሐናንያህ፡(ምሕረተ፡እግዚአብሔር)። 263 ዕብ.፥ሚሻኤል፡(ማን፡እግዚአብሔር)። 264ዕብ.፥ዐዛርያ፡(እግዚአብሔር፡የሚረዳው)። 265 ዕብ.፥ብልጥሻጻ፟ር። 266 ዕብ.፥ሻድራክ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
16ሜልዳርም፡መብላቸውንና፡የሚጠጡትን፡ጠጅ፡አስቀርቶ፡ጥራጥሬውን፡ሰጣቸው።
17ለእነዚህም፡ለአራቱ፡ብላቴናዎች፡እግዚአብሔር፡በትምህርትና፡በጥበብ፡ዅሉ፡ዕውቀትንና፡ማስተዋልን፡ ሰጣቸው፤ዳንኤልም፡በራእይና፡በሕልም፡ዅሉ፡አስተዋይ፡ነበረ።
18እነርሱም፡ይገቡ፡ዘንድ፥ንጉሡ፡ያዘዘው፡ቀን፡በተፈጸመ፡ጊዜ፥የጃን፡ደረባዎቹ፡አለቃ፡ወደ፡ ናቡከደነጾር፡ዘንድ፡አገባቸው።
19ንጉሡም፡በተነጋገራቸው፡ጊዜ፡ከብላቴናዎቹ፡ዅሉ፡እንደ፡ዳንኤልና፡እንደ፡ዐናንያ፡እንደ፡ሚሳኤልና፡ እንደ፡ዐዛርያ፡ያለ፡አልተገኘም፤በንጉሡም፡ፊት፡ቆሙ።
20ንጉሡም፡በጠየቃቸው፡በጥበብና፡በማስተዋል፡ነገር፡ዅሉ፡በግዛቱ፡ዅሉ፡ከሚኖሩ፡የሕልም፡ ተርጓሚዎችና፡አስማተኛዎች፡ዅሉ፡እነርሱ፡ዐሥር፡እጅ፡የበለጡ፡ኾነው፡አገኘባቸው።
21ዳንኤልም፡እስከንጉሡ፡እስከቂሮስ፡መዠመሪያ፡ዓመት፡ተቀመጠ።