1ናቡከደነጾርም፡በነገሠ፡በኹለተኛው፡ዓመት፡ናቡከደነጾር፡ሕልም፡ዐለመ፤መንፈሱም፡ታወከ፥እንቅልፉም፡ ከርሱ፡ራቀ።
2ለንጉሡም፡ሕልሙን፡እንዲነግሩት፡ንጉሡ፡የሕልም፡ተርጓሚዎቹንና፡አስማተኛዎቹን፡መተተኛዎቹንና፡ ከለዳውያኑንም፡ይጠሩ፡ዘንድ፥አዘዘ፤እነርሱም፡ገብተው፡በንጉሡ፡ፊት፡ቆሙ።
3ንጉሡም፦ሕልም፡ዐልሜያለኹ፥ሕልሙንም፡ለማወቅ፡መንፈሴ፡ታውኳል፡አላቸው።
4ከለዳውያኑም፡ንጉሡን፡በሶርያ፡ቋንቋ፦ንጉሥ፡ሆይ፥ሺሕ፡ዓመት፡ንገሥ፤ለባሪያዎችኽ፡ሕልምኽን፡ ንገር፥እኛም፡ፍቺውን፡እናሳይኻለን፡ብለው፡ተናገሩት።
5ንጉሡም፡መለሰ፡ከለዳውያኑንም፦ነገሩ፡ከእኔ፡ዘንድ፡ርቋል፤ሕልሙንና፡ፍቺውን፡ ባታስታውቁኝ፥ትቈረጣላችኹ፡ቤቶቻችኹም፡የጕድፍ፡መጣያ፡ይደረጋሉ።
6ሕልሙንና፡ፍቺውን፡ግን፡ብታሳዩ፥ከእኔ፡ዘንድ፡ስጦታና፡ዋጋ፡ብዙ፡ክብርም፡ትቀበላላችኹ፤ስለዚህም፡ ሕልሙንና፡ፍቺውን፡አሳዩኝ፡አላቸው።
7ኹለተኛም፡ጊዜ፡መልሰው፦ንጉሡ፡ለባሪያዎቹ፡ሕልሙን፡ይንገር፥እኛም፡ፍቺውን፡እናሳያለን፡አሉት።
8ንጉሡ፡መልሶ፦ነገሩ፡ከእኔ፡ዘንድ፡እንደ፡ራቀ፡ታውቃላችኹና፡ጊዜውን፡እንድታስረዝሙ፡እኔ፡ ዐውቃለኹ።
9ሕልሙንም፡ባታስታውቁኝ፡አንድ፡ፍርድ፡አለባችኹ፤ጊዜውን፡ለማሳለፍ፡የሐሰትንና፡የተንኰልን፡ቃል፡ ልትነግሩኝ፡አዘጋጅታችዃል፤ስለዚህ፥ሕልሙን፡ንገሩኝ፥ፍቺውንም፡ማሳየት፡እንድትችሉ፡ዐውቃለኹ፡አለ።
10ከለዳውያኑም፡በንጉሡ፡ፊት፡መልሰው፦የንጉሡን፡ነገር፡ያሳይ፡ዘንድ፡የሚችል፡ሰው፡በምድር፡ላይ፡ የለም፤ከነገሥታትም፡ታላቅና፡ኀይለኛ፡የኾነ፡እንደዚህ፡ያለ፡ነገር፡የሕልም፡ተርጓሚንና፡አስማተኛን፡ ከለዳዊንም፡አልጠየቀም።
11ንጉሡም፡የሚጠይቀው፡ነገር፡የቸገረ፡ነው፤መኖሪያቸው፡ከሰው፡ጋራ፡ካልኾነ፡ከአማልክት፡በቀር፡ በንጉሡ፡ፊት፡የሚያሳየው፡ማንም፡የለም፡አሉ።
12ስለዚህም፡ንጉሡ፡ተበሳጨ፡እጅግም፡ተቈጣ፥የባቢሎንንም፡ጠቢባን፡ዅሉ፡ያጠፉ፡ዘንድ፡አዘዘ።
13ትእዛዝም፡ወጣ፥ጠቢባንንም፡ይገድሉ፡ዘንድ፡ዠመሩ፤ዳንኤልንና፡ባልንጀራዎቹንም፡ይገድሉ፡ዘንድ፡ ፈለጓቸው።
14የዚያን፡ጊዜም፡ዳንኤል፡የባቢሎንን፡ጠቢባን፡ይገድል፡ዘንድ፡የወጣውን፡የንጉሡን፡የዘበኛዎቹ፡አለቃ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org አርዮክን፡በፈሊጥና፡በማስተዋል፡ተናገረው፤
15ለንጉሡም፡አለቃ፡ለአርዮክ፡መልሶ፦የንጉሡ፡ትእዛዝ፡ስለ፡ምን፡ቸኰለ፧አለው።አርዮክም፡ነገሩን፡ ለዳንኤል፡አስታወቀው።
16ዳንኤልም፡ገብቶ፡ፍቺውን፡ለንጉሡ፡የሚያስታውቅበት፡ጊዜ፡ይሰጠው፡ዘንድ፥ንጉሡን፡ለመነ።
18የዚያን፡ጊዜም፡ዳንኤል፡ወደ፡ቤቱ፡ኼደ።ዳንኤልም፡ባልንጀራዎቹም፡ከቀሩት፡ከባቢሎን፡ጠቢባን፡ ጋራ፡እንዳይሞቱ፡ስለዚህ፡ምስጢር፡ምሕረትን፡ከሰማይ፡አምላክ፡ይለምኑ፡ዘንድ፥ነገሩን፡ለባልንጀራዎቹ፡ ለዐናንያና፡ለሚሳኤል፡ለዐዛርያ፡አስታወቃቸው።
19የዚያን፡ጊዜም፡ምስጢሩ፡በሌሊት፡ራእይ፡ለዳንኤል፡ተገለጠለት፤ዳንኤልም፡የሰማይን፡አምላክ፡አመሰገነ።
20ዳንኤልም፡ተናገረ፡እንዲህም፡አለ፦ጥበብና፡ኀይል፡ለርሱ፡ነውና፥የእግዚአብሔር፡ስም፡ከዘለዓለም፡ እስከ፡ዘለዓለም፡ይባረክ፤
21ጊዜያትንና፡ዘመናትን፡ይለውጣል፤ነገሥታትን፡ያፈልሳል፥ነገሥታትንም፡ያስነሣል፤ጥበብን፡ለጠቢባን፡ ዕውቀትንም፡ለአስተዋዮች፡ይሰጣል።
22የጠለቀውንና፡የተሰወረውን፡ይገልጣል፤በጨለማ፡ያለውን፡ያውቃል፥ብርሃንም፡ከርሱ፡ጋራ፡ነው።
23ጥበብንና፡ኀይልን፡የሰጠኸኝ፥እኛም፡የለመ፟ን፟ኽን፡ነገር፡አኹን፡ያስታወቅኸኝ፥አንተ፡የአባቶቼ፡አምላክ፡ ሆይ፥የንጉሡን፡ነገር፡አስታውቀኸኛልና፥እገዛልኻለኹ፡አመሰግንኽማለኹ።
24ከዚህም፡በዃላ፡ዳንኤል፡ንጉሡ፡የባቢሎንን፡ጠቢባን፡ያጠፋ፡ዘንድ፡ወዳዘዘው፥ወደ፡አርዮክ፡ ገባ፤በገባም፡ጊዜ፦የባቢሎንን፡ጠቢባን፡አታጥፋ፤ወደ፡ንጉሡ፡አስገባኝ፥እኔም፡ፍቺውን፡ለንጉሡ፡ አሳያለኹ፡አለው።
25የዚያን፡ጊዜም፡አርዮክ፡ዳንኤልን፡ፈጥኖ፡ወደ፡ንጉሡ፡አስገባውና፦ከይሁዳ፡ምርኮኛዎች፡ያለውን፡ ለንጉሡ፡ፍቺውን፡የሚያስታውቀውን፡ሰው፡አግኝቻለኹ፡አለው።
26ንጉሡም፡መለሰ፡ብልጣሶርም፡የሚባለውን፡ዳንኤልን፦ያየኹትን፡ሕልምና፡ፍቺውን፡ታስታውቀኝ፡ዘንድ፡ ትችላለኽን፧አለው።
27ዳንኤልም፡በንጉሡ፡ፊት፡መልሶ፡እንዲህ፡አለ፦ንጉሡ፡የጠየቀውን፡ምስጢር፡ጠቢባንና፡አስማተኛዎች፡ የሕልም፡ተርጓሚዎችና፡ቃላ፟ተኛዎች፡ለንጉሡ፡ያሳዩ፡ዘንድ፡አይችሉም፤
28ነገር፡ግን፥ምስጢር፡የሚገልጥ፡አምላክ፡በሰማይ፡ውስጥ፡አለ፥ርሱም፡በዃለኛው፡ዘመን፡የሚኾነውን፡ ለንጉሡ፡ለናቡከደነጾር፡አስታውቆታል።በዐልጋኽ፡ላይ፡የኾነው፡ሕልምና፡የራስኽ፡ራእይ፡ይህ፡ነው።
29አንተ፥ንጉሥ፡ሆይ፥ከአንተ፡በዃላ፡የሚኾነው፡ምን፡እንደ፡ኾነ፡በዐልጋኽ፡ላይ፡ታስብ፡ ነበር፤ምስጢርንም፡የሚገልጠው፡የሚኾነውን፡ነገር፡አስታውቆኻል።
30ነገር፡ግን፥ይህ፡ምስጢር፡ለእኔ፡መገለጡ፡ፍቺው፡ለንጉሡ፡ይታወቅ፡ዘንድ፥አንተም፡የልብኽን፡ ዐሳብ፡ታውቅ፡ዘንድ፡ነው፡እንጂ፡በዚህ፡ዓለም፡ካሉ፡ሰዎች፡ይልቅ፡በጥበብ፡ስለ፡በለጥኹ፡አይደለም።
31አንተ፥ንጉሥ፡ሆይ፥ታላቅ፡ምስል፡አየኽ፤ይህም፡ምስል፡ታላቅና፡ብልጭልጭታው፡የበዛ፡ ነበረ፥በፊትኽም፡ቆሞ፡ነበር፤መልኩም፡ግሩም፡ነበረ።
32የዚህም፡ምስል፡ራስ፡ጥሩ፡ወርቅ፥ደረቱና፡ክንዶቹም፡ብር፥ሆዱና፡ወገቡም፡ናስ፥
33ጭኖቹም፡ብረት፥እግሮቹም፡እኩሉ፡ብረት፡እኩሉም፡ሸክላ፡ነበረ።
34እጅም፡ሳይነካው፡ድንጋይ፡ከተራራው፡ተፈንቅሎ፡ከብረትና፡ከሸክላ፡የኾነውን፡የምስሉን፡እግሮች፡ ሲመታና፡ሲፈጭ፡አየኽ።
35የዚያን፡ጊዜም፡ብረቱና፡ሸክላው፥ናሱና፡ብሩ፡ወርቁም፡በአንድነት፡ተፈጨ፥በመከርም፡ጊዜ፡ በዐውድማ፡ላይ፡እንዳለ፡እብቅ፡ኾነ፤ነፋስም፡ወሰደው፥ቦታውም፡አልታወቀም፤ምስሉንም፡የመታ፡ድንጋይ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ታላቅ፡ተራራ፡ኾነ፡ምድርንም፡ፈጽሞ፡ሞላ፡
36ሕልሙ፡ይህ፡ነው፤አኹንም፡ፍቺውን፡በንጉሡ፡ፊት፡እንናገራለን።
37አንተ፥ንጉሥ፡ሆይ፥የሰማይ፡አምላክ፡መንግሥትንና፡ኀይልን፥ብርታትንና፡ክብርን፡የሰጠኽ፡የነገሥታት፡ ንጉሥ፡አንተ፡ነኽ።
38በሚቀመጡበትም፡ስፍራ፡ዅሉ፡የሰው፡ልጆችንና፡የምድር፡አራዊትን፡የሰማይ፡ወፎችንም፡በእጅኽ፡ አሳልፎ፡ሰጥቶኻል፥ለዅሉም፡ገዢ፡አድርጎኻል፤አንተ፡የወርቁ፡ራስ፡ነኽ።
39ከአንተም፡በዃላ፡ከአንተ፡የሚያንስ፡ሌላ፡መንግሥት፡ይነሣል፤ከዚያም፡በዃላ፡በምድር፡ዅሉ፡ላይ፡ የሚገዛ፡ሌላ፡ሦስተኛ፡የናስ፡መንግሥት፡ይነሣል።
40አራተኛውም፡መንግሥት፡ዅሉን፡እንደሚቀጠቅጥና፡እንደሚያደቅ፟፡ብረት፡ይበረታል፤እነዚህንም፡ዅሉ፡ እንደሚፈጭ፡ብረት፡ይቀጠቅጣል፡ይፈጭማል።
41እግሮቹና፡ጣቶቹም፡እኩሉ፡ሸክላ፡እኩሉም፡ብረት፡ኾኖ፡እንዳየኽ፥እንዲሁ፡የተከፋፈለ፡መንግሥት፡ ይኾናል፤ብረቱም፡ከሸክላው፡ጋራ፡ተደባልቆ፡እንዳየኹ፥የብረት፡ብርታት፡ለርሱ፡ይኾናል።
42የእግሮቹም፡ጣቶች፡እኩሉ፡ብረት፡እኩሉም፡ሸክላ፡እንደ፡ነበሩ፥እንዲሁ፡መንግሥቱ፡እኩሉ፡ብርቱ፡ እኩሉ፡ደካማ፡ይኾናል።
43ብረቱም፡ከሸክላው፡ጋራ፡ተደባልቆ፡እንዳየኽ፥እንዲሁ፡ከሰው፡ዘር፡ጋራ፡ይደባለቃሉ፤ነገር፡ ግን፥ብረት፡ከሸክላ፡ጋራ፡እንደማይጣበቅ፥እንዲሁ፡ርስ፡በርሳቸው፡አይጣበቁም።
44በእነዚያም፡ነገሥታት፡ዘመን፡የሰማይ፡አምላክ፡ለዘለዓለም፡የማይፈርስ፡መንግሥት፡ያስነሣል፤ለሌላ፡ ሕዝብም፡የማይሰጥ፡መንግሥት፡ይኾናል፤እነዚያንም፡መንግሥታት፡ዅሉ፡ትፈጫቸዋለች፡ ታጠፋቸውማለች፥ለዘለዓለምም፡ትቆማለች።
45ድንጋዩም፡እጅ፡ሳይነካው፡ከተራራ፡ተፈንቅሎ፡ብረቱንና፡ናሱን፡ሸክላውንና፡ብሩን፡ወርቁንም፡ሲፈጨው፡ እንዳየኽ፥እንዲሁ፡ከዚህ፡በዃላ፡የሚኾነውን፡ታላቁ፡አምላክ፡ለንጉሡ፡አስታውቆታል፤ሕልሙም፡እውነተኛ፡ ፍቺውም፡የታመነ፡ነው።
46የዚያን፡ጊዜም፡ንጉሡ፡ናቡከደነጾር፡በግንባሩ፡ተደፍቶ፡ለዳንኤል፡ሰገደለት፥የእኽሉንም፡ቍርባን፡ ዕጣኑንም፡ያቀርቡለት፡ዘንድ፡አዘዘ።
47ንጉሡም፡ዳንኤልን፦ይህን፡ምስጢር፡ትገልጥ፡ዘንድ፡ተችሎኻልና፥በእውነት፡አምላካችኹ፡የአማልክት፡ አምላክ፥የነገሥታትም፡ጌታ፥ምስጢርም፡ገላጭ፡ነው፡ብሎ፡ተናገረው።
48ንጉሡም፡ዳንኤልን፡ከፍ፡ከፍ፡አደርገው፥ብዙም፡ታላቅ፡ስጦታ፡ሰጠው፥በባቢሎንም፡አውራጃ፡ዅሉ፡ ላይ፡ሾመው፥በባቢሎንም፡ጠቢባን፡ዅሉ፡ላይ፡ዋነኛ፡አለቃ፡አደረገው።
49ዳንኤልም፡ንጉሡን፡ለመነ፥ርሱም፡ሲድራቅንና፡ሚሳቅን፡ዐብደናጎንም፡በባቢሎን፡አውራጃ፡ሥራ፡ላይ፡ ሾማቸው፤ዳንኤል፡ግን፡በንጉሡ፡በር፡ነበረ።