Skip to content
← Daniel

Chapter 3 · Amharic

Daniel

1ንጉሡ፡ናቡከደነጾር፡ቁመቱ፡ስድሳ፡ክንድ፡ወርዱም፡ስድስት፡ክንድ፡የኾነውን፡የወርቁን፡ምስል፡ አሠራ፤በባቢሎንም፡አውራጃ፡በዱራ፡ሜዳ፡አቆመው።

2ንጉሡም፡ናቡከደነጾር፡መኳንንትንና፡ሹማምቶችን፥አዛዦችንና፡ዐዛውንቶችን፥በጅሮንዶችንና፡ አማካሪዎችን፥መጋቢዎችንም፥አውራጃ፡ገዢዎችንም፡ዅሉ፡ይሰበስቡ፡ዘንድ፥ንጉሡም፡ናቡከደነጾር፡ላቆመው፡ ምስል፡ምረቃ፡ይመጡ፡ዘንድ፡ላከ።

3በዚያን፡ጊዜም፡መኳንንቱና፡ሹማምቶቹ፥አዛዦቹና፡ዐዛውንቶቹ፥በጅሮንዶቹና፡አማካሪዎቹ፥መጋቢዎቹና፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org አውራጃ፡ገዢዎቹ፡ዅሉ፡ንጉሡ፡ናቡከደነጾር፡ላቆመው፡ምስል፡ምረቃ፡ተሰበሰቡ፤ናቡከደነጾርም፡ባቆመው፡ ምስል፡ፊት፡ቆሙ።

4ዐዋጅ፡ነጋሪውም፡እየጮኸ፡እንዲህ፡አለ፦ወገኖችና፡አሕዛብ፡በልዩ፡ልዩ፡ቋንቋም፡የምትናገሩ፡ሆይ፥

5የመለከትንና፡የእንቢልታን፥የመሰንቆንና፡የክራርን፥የበገናንና፡የዋሽንትን፥የዘፈንንም፡ዅሉ፡ድምፅ፡ በሰማችኹ፡ጊዜ፥ተደፍታችኹ፡ንጉሡ፡ናቡከደነጾር፡ላቆመው፡ለወርቁ፡ምስል፡እንድትሰግዱ፡ታዛ፟ችዃል።

6ተደፍቶም፡የማይሰግድ፡በዚያን፡ጊዜ፡በሚነድ፟፡እሳት፡እቶን፡ውስጥ፡ይጣላል።

7ስለዚህ፥በዚያን፡ጊዜ፡አሕዛብ፡ዅሉ፡የመለከቱንና፡የእንቢልታውን፥የመሰንቆውንና፡የክራሩን፥የበገናውንና፡ የዘፈኑንም፡ዅሉ፡ድምፅ፡በሰሙ፡ጊዜ፥ወገኖችና፡አሕዛብ፡በልዩ፡ልዩ፡ቋንቋም፡የተናገሩ፡ዅሉ፡ ተደፉ፥ንጉሡም፡ናቡከደነጾር፡ላቆመው፡ለወርቅ፡ምስል፡ሰገዱ።

8በዚያን፡ጊዜም፡ከለዳውያን፡ቀርበው፡አይሁድን፡ከሰሱ።

9ለንጉሡም፡ለናቡከደነጾር፡ተናገሩ፡እንዲህም፡አሉ።ንጉሥ፡ሆይ፥ሺሕ፡ዓመት፡ንገሥ።

10አንተ፥ንጉሥ፡ሆይ፦የመለከትንና፡የእንቢልታን፥የመሰንቆንና፡የክራርን፥የበገናንና፡ የዋሽንትን፥የዘፈንንም፡ዅሉ፡ድምፅ፡የሚሰማ፡ሰው፡ዅሉ፡ተደፍቶ፡ለወርቁ፡ምስል፡ይስገድ፤

11ተደፍቶም፡የማይሰግድ፡በሚነድ፟፡እሳት፡እቶን፡ውስጥ፡ይጣላል፡ብለኽ፡አዘዝኽ።

12በባቢሎን፡አውራጃ፡ሥራ፡ላይ፡የሾምኻቸው፡ሲድራቅና፡ሚሳቅ፡ዐብደናጎም፡የሚባሉ፡አይሁድ፡ አሉ፤ንጉሥ፡ሆይ፥እነዚህ፡ሰዎች፡ትእዛዝኽን፡እንቢ፡ብለዋል፤አማልክትኽን፡አያመልኩም፥ላቆምኸውም፡ ለወርቁ፡ምስል፡አይሰግዱም።

13ናቡከደነጾርም፡በብስጭትና፡በቍጣ፡ሲድራቅንና፡ሚሳቅን፡ዐብደናጎንም፡ያመጡ፡ዘንድ፡አዘዘ፤እነዚህንም፡ ሰዎች፡ወደንጉሡ፡ፊት፡አመጧቸው።

14ናቡከደነጾርም፦ሲድራቅና፡ሚሳቅ፡ዐብደናጎም፡ሆይ፥አምላኬን፡አለማምለካችኹ፥ላቆምኹትም፡ለወርቁ፡ ምስል፡አለመስገዳችኹ፡እውነት፡ነውን፧

15አኹንም፡የመለከቱንና፡የእንቢልታውን፡የመሰንቆውንና፡የክራሩን፡የበገናውንና፡የዋሽንቱን፡የዘፈኑንም፡ ዅሉ፡ድምፅ፡በሰማችኹ፡ጊዜ፡ተደፍታችኹ፡ላሠራኹት፡ምስል፡ብትሰግዱ፡መልካም፡ነው፤ባትሰግዱ፡ግን፡ በዚያ፡ጊዜ፡በሚነድ፟፡እሳት፡እቶን፡ውስጥ፡ትጣላላችኹ፤ከእጄስ፡የሚያድናችኹ፡አምላክ፡ማን፡ነው፧ብሎ፡ ተናገራቸው።

16ሲድራቅና፡ሚሳቅ፡ዐብደናጎም፡መለሱ፡ንጉሡንም፦ናቡከደነጾር፡ሆይ፥በዚህ፡ነገር፡እንመልስልኽ፡ዘንድ፡ አስፈላጊያችን፡አይደለም።

17የምናመልከው፡አምላካችን፡ከሚነደ፟ው፡ከእሳቱ፡እቶን፡ያድነን፡ዘንድ፡ይችላል፤ከእጅኽም፡ ያድነናል፥ንጉሥ፡ሆይ!

18ነገር፡ግን፥ንጉሥ፡ሆይ፥ርሱ፡ባያድነን፥አማልክትኽን፡እንዳናመልክ፡ላቆምኸውም፡ለወርቁ፡ምስል፡ እንዳንሰግድለት፡ዕወቅ፡አሉት።

19የዚያን፡ጊዜም፡ናቡከደነጾር፡በሲድራቅና፡በሚሳቅ፡በዐብደናጎም፡ላይ፡ቍጣ፡ሞላበት፥የፊቱም፡መልክ፡ ተለወጠባቸው፤ርሱም፡ተናገረ፥የእቶንም፡እሳት፡ይነድ፟፡ከነበረው፡ይልቅ፡ሰባት፡ዕጥፍ፡አድርገው፡ እንዲያነዱ፟ት፡አዘዘ።

20ሲድራቅንና፡ሚሳቅንም፡ዐብደናጎንም፡ያስሩ፡ዘንድ፥ወደሚነድ፟ም፡ወደእቶን፡እሳት፡ይጥሏቸው፡ ዘንድ፥በሰራዊቱ፡ውስጥ፡ከነበሩት፡ኀያላን፡አዘዘ።

21የዚያን፡ጊዜም፡እነዚህ፡ሰዎች፡ከሰናፊላቸውና፡ከቀሚሳቸው፡ከመጐናጸፊያቸውም፡ከቀረውም፡ልብሳቸው፡ ጋራ፡ታስረው፡በሚነድ፟፡በእቶን፡እሳት፡ውስጥ፡ተጣሉ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

22የንጉሡም፡ትእዛዝ፡አስቸኳይ፡ስለ፡ኾነ፡የእቶኑም፡እሳት፡እጅግ፡ስለሚነድ፟፥ሲድራቅንና፡ሚሳቅን፡ ዐብደናጎንም፡የጣሏቸውን፡ሰዎች፡የእሳቱ፡ወላፈን፡ገደላቸው።

23እነዚህም፡ሦስቱ፡ሰዎች፡ሲድራቅና፡ሚሳቅ፡ዐብደናጎም፡ታስረው፡በሚነደ፟ው፡በእቶኑ፡እሳት፡ውስጥ፡ ወደቁ።

24የዚያን፡ጊዜም፡ንጉሡ፡ናቡከደነጾር፡ተደነቀ፡ፈጥኖም፡ተነሣ፤አማካሪዎቹንም፦ሦስት፡ሰዎች፡አስረን፡ በእሳት፡ውስጥ፡ጥለን፡አልነበረምን፧ብሎ፡ተናገራቸው።እነርሱም፦ንጉሥ፡ሆይ፥እውነት፡ነው፡ብለው፡ ለንጉሡ፡መለሱለት።

25ርሱም፦እንሆ፥እኔ፡የተፈቱ፡በእሳቱም፡መካከል፡የሚመላለሱ፡አራት፡ሰዎች፡አያለኹ፤ምንም፡ አላቈሰላቸውም፤የአራተኛውም፡መልክ፡የአማልክትን፡ልጅ፡ይመስላል፡ብሎ፡መለሰ።

26የዚያን፡ጊዜም፡ናቡከደነጾር፡ወደሚነደ፟ው፡ወደእሳቱ፡እቶን፡በር፡ቀርቦ፦እናንተ፡የልዑል፡አምላክ፡ ባሪያዎች፥ሲድራቅና፡ሚሳቅ፡ዐብደናጎም፥ኑ፡ውጡ፡ብሎ፡ተናገራቸው።ሲድራቅና፡ሚሳቅም፡ዐብደናጎም፡ ከእሳቱ፡መካከል፡ወጡ።

27መሳፍንቱና፡ሹማምቶቹም፡አዛዦቹና፡የንጉሡ፡አማካሪዎች፡ተሰብስበው፡እሳቱ፡በእነዚያ፡ሰዎች፡አካል፡ ላይ፡ኀይል፡እንዳልነበረው፥የራሳቸውም፡ጠጕር፡እንዳልተቃጠለች፥ሰናፊላቸውም፡እንዳልተለወጠ፥የእሳቱም፡ ሽታ፡እንዳልደረሰባቸው፡አዩ።

28ናቡከደነጾርም፡መልሶ፦መልአኩን፡የላከ፥ከአምላካቸውም፡በቀር፡ማንም፡አምላክ፡እንዳያመልኩ፡ ለርሱም፡እንዳይሰግዱ፡ሰውነታቸውን፡አሳልፈው፡የሰጡትን፡የንጉሡንም፡ቃል፡የተላለፉትን፡በርሱ፡የታመኑትን፡ ባሪያዎቹን፡ያዳነ፥የሲድራቅና፡የሚሳቅ፡የዐብደናጎም፡አምላክ፡ይባረክ።

29እኔም፡እንደዚህ፡የሚያድን፡ሌላ፡አምላክ፡የለምና፡በሲድራቅና፡በሚሳቅ፡በዐብደናጎም፡አምላክ፡ላይ፡ የስድብን፡ነገር፡የሚናገር፡ወገንና፡ሕዝብ፡በልዩ፡ልዩም፡ቋንቋ፡የሚናገሩ፡ይቈረጣሉ፥ቤቶቻቸውም፡የጕድፍ፡ መጣያ፡ይደረጋሉ፡ብዬ፡አዝዣለኹ፡አለ።

30የዚያን፡ጊዜም፡ንጉሡ፡ሲድራቅንና፡ሚሳቅን፡ዐብደናጎንም፡በባቢሎን፡አውራጃ፡ውስጥ፡ከፍ፡ከፍ፡ አደረጋቸው።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source