1በዚያም፡ዘመን፡ስለሕዝብኽ፡ልጆች፡የሚቆመው፡ታላቁ፡አለቃ፡ሚካኤል፡ይነሣል፤ሕዝብም፡ከኾነ፡ ዠምሮ፡እስከዚያ፡ዘመን፡ድረስ፡እንደ፡ርሱ፡ያለ፡ያልኾነ፡የመከራ፡ዘመን፡ይኾናል፤በዚያም፡ዘመን፡ በመጽሐፉ፡ተጽፎ፡የተገኘው፡ሕዝብኽ፡ዅሉ፡እያንዳንዱ፡ይድናል።
2በምድርም፡ትቢያ፡ውስጥ፡ካንቀላፉቱ፡ብዙዎች፡ይነቃሉ፤እኩሌቶቹ፡ወደዘለዓለም፡ሕይወት፥እኩሌቶቹም፡ ወደ፡ዕፍረትና፡ወደዘለዓለም፡ጕስቍልና።
3ጥበበኛዎቹም፡እንደሰማይ፡ጸዳል፥ብዙ፡ሰዎችንም፡ወደ፡ጽድቅ፡የሚመልሱ፡እንደ፡ከዋክብት፡ለዘለዓለም፡ ይደምቃሉ።
4ዳንኤል፡ሆይ፥አንተ፡ግን፡እስከ፡ፍጻሜ፡ዘመን፡ድረስ፡ቃሉን፡ዝጋ፥መጽሐፉንም፡ዐትም፤ብዙ፡ሰዎች፡ ይመረምራሉ፥ዕውቀትም፡ይበዛል።
5እኔም፡ዳንኤል፡አየኹ፤እንሆም፥ኹለት፡ሌላዎች፡ቆመው፡ነበር፥አንዱ፡በዚህ፡በወንዙ፡ዳር፥ሌላውም፡ በዚያ፡በወንዙ፡ዳር።
6አንዱም፡ከወንዙ፡ውሃ፡በላይ፡የነበረውን፡በፍታም፡የለበሰውን፦የዚህ፡ድንቅ፡ፍጻሜ፡እስከ፡መቼ፡ ነው፧አለው።
7ከወንዙም፡ውሃ፡በላይ፡የነበረው፡በፍታም፡የለበሰው፡ሰው፡ቀኝና፡ግራ፡እጁን፡ወደ፡ሰማይ፡ አንሥቶ፦ለዘመንና፡ለዘመናት፡ለዘመንም፡እኩሌታ፡ነው፤የተቀደሰውም፡ሕዝብ፡ኀይል፡መበተን፡በተጨረሰ፡ ጊዜ፡ይህ፡ዅሉ፡ይፈጸማል፡ብሎ፡ለዘለዓለም፡ሕያው፡ኾኖ፡በሚኖረው፡ሲምል፡ሰማኹ።
8ሰማኹም፥ነገር፡ግን፥አላስተዋልኹም፤የዚያን፡ጊዜም፦ጌታዬ፡ሆይ፥የዚህ፡ዅሉ፡ፍጻሜ፡ምንድር፡ ነው፧አልኹ።
9ርሱም፡እንዲህ፡አለኝ፦ዳንኤል፡ሆይ፥ቃሉ፡እስከ፡ፍጻሜ፡ዘመን፡ድረስ፡የተዘጋና፡የታተመ፡ ነውና፥ኺድ፤
10ብዙ፡ሰዎች፡ሰውነታቸውን፡ያጠራሉ፥ያነጡማል፥ይነጥሩማል፤ክፉዎች፡ግን፡ክፋትን፡ ያደርጋሉ፤ክፉዎችም፡ዅሉ፡አያስተውሉም፥ጥበበኛዎች፡ግን፡ያስተውላሉ።
11የዘወትሩም፡መሥዋዕት፡ከቀረ፡ዠምሮ፥የጥፋትም፡ርኵሰት፡ከቆመ፡ዠምሮ፡ሺሕ፡ኹለት፡መቶ፡ዘጠና፡ ቀን፡ይኾናል።
12የሚታገሥ፥እስከ፡ሺሕ፡ሦስት፡መቶ፡ሠላሳ፡ዐምስት፡ቀንም፡የሚደርስ፡ምስጉን፡ነው።
13አንተ፡ግን፡እስከ፡ፍጻሜው፡ድረስ፡ኺድ፤አንተም፡ታርፋለኽ፥በቀኑም፡መጨረሻ፡በዕጣ፡ክፍልኽ፡ ትቆማለኽ፨ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org