Skip to content
← Daniel

Chapter 11 · Amharic

Daniel

1እኔም፡በሜዶናዊ፡በዳርዮስ፡መዠመሪያ፡ዓመት፡አጸናውና፡አበረታው፡ዘንድ፡ቆሜ፡ነበር።

2አኹንም፡እውነትን፡አሳይኻለኹ።እንሆ፥ሦስት፡ነገሥታት፡ደግሞ፡በፋርስ፡ይነሣሉ፤አራተኛውም፡ከዅሉ፡ ይልቅ፡እጅግ፡ባለጠጋ፡ይኾናል፤በባለጠግነቱም፡በበረታ፡ጊዜ፡በግሪክ፡መንግሥት፡ላይ፡ዅሉን፡ያስነሣል።

3ኀያልም፡ንጉሥ፡ይነሣል፥በትልቅ፡አገዛዝም፡ይገዛል፥እንደ፡ፈቃዱም፡ያደርጋል።

4ርሱም፡በተነሣ፡ጊዜ፡መንግሥቱ፡ይሰበራል፤እስከ፡አራቱ፡የሰማይ፡ነፋሳት፡ይከፋፈላል።ለዘሩ፡ግን፡ አይከፋፈልም፥እንደ፡ገዛበትም፡አገዛዝ፡አይኾንም፤መንግሥቱ፡ይነቀላልና፤ከነዚህም፡ለሌላዎች፡ይኾናልና።

5የደቡብም፡ንጉሥ፡ከአለቃዎቹም፡አንዱ፡ይበረታሉ፤ርሱም፡ይበረታበታል፡ይሠለጥንማል፤ግዛቱም፡ታላቅ፡ ግዛት፡ይኾናል።

6ከዘመናትም፡በዃላ፡ይጋጠማሉ፤የደቡብም፡ንጉሥ፡ሴት፡ልጅ፡ቃል፡ኪዳን፡ለማድረግ፡ወደሰሜን፡ንጉሥ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ትመጣለች፤የክንዷ፡ኀይል፡ግን፡አይጸናም፥ርሱና፡ክንዱም፡አይጸናም፤ርሷና፡ርሷን፡ያመጡ፡የወለዳትም፡ በዚያም፡ዘመን፡ያጸናት፡ዐልፈው፡ይሰጣሉ።

7ነገር፡ግን፥ከሥሯ፡ቍጥቋጥ፡አንዱ፡በስፍራው፡ይነሣል፤ወደ፡ሰራዊቱም፡ይመጣል፥ወደሰሜንም፡ንጉሥ፡ ዐምባ፡ይገባል፥በላያቸውም፡ያደርጋል፥ያሸንፍማል።

8አማልክታቸውንና፡ቀልጠው፡የተሠሩትን፡ምስሎቻቸውን፡ከብርና፡ከወርቅም፡የተሠሩትን፡የከበሩትን፡ ዕቃዎች፡ወደ፡ግብጽ፡ይማርካል፤እስከ፡ጥቂትም፡ዓመት፡ድረስ፡ከሰሜን፡ንጉሥ፡ጋራ፡ሳይዋጋ፡ይቀመጣል።

9ይህም፡ወደደቡብ፡ንጉሥ፡መንግሥት፡ይገባል፥ነገር፡ግን፥ወደገዛ፡ምድሩ፡ይመለሳል።

10ልጆቹም፡ይዋጋሉ፤ብዙ፡ሰራዊትንና፡ሕዝብን፡ይሰበስባል፤ርሱም፡ ይመጣል፥ይጐርፍማል፥ያልፍማል፤ተመልሶም፡እስከ፡ዐምባው፡ድረስ፡ይዋጋል።

11የደቡብም፡ንጉሥ፡ይቈጣል፡ወጥቶም፡ከሰሜን፡ንጉሥ፡ጋራ፡ይዋጋል፤ብዙ፡ሕዝብንም፡ለሰልፍ፡ ያቆማል፥ሕዝቡም፡ዐልፎ፡በእጁ፡ይሰጣል።

12ሕዝቡም፡በተወሰደ፡ጊዜ፡ልቡ፡ይታበያል፤አእላፋትንም፡ይጥላል፥ነገር፡ግን፥አያሸንፍም።

13የሰሜንም፡ንጉሥ፡ይመለሳል፥ከቀደመውም፡የበለጠ፡ብዙ፡ሕዝብ፡ለሰልፍ፡ያቆማል፤በዘመናትና፡ በዓመታትም፡ፍጻሜ፡ከታላቅ፡ሰራዊትና፡ከብዙ፡ሀብት፡ጋራ፡ይመጣል።

14በዚያም፡ዘመን፡ብዙ፡ሰዎች፡በደቡብ፡ንጉሥ፡ላይ፡ይነሣሉ፤ከሕዝብኽም፡መካከል፡የዐመፅ፡ልጆች፡ ራእዩን፡ያጸኑ፡ዘንድ፡ይነሣሉ፤ነገር፡ግን፥ይወድቃሉ።

15የሰሜንም፡ንጉሥ፡ይመጣል፥ዐፈርንም፡ይደለድላል፥የተመሸገችንም፡ከተማ፡ይወስዳል፤የደቡብም፡ ሰራዊት፡የተመረጡትም፡ሕዝቡ፡አይቆሙም፤ለመቋቋምም፡ኀይል፡የላቸውም።

16በርሱም፡ላይ፡የሚመጣው፡ግን፡እንደ፡ፈቃዱ፡ያደርጋል፥በፊቱም፡የሚቆም፡የለም፤በመልካሚቱም፡ ምድር፡ይቆማል፥በእጁም፡ውስጥ፡ጥፋት፡ይኾናል።

17ከመንግሥቱም፡ዅሉ፡ኀይል፡ጋራ፡ይመጣ፡ዘንድ፡ፊቱን፡ያቀናል፥ከርሱም፡ጋራ፡አንድነትን፡ ያደርጋል፤ያረክሳትም፡ዘንድ፡ሴትን፡ልጅ፡ይሰጠዋል፤ርሷም፡አትጸናም፡ለርሱም፡አትኾንም።

18ከዚህም፡በዃላ፡ፊቱን፡ወደ፡ደሴቶች፡ይመልሳል፥ብዙዎችንም፡ይወስዳል፤አንድ፡አለቃ፡ግን፡ስድቡን፡ ይሽራል፥ስድቡንም፡በራሱ፡ላይ፡ይመልሳል።

19ፊቱንም፡ወደገዛ፡ምድሩ፡ዐምባዎች፡ይመልሳል፤ተሰናክሎም፡ይወድቃል፥አይገኝምም።

20የዚያን፡ጊዜም፡በመንግሥቱ፡ክብር፡መካከል፡አስገባሪውን፡የሚያሳልፍ፡በስፍራው፡ይነሣል፤ነገር፡ ግን፥በቍጣው፡ሳይኾን፡በሰልፍም፡ሳይኾን፡በጥቂት፡ቀን፡ይሰበራል።

21በርሱም፡ስፍራ፡የተጠቃ፡ሰው፡ይነሣል፡የመንግሥቱንም፡ክብር፡አይሰጡትም፤በቀስታ፡መጥቶ፡ መንግሥቱን፡በማታለል፡ይገዛል።

22የሚጐርፍም፡ሰራዊት፡ከፊቱ፡ይወሰዳል፥ርሱና፡የቃል፡ኪዳኑ፡አለቃ፡ይሰበራሉ።

23ከርሱም፡ጋራ፡ከተወዳጀ፡በዃላ፥በተንኰል፡ያደርጋል፤ከጥቂትም፡ሕዝብ፡ጋራ፡ወጥቶ፡ይበረታል።

24በቀስታ፡ከአገር፡ዅሉ፡ወደለመለመችው፡ክፍል፡ይገባል፤አባቶቹና፡የአባቶቹ፡አባቶች፡ያላደረጉትንም፡ ያደርጋል፤ብዝበዛውንና፡ምርኮውንም፣ሀብቱንም፡በመካከላቸው፡ይበትናል፤በምሽጎችም፡ላይ፡እስከ፡ጊዜው፡ ድረስ፡ዐሳቡን፡ይፈጥራል።

25በታላቅም፡ሰራዊት፡ኾኖ፡ኀይሉንና፡ልቡን፡በደቡብ፡ንጉሥ፡ላይ፡ያስነሣል፤የደቡብም፡ንጉሥ፡በታላቅና፡ በብዙ፡ሰራዊት፡ኾኖ፡በሰልፍ፡ይዋጋል፤ነገር፡ግን፥ዐሳብ፡በርሱ፡ላይ፡ይፈጥራሉና፥አይጸናም።

26መብሉንም፡የሚበሉ፡ሰዎች፡ይሰብሩታል፤ሰራዊቱም፡ይጐርፋል፤ብዙዎችም፡ተገድለው፡ይወድቃሉ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

27እነዚህም፡ኹለት፡ነገሥታት፡ክፋትን፡ያደርጉ፡ዘንድ፡በልባቸው፡ያስባሉ፥ባንድ፡ገበታም፡ተቀምጠው፡ ሐሰት፡ይናገራሉ፤ነገር፡ግን፥ፍጻሜው፡እስከተወሰነው፡ጊዜ፡ነውና፥አይከናወንላቸውም።

28ከብዙም፡ሀብት፡ጋራ፡ወደ፡ምድሩ፡ይመለሳል፥ልቡም፡በተቀደሰ፡ቃል፡ኪዳን፡ላይ፡ ይኾናል፤ፈቃዱንም፡ያደርጋል፥ወደገዛ፡ምድሩም፡ይመለሳል።

29በተወሰነውም፡ጊዜ፡ይመለሳል፥ወደ፡ደቡብም፡ይመጣል፤ነገር፡ግን፥ዃለኛው፡እንደ፡ፊተኛው፡ አይኾንም።

30የኪቲም፡መርከቦች፡ይመጡበታልና፥ስለዚህ፡ዐዝኖ፡ይመለሳል፥በቅዱሱም፡ቃል፡ኪዳን፡ላይ፡ ይቈጣል፥ፈቃዱንም፡ያደርጋል፤ተመልሶም፡ቅዱሱን፡ቃል፡ኪዳን፡የተዉትን፡ሰዎች፡ይመለከታል።

31ከርሱም፡ጋራ፡ሰራዊቶች፡ይቆማሉ፥መቅደሱንም፣ግንቡንም፡ያረክሳሉ፥የዘወትሩንም፡መሥዋዕት፡ ያስቀራሉ፥የጥፋትንም፡ርኵሰት፡ያቆማሉ።

32ቃል፡ኪዳኑን፡የሚበድሉትንም፡በማታለል፡ያስታል፤ነገር፡ግን፥አምላካቸውን፡የሚያውቁ፡ሕዝብ፡ ይበረታሉ፥ያደርጋሉም።

33በሕዝቡም፡መካከል፡ያሉ፡ጥበበኛዎች፡ብዙ፡ሰዎችን፡ያስተምራሉ፤ነገር፡ግን፥በሰይፍና፡በእሳት፡ ነበልባል፡በምርኮና፡በመበዝበዝ፡ብዙ፡ዘመን፡ይወድቃሉ።

34በወደቁም፡ጊዜ፡በጥቂት፡ርዳታ፡ይረ፟ዳ፟ሉ፤ብዙ፡ሰዎችም፡በግብዝነት፡ወደ፡እነርሱ፡ተባብረው፡ ይሰበሰባሉ።

35እስከተወሰነውም፡ዘመን፡ይኾናልና፥ከጥበበኛዎቹ፡ዐያሌዎቹ፡እስከ፡ፍጻሜ፡ዘመን፡ይነጥሩና፡ ይጠሩ፣ይነጡም፡ዘንድ፡ይወድቃሉ።

36ንጉሡም፡እንደ፡ፈቃዱ፡ያደርጋል፤ራሱንም፡ከፍ፡ከፍ፡ያደርጋል፥በአማልክት፡ዅሉ፡ላይ፡ራሱን፡ ታላቅ፡ያደርጋል፥በአማልክትም፡አምላክ፡ላይ፡በትዕቢት፡ይናገራል፤ቍጣም፡እስኪፈጸም፡ድረስ፡ ይከናወንለታል፥የተወሰነው፡ይደረጋልና።

37የአባቶቹንም፡አማልክት፡የሴቶችንም፡ምኞት፡አይመለከትም፤ራሱንም፡በዅሉ፡ላይ፡ታላቅ፡ ያደርጋልና፥አማልክትን፡ዅሉ፡አይመለከትም።

38በእነዚህ፡ፋንታ፡ግን፡የዐምባዎቹን፡አምላክ፡ያከብራል፤አባቶቹም፡ያላወቁትን፡አምላክ፡በወርቅና፡በብር፡ በዕንቍና፡በከበረ፡ነገር፡ያከብረዋል።

39በእንግዳም፡አምላክ፡ርዳታ፡በጽኑ፡ዐምባ፡ላይ፡ያደርጋል፤ለሚያውቁት፡ክብር፡ያበዛላቸዋል፥በብዙም፡ ላይ፡ያስገዛቸዋል፥ምድርንም፡በዋጋ፡ይከፍላል።

40በፍጻሜ፡ዘመንም፡የደቡብ፡ንጉሥ፡ከርሱ፡ጋራ፡ይዋጋል፤የሰሜንም፡ንጉሥ፡ከሠረገላዎችና፡ ከፈረሰኛዎች፡ከብዙም፡መርከቦች፡ጋራ፡እንደ፡ዐውሎ፡ነፋስ፡ይመጣበታል፤ወደ፡አገሮችም፡ ይገባል፥ይጐርፍማል፥ያልፍማል።

41ወደ፡መልካሚቱም፡ምድር፡ይገባል፥ብዙ፡አገሮችም፡ይወድቃሉ፤ነገር፡ግን፥ኤዶምያስና፡ሞዐብ፡ ከዐሞንም፡ልጆች፡የበለጡት፡ከእጁ፡ይድናሉ።

42እጁን፡በአገሮች፡ላይ፡ይዘረጋል፥የግብጽም፡ምድር፡አታመልጥም።

43በወርቅና፡በብርም፡መዝገብ፡ላይ፥በከበረችም፡በግብጽ፡ዕቃ፡ዅሉ፡ላይ፡ይሠለጥናል፤የልብያና፡ የኢትዮጵያ፡ሰዎችም፡ይከተሉታል።

44ከምሥራቅና፡ከሰሜን፡ግን፡ወሬ፡ያውከዋል፤ብዙ፡ሰዎችንም፡ይገድል፡ዘንድና፡ፈጽሞ፡ያጠፋ፡ዘንድ፡ በታላቅ፡ቍጣ፡ይወጣል።

45ንጉሣዊ፡ድንኳኑንም፡በባሕርና፡በከበረው፡በቅዱስ፡ተራራ፡መካከል፡ይተክላል፤ወደ፡ፍጻሜው፡ግን፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ይመጣል፥ማንም፡አይረዳውም።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source