Skip to content
← Daniel

Chapter 10 · Amharic

Daniel

1በፋርስ፡ንጉሥ፡በቂሮስ፡በሦስተኛው፡ዓመት፡ብልጣሶር፡ለተባለው፡ለዳንኤል፡ነገር፡ተገለጠለት፤ነገሩም፡ እውነት፡ነበረ፥ርሱም፡ታላቅ፡ጦርነት፡ነው፤ነገሩንም፡አስተዋለ፥በራእዩም፡ውስጥ፡ማስተዋል፡ተሰጠው።

2በዚያም፡ወራት፡እኔ፡ዳንኤል፡ሦስት፡ሳምንት፡ሙሉ፡ሳዝን፡ነበር።

3ማለፊያ፡እንጀራም፡አልበላኹም፥ሥጋና፡ጠጅም፡በአፌ፡አልገባም፥ሦስቱም፡ሳምንት፡እስኪፈጸም፡ድረስ፡ ዘይት፡አልተቀባኹም።

4ከመዠመሪያውም፡ወር፡በኻያ፡አራተኛው፡ቀን፡ጤግሮስ፡በተባለው፡በታላቁ፡ወንዝ፡አጠገብ፡ ሳለኹ፥ዐይኔን፡አነሣኹ፥

5እንሆም፥በፍታ፡የለበሰውን፡ጥሩም፡የአፌዝን፡ወርቅ፡በወገቡ፡ላይ፡የታጠቀውን፡ሰው፡አየኹ።

6አካሉም፡እንደ፡ቢረሌ፡ይመስል፡ነበር፥ፊቱም፡እንደ፡መብረቅ፡ምስያ፡ነበረ፥ዐይኖቹም፡እንደሚንበለበል፡ ፋና፥ክንዶቹና፡እግሮቹም፡እንደ፡ጋለ፡ናስ፥የቃሉም፡ድምፅ፡እንደ፡ብዙ፡ሕዝብ፡ድምፅ፡ነበረ።

7እኔም፡ዳንኤል፡ብቻዬን፡ራእዩን፡አየኹ፥ከእኔ፡ጋራ፡የነበሩ፡ሰዎች፡ግን፡ራእዩን፡አላዩም፤ነገር፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ግን፥ጽኑ፡መንቀጥቀጥ፡ወደቀባቸው፥ሊሸሸጉም፡ሸሹ።

8እኔም፡ብቻዬን፡ቀረኹ፡ይህንም፡ታላቅ፡ራእይ፡አየኹ፤ኀይልም፡አልቀረልኝም፥ደም፡ግባቴም፡ወደ፡ ማሸብሸብ፡ተለወጠብኝ፥ኀይልም፡ዐጣኹ።

9የቃሉንም፡ድምፅ፡ሰማኹ፤የቃሉንም፡ድምፅ፡በሰማኹ፡ጊዜ፡ደንግጬ፡በምድር፡ላይ፡በግንባሬ፡ተደፋኹ።

10እንሆም፥አንዲት፡እጅ፡ዳሰሰችኝ፥በጕልበቴና፡በእጄም፡አቆመችኝ።

11ርሱም፦እጅግ፡የተወደድኽ፡ሰው፡ዳንኤል፡ሆይ፥እኔ፡ዛሬ፡ወዳንተ፡ተልኬያለኹና፡የምነግርኽን፡ቃል፡ አስተውል፥ቀጥ፡ብለኽም፡ቁም፡አለኝ።ይህንም፡ቃል፡ባለኝ፡ጊዜ፡እየተንቀጠቀጥኹ፡ቆምኹ።

12ርሱም፡እንዲህ፡አለኝ፦ዳንኤል፡ሆይ፥አትፍራ፤ልብኽ፡ያስተውል፡ዘንድ፥ሰውነትኽም፡በአምላክኽ፡ ፊት፡ይዋረድ፡ዘንድ፡ካደረግኽበት፡ከመዠመሪያው፡ቀን፡ዠምሮ፡ቃልኽ፡ተሰምቷል፤እኔም፡ስለ፡ቃልኽ፡ መጥቻለኹ።

13የፋርስ፡መንግሥት፡አለቃ፡ግን፡ኻያ፡አንድ፡ቀን፡ተቋቋመኝ፤እንሆም፥ከዋነኛዎቹ፡አለቃዎች፡አንዱ፡ ሚካኤል፡ሊረዳኝ፡መጣ፤እኔም፡ከፋርስ፡ነገሥታት፡ጋራ፡በዚያ፡ተውኹት።

14ራእዩም፡ገና፡ለብዙ፡ዘመን፡ነውና፥በዃለኛው፡ዘመን፡ለሕዝብኽ፡የሚኾነውን፡አስታውቅኽ፡ዘንድ፡ አኹን፡መጥቻለኹ።

15ይህንም፡ቃል፡በተናገረኝ፡ጊዜ፡ፊቴን፡ወደ፡ምድር፡አቀረቀርኹ፥ዲዳም፡ኾንኹ።

16እንሆም፥የሰው፡ልጅ፡የሚመስል፡ከንፈሬን፡ዳሰሰኝ፤የዚያን፡ጊዜም፡አፌን፡ከፍቼ፡ተናገርኹ፡በፊቴም፡ ቆሞ፡የነበረውን፦ጌታዬ፡ሆይ፥ከራእዩ፡የተነሣ፡ሕመሜ፡መጣብኝ፥ኀይልም፡ዐጣኹ።

17ይህ፡የጌታዬ፡ባሪያ፡ከዚህ፡ከጌታዬ፡ጋራ፡ይናገር፡ዘንድ፡እንዴት፡ይችላል፧አኹንም፡ኀይል፡ ዐጣኹ፥እስትንፋስም፡አልቀረልኝም፡አልኹት።

18ደግሞ፡ሰው፡የሚመስል፡ዳሰሰኝ፥አበረታኝም።

19ርሱም፦እጅግ፡የተወደድኽ፡ሰው፡ሆይ፥አትፍራ፤ሰላም፡ለአንተ፡ይኹን፤በርታ፥ጽና፡ አለኝ።በተናገረኝም፡ጊዜ፡በረታኹና፦አበርትተኸኛልና፥ጌታዬ፡ይናገር፡አልኹ።

20ርሱም፡እንዲህ፡አለኝ፦ወዳንተ፡የመጣኹት፡ስለ፡ምን፡እንደ፡ኾነ፥ታውቃለኽን፧አኹንም፡ከፋርስ፡ አለቃ፡ጋራ፡እዋጋ፡ዘንድ፡እመለሳለኹ፤እኔም፡ስወጣ፥እንሆ፤የግሪክ፡አለቃ፡ይመጣል።

21ነገር፡ግን፥በእውነት፡ጽሑፍ፡የተጻፈውን፡እነግርኻለኹ፤በዚህም፡ነገር፡ከአለቃችኹ፡ከሚካኤል፡በቀር፡ ማንም፡የሚያጸናኝ፡የለም።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source