1አዳር፡በሚባለውም፡በዐሥራ፡ኹለተኛው፡ወር፡ከወሩም፡በዐሥራ፡ሦስተኛው፡ቀን፥የንጉሡ፡ትእዛዝና፡ ዐዋጅ፡ሊፈጸምበት፡በነበረው፡ቀን፥የአይሁድ፡ጠላቶች፡ሊሠለጥኑባቸው፡በነበረው፡ቀን፥አይሁድ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org በጠላቶቻቸው፡ላይ፡እንዲሠለጥኑ፡ነገሩ፡ተገለበጠ።
2አይሁድም፡ክፋታቸውን፡በሚሹት፡ሰዎች፡ላይ፡እጃቸውን፡ይዘረጉ፡ዘንድ፡በንጉሡ፡በአርጤክስስ፡አገሮች፡ ዅሉ፡በነበሩ፡ከተማዎቻቸው፡ውስጥ፡ተሰበሰቡ፤እነርሱንም፡መፍራት፡በአሕዛብ፡ዅሉ፡ላይ፡ወድቆ፡ ነበርና፥እነርሱን፡የሚቃወም፡ሰው፡አልነበረም።
3መርዶክዮስን፡መፍራት፡በላያቸው፡ስለ፡ወደቀ፡በያገሩ፡የነበሩ፡ዐዛውንትና፡ሹማምቶች፡ አለቃዎችም፥የንጉሡንም፡ሥራ፡የሚሠሩቱ፡ዅሉ፡አይሁድን፡አገዙ።
4ያ፡ሰው፡መርዶክዮስ፡ከፍ፡ከፍ፡እያለ፡ስለ፡ኼደ፡በንጉሡ፡ቤት፡ታላቅ፡ኾኖ፡ነበርና፥የመርዶክዮስም፡ ዝና፡በያገሩ፡ዅሉ፡ተሰምቶ፡ነበርና።
5አይሁድም፡ጠላቶቻቸውን፡ዅሉ፡በሰይፍ፡እየመቱ፡ገደሏቸው፥አጠፏቸውም፤በሚጠሏቸውም፡ላይ፡እንደ፡ ወደዱ፡አደረጉባቸው።
6አይሁድም፡በሱሳ፡ግንብ፡ዐምስት፡መቶ፡ያኽል፡ሰዎች፡ገደሉ፡አጠፉም።
8ፈርሰኔስ፥ደልፎን፥ፋስጋ፥ፋረዳታ፥
9በርያ፥ሰርባካ፥መርመሲማ፥ሩፋዮስ፥አርሳዮስ፥ዛቡታዮስ፡የሚባሉትን፥
10የሐመዳቱን፡ልጅ፡የአይሁድን፡ጠላት፡ዐሥሩን፡የሐማን፡ልጆች፡ገደሉ፤ነገር፡ግን፥ወደ፡ብዝበዛው፡ እጃቸውን፡አልዘረጉም።
11በዚያም፡ቀን፡በሱሳ፡ግንብ፡የተገደሉት፡ሰዎች፡ቍጥር፡ወደ፡ንጉሡ፡መጣ።
12ንጉሡም፡ንግሥቲቱን፡አስቴርን፦አይሁድ፡በሱሳ፡ግንብ፡ዐምስት፡መቶ፡ሰዎችንና፡ዐሥሩን፡የሐማ፡ ልጆች፡ገደሉ፡አጠፏቸውም፤በቀሩትስ፡በንጉሡ፡አገሮች፡እንዴት፡አድርገው፡ይኾን! አኹንስ፡ልመናሽ፡ ምንድር፡ነው፧ይሰጥሻል፤ሌላስ፡የምትሺው፡ምንድር፡ነው፧ይደረጋል፡አላት።
13አስቴርም፦ንጉሡን፡ደስ፡ቢያሠኘው፥በሱሳ፡የሚኖሩ፡አይሁድ፡ዛሬ፡እንደተደረገው፡ትእዛዝ፡ነገ፡ ደግሞ፡ያድርጉ፤ዐሥሩም፡የሐማ፡ልጆች፡በግንድ፡ላይ፡ይሰቀሉ፡አለች።
14ንጉሡም፡ይህ፡ይደረግ፡ዘንድ፡አዘዘ፤ዐዋጅም፡በሱሳ፡ተነገረ፤ዐሥሩንም፡የሐማን፡ልጆች፡ሰቀሉ።
15በሱሳም፡የነበሩ፡አይሁድ፡አዳር፡በሚባለው፡ወር፡በዐሥራ፡አራተኛው፡ቀን፡ደግሞ፡ተሰብስበው፡በሱሳ፡ ሦስት፡መቶ፡ያኽል፡ሰዎች፡ገደሉ፤ነገር፡ግን፥ወደ፡ብዝበዛው፡እጃቸውን፡አልዘረጉም።
16የቀሩትም፡በንጉሡ፡አገር፡ያሉ፡አይሁድ፡ተሰብስበው፡ለሕይወታቸው፡ቆሙ፥ከጠላቶቻቸውም፡ ዐረፉ፤ከሚጠሏቸውም፡ሰባ፡ዐምስት፡ሺሕ፡ገደሉ፤ነገር፡ግን፥ወደ፡ብዝበዛው፡እጃቸውን፡አልዘረጉም።
17አዳር፡በሚባለው፡ወር፡በዐሥራ፡ሦስተኛው፡ቀን፡ይህ፡ተደረገ፤በዐሥራ፡አራተኛውም፡ቀን፡ ዐረፉ፥የግብዣና፡የደስታም፡ቀን፡አደረጉ።
18በሱሳ፡የነበሩት፡አይሁድ፡ግን፡በዐሥራ፡ሦስተኛውና፡በዐሥራ፡አራተኛው፡ቀን፡ተሰበሰቡ፤በዐሥራ፡ ዐምስተኛውም፡ቀን፡ዐረፉ፥የመጠጥና፡የደስታም፡ቀን፡አደረጉት።
19ስለዚህም፡በመንደሮችና፡ባልተመሸጉ፡ከተማዎች፡የሚኖሩ፡አይሁድ፡አዳር፡በሚባለው፡ወር፡ዐሥራ፡ አራተኛውን፡ቀን፡የደስታና፡የመጠጥ፡የመልካምም፡ቀን፥ርስ፡በርሳቸውም፡ስጦታ፡የሚሰጣጡበት፡ቀን፡ ያደርጉታል።
20መርዶክዮስም፡ይህን፡ነገር፡ጻፈ፥በንጉሡም፡በአርጤክስስ፡አገሮች፡ዅሉ፡በቅርብና፡በሩቅ፡ወዳሉት፡ አይሁድ፡ዅሉ፡ደብዳቤዎችን፡ላከ።
21በየዓመቱም፡አዳር፡በሚባለው፡ወር፡ዐሥራ፡አራተኛውና፡ዐሥራ፡ዐምስተኛው፡ቀን፥
22አይሁድ፡ከጠላቶቻቸው፡ዕረፍትን፡ያገኙበት፡ቀን፥ወሩም፡ከሐዘን፡ወደ፡ደስታ፡ከልቅሶም፡ወደ፡ መልካም፡ቀን፡የተለወጠበት፡ወር፡ኾኖ፡ይጠብቁት፡ዘንድ፥የግብዣና፡የደስታም፡ቀን፥ርስ፡በርሳቸውም፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ስጦታ፡የሚሰጣጡበትና፡ለድኻዎች፡ስጦታ፡የሚሰጡበት፡ቀን፡ያደርጉት፡ዘንድ፡አዘዛቸው።
23አይሁድም፡ለመሥራት፡የዠመሩትን፥መርዶክዮስም፡የጻፈላቸውን፡ያደርጉ፡ዘንድ፡ተቀበሉት፤
24አጋጋዊው፡የሐመዳቱ፡ልጅ፡የአይሁድ፡ዅሉ፡ጠላት፡ሐማ፡አይሁድን፡ያጠፋ፡ዘንድ፡ተተንኵሎ፡ ነበር፤ሊደመስሳቸውና፡ሊያጠፋቸውም፡ፉር፡የሚባል፡ዕጣ፡ጥሎ፡ነበር።
25አስቴርም፡ወደንጉሡ፡ፊት፡በገባች፡ጊዜ፡በአይሁድ፡ላይ፡የተተነኰለው፡ክፉ፡ተንኰል፡በራሱ፡ላይ፡ እንዲመለስ፥ርሱና፡ልጆቹም፡በግንድ፡ላይ፡እንዲሰቀሉ፡በደብዳቤው፡አዘዘ።
26ስለዚህም፡እነዚህ፡ቀኖች፡እንደ፡ፉር፡ስም፡ፉሪም፡ተባሉ።በዚህም፡ደብዳቤ፡ስለተጻፈው፡ቃል፡ ዅሉ፥ስላዩትና፡ስላገኟቸውም፡ነገር፡ዅሉ፥
28አይሁድ፡እነዚህን፡ኹለት፡ቀኖች፡እንደ፡ጽሕፈቱና፡እንደ፡ጊዜው፡በየዓመቱ፡ይጠብቁ፡ ዘንድ፥እነዚህም፡ቀኖች፡በየትውልዳቸውና፡በየወገናቸው፡በያገራቸውም፡በየከተማቸውም፡የታሰቡና፡የተከበሩ፡ ይኾኑ፡ዘንድ፥እነዚህም፡የፉሪም፡ቀኖች፡በአይሁድ፡ዘንድ፡እንዳይሻሩ፥መታሰባቸውም፡ከዘራቸው፡ እንዳይቈረጥ፥በራሳቸውና፡በዘራቸው፡ወደ፡እነርሱም፡በተጠጉት፡ዅሉ፡ላይ፡እንዳይቀር፡ሥርዐት፡አድርገው፡ ተቀበሉ።
29የአቢካኢልም፡ልጅ፡ንግሥቲቱ፡አስቴርና፡አይሁዳዊው፡መርዶክዮስ፡ይህችን፡ስለ፡ፉሪም፡የምትናገረውን፡ ኹለተኛዪቱን፡ደብዳቤ፡በሥልጣናቸው፡ዅሉ፡ያጸኗት፡ዘንድ፡ጻፉ።
30ደብዳቤዎቹንም፡በአርጤክስስ፡መንግሥት፡በመቶ፡ኻያ፡ሰባቱ፡አገሮች፡ወዳሉ፡አይሁድ፡ዅሉ፡በሰላምና፡ በእውነት፡ቃል፡ላኩ።
31እነዚህንም፡የፉሪም፡ቀኖች፥አይሁዳዊው፡መርዶክዮስና፡ንግሥቲቱ፡አስቴር፡እንዳዘዙ፥ለራሳቸውና፡ ለዘራቸውም፡የጾማቸውንና፡የልቅሷቸውን፡ነገር፡ለማክበር፡እንደ፡ተቀበሉ፥በየጊዜያቸው፡ያጸኑ፡ዘንድ፡ጻፉ።
32የአስቴርም፡ትእዛዝ፡ይህን፡የፉሪምን፡ነገር፡አጸና፤በመጽሐፍም፡ተጻፈ።